መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 9

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ «ወደ ፈርዖን ሂድና እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ይህን ይናገራል፡፡ «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡»
2ብትልና አሁንም ከልክለህ ብታስቀራቸው፣
3የእግዚአብሔር እጅ መስክ ላይ ባለው ከብትህ፣ በፈረሶችህ፣ በአህዮችህ፣ በግመሎችህ፣ በፍየሎችህና በበጎችህ ላይ ይሆናል፤ አስከፊ በሽታም ያመጣል፡፡
4እግዚአብሔር በእስራኤል ከብትና በግብፅ ከብት መካከል ልዩነት አድርጓል፡- የእስራኤል ከብት አይሞትም፡፡
5ጊዜ ወስኖአል፤ «በምድሪቱ ላይ ይህን የማደርገው ነገ ነው» ብሎአል፡፡
6ይህን በሚቀጥለው ቀን አደረገው፡- የግብፅ ከብት ሁሉ ሞተ፡፡ ከእስራኤል ከብት ግን አንድም አልሞተም፡፡
7ተከታትሎ አጣራ፣ ከእስራኤል ከብት አንድም እንኳ አለመሞቱን ተረዳ፡፡ ነገር ግን ልቡ ደንድኖ ነበር፤ ስለዚህ ሕዝቡ እንዲሄድ አልፈቀደም፡፡
8እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን አላቸው፤ «ከምድጃ ላይ እፍኝ ዐመድ ውሰዱና አንተ ሙሴ ወደ ሰማይ ፈርዖን እያየ ዐመዱን በትነው፡፡
9በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ትቢያ ይሆናል፡፡ ይህም በመላው የግብፅ ምድር በሰውና በእንስሳት ላይ ዕባጭና ቊስል ያመጣል፡፡»
10ስለዚህ ሙሴና አሮን ከምድጃ ዐመድ ወስደው ከፈርዖን ፊት ለፊት ቆሙ፡፡ ከዚያም ሙሴ ዐመዱን ወደ ሰማይ በተነው፡፡ ዐመዱ በሰውና በእንስሳ ላይ የሚወጣ ዕባጭና ቊስልን አመጣ፡፡
11በእነርሱና በሌች ግብፃውያን ሁሉ ላይ ወጥቶ በነበረው ዕባጭ ምክንያት ጠንቋዮቹ በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፡፡
12እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ስለ አደነደነው፣ ፈርዖን ሙሴንና አሮንን አልሰማቸውም፡፡ ይህም የሆነው ፈርዖን እንደዚህ እንደሚደርግ እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮት እንድ ነበረው ነው፡፡
13እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «በጠዋት ተነሣና ከፈርዖን ፊት ለፊት ቁም፤ እንደዚህ ብለህም ንገረው፤ ‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናገሯል፡- «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡
14ጊዜ በአንተ በራስህ፣ በአገልጋዮችህና በሕዝብህ ላይ መቅሠፍቴን ሁሉ እልካለሁ፡፡ ይህን የማየደርገውም በድምር ሁሉ እንደ እኔ ያለ እንደሌለ እንድታውቅ ነው፡፡
15ጊዜ እጄን ዘርግቼ አንተንና ሕዝብህን በበሽታ በመምታት ከምድር ባጠፋኋችሁ ነበር፡፡
16ግን በሕይወት እንድትቈይ ያደረግሁህ፣ ኀይሌን እንድገልጥብህና ስሜም በምድር ሁሉ እንዲታወቅ ነው፡፡
17ሕዝቤን እንዳይሄድ በማድረግ በሕዝቤ ላይ ራስህን እያሳበይህ ነው፡፡
18ነገ በዚህ ጊዜ ከተመሠረተችበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ በግብፅ ታይቶ የማይታወቅ ከባድ የበረዶ ማዕበል አመጣለሁ፡፡
19አሁን ሰው ላክና ከብትህን፣ በመስክ ላይ ያለህን ማንኛውንም ነገር ወደ ጠለያ ስፍራ ሰብስብ፡፡ መስክ ላይ የቀረና ወደ ቤት ያልመጣ ማንኛውም ከብትና ሰው ሁሉ በረዶው ይወርድባቸውና ይሞታሉ፡፡»
20አገልጋዮች የእግዚአብሔር ቃል የተቀበሉት ባሮቻቸውንና ከብቶቻቸውን ወደ ቤት ለማምጣት ተጣደፉ፡፡
21የእግዚአብሔርን ቃል ከምር ያልተቀበሉት ግን ባሮቻቸውንና ከብታቸውን መስክ ላይ ተዉ፡፡
22ሙሴን እንዲህ አለው፤ «በሁሉም የግብፅ ምድር፣ በሕዝብ፣ በእንስሳትና በመላው የግብፅ ምድር መስክ ላይ ባሉ ተክሎች ሁሉ ላይ በረዶ እንዲወርድ እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፡፡»
23በትሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጐድጓድ፣ በረዶና መብረቅ ወደ ምድር ላከ፡፡በግብፅም ምድር ላይ በረዶ አዘነበ፡፡
24ግብፅ አገር ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ በምድሪቱ ሁሉ ያልታየ እጅግ ከባድ የበረዶና የመብረቅ ቅልቅል ነበር የዘነበው፡፡
25የግብፅ ምድር፣ በረዶው መስክ ላይ ያለውን ማንኛውንም ነገር፣ ሰውንም እንስሳቱንም መታ፡፡ በመስክ ያለውን ተክል ሁሉ መታው፣ ዛፉንም ሁሉ ሰባበረው፡፡
26እስራኤላውያን በሚኖሩበት በጌሤም ምድር ብቻ በረዶ አልነበረም፡፡
27በኋላ ፈርዖን ሙሴንና አሮንን እንዲጠሩ ሰዎችን ላከ፡፡ እንዲህም አላቸው፤ «በዚህ ጊዜ ኀጢአት ፈጽሜአለሁ፡፡ እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን ኀጢአተኞች ነን፡፡
28እግዚአብሔር ጸልዩ፤ ምክንያቱም ከባዱ ነጐድጓድና በረዶ እጅግ በዝቶብናል፡፡ እለቅቃችኋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ እዚህ አትቆዩም፡፡
29ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ «ከከተማዪቱ እንደ ወጣሁ፣ እጆቼን ወደ እግዚአብሔር እዘረጋለሁ፡፡ ነጐድጓዱ ያቆማል፣ በረዶም አይኖርም፡፡ በዚህ መንገድ አንተ ምድር የእግዚአብሔር መሆኗን ታውቃለህ፡፡
30ግን አንተንና አገልጋዮችህን በሚመለከት እግዚአብሔር አምላክን ገና በእውነት እንደማታከብሩ ዐውቃለሁ፡፡»
31ጊዜ ተልባው አብቦ፣ ገብሱም ፍሬ በመያዝ ላይ ነበረ፣ ተልባውና ገብሱ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል፡፡
32አጃው ግን ቈይተው የሚደርሱ ሰብሎች በመሆናቸው አልተጐዱም፡፡
33ሙሴ ከፈርዖንና ከከተማዪቱ ሲወጣ፣ እጆቹን ወደ እግዚአብሔር ዘረጋ፤ ነጐድጓዱና በረዶው ቆሙ፤ ዝናብም አልዘነበም፡፡
34ፈርዖን ዝናቡ፣ በረዶውና ነጐድጓዱ መቆሙን ሲያይ፣ እንደ ገና ኀጢአት አደረገ፤ ከአገልጋዮቹ ጋርም በአንድነት ልቡን አደነደነ፡፡
35የፈርዖን ልብ ስለ ደነደነ፣ የእስራኤል ሕዝብ እንዲሄዱ አልፈቀደም፡፡ ይህም የሆነው ፈርዖን ልቡን እንድሚያደነድን እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮት የነበረው መንገድ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።