መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 8

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «ወደ ፈርዖን ሂድና እንዲህ በለው፤ ‹እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡
2ካልህ፣ አገርህን በሙሉ በጓጕንቸው መቅሠፍት እመታዋለሁ፡፡
3ጓጕንቸር ይርመሰመሳል፡፡ ጓጕንቸሮቹ ከወንዙ ይወጡና ወደ ቤትህ፣ ወደ መኝታ ክፍልህና ወደ ዐልጋህ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ወደ አገልጋዮችህም ቤቶች ውስጥ ይገባሉ፡፡ ወደ ሕዝብህ፣ ወደ ምድጆችህና ወደ ቡሃቆችም ይዛመታሉ፡፡
4ጓጕንቸሮቹ አንተን፣ ሕዝብህንና አገልጋዮችህን ሁሉ ይመታሉ፡፡»
5ለሙሴ እንዲህ አለ፤ «አሮንን፣ እጅህንና በትርህን በወንዞች፣ በምንጮችና በቦዮች ላይ ዘርጋና በግብፅ ምድር ላይ ጓጕንቸሮች እንዲወጡ አድርግ» በለው፡፡
6በግብፅ ውሆች ላይ እጁን ዘረጋ፤ ጓጕንቸዎቹም ወጥተው የግብፅን ምድር ሸፈኑት፡፡
7ጠንቋዮቹም በምትሃቸው ያንኑ አደረጉ፤ ጓጕንቸሮቹ በግብፅ ምድር ላይ እንዲወጡ አደረጉ፡፡
8ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ፣ «ጓጕንቸሮቹን ከእኔና ከሕዝቤ ላይ አንዲያስወግድ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ፡፡ ከዚያም ለእግዚአብሔር እንዲሠዉ ሕዝቡን እለቃቸዋለሁ» አላቸው፡፡
9ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ «ጓጕንቸሮቹ ከአንተና ከቤቶችህ እንዲወገዱ፣ በወንዙ ውስጥ ብቻ ግን እንዲቈዩ፣ ለአንተ፣ ለአገልጋዮችህና ለሕዝብህ የምጸልይበትን ጊዜ ለእኔ መንገሩ የአንተ ድርሻ ነው፡፡»
10«ነገ» አለው፡፡ ሙሴም ፈርዖንን መልሶ፣ «እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም እንደሌለ እንድታውቅ አንተ እንደምትለው ይሁን፡፡
11ጓጕንቸሮቹ ከአንተ፣ ከቤቶችህ ከአገልጋዮችህና ከሕዝብህ ይወገዳሉ፡፡ በወንዙ ውስጥ ብቻ ግን ይቈያሉ» አለው፡፡
12አሮን ከፈርዖን ወጥተው ሄዱ፡፡ ሙሴም እግዚአብሔር በፈርዖን ላይ ስላመጣቸው ጓጕንቸሮች ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፡፡
13ሙሴ እንደ ለመነው አደረገ፡- ጓጕንቸሮቹ በየቤቱ፣ በየግቢውና በየሜዳው ሞቱ፡፡
14ሕዝቡ የሞቱትን ሰብስበው ከመሯቸው፤ ምድሩም ከረፋ፡፡
15ነገር ግን ፈርዖን ፋታ መገኘቱን ሲያይ፣ ልቡን አደነደነ፤ እንደዚህ ያደርጋል ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮ እንድ ነበረ፣ ሙሴንና አሮንንም አልሰማቸውም፡፡
16ለሙሴ እንዲህ አለ፤ «አሮንን እንዲህ በለው ‹በመላው የግብፅ ምድር ተባይ እንዲሆን የምድሩን ትቢያ በበትርህ ምታ፡፡»
17እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፡- አሮን እጁን ዘርግቶ በበትሩ የምድሩን ትቢያ መታው፡፡ በሰውና በእንስሳ ላይ ተባይ መጣ፡፡ የምድሩ ትቢያ ሁሉ በመላው የግብፅ ምድር ተባይ ሆነ፡፡
18በምትሃቸው ተባይ እንዲመጣ ሙከራ አደረጉ፤ ነገር ግን አልቻም፡፡ በሰውና በእንስሳ ላይ ተባዮች ነበሩ፡፡
19ጠንቋዮቹ ታዲያ ፈርዖንን፣ «ይህ የእግዚአብሔር ጣት ነው» አሉት፡፡ ነገር ግን የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ እነርሱንም ለማድመጥ እምቢ አለ፡፡ ይህም የሆነው ፈርዖን እንዲህ እንደሚያደርግ እግዚአብሔር ተናግሮት በነበረው መሠረት ነው፡፡
20እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «በማለዳ ተነሣና ፈርዖን ወደ ወንዙ ሲወጣ በፊት ለፊቱ ቁም፡፡ እንደዚህም ብለህ ንገረው፤ ‹እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡
21የማትለቅ ከሆነ ግን፣ በአንተ፣ በአገልጋዮችህና በሕዝብህ ላይ፣ ወደ ቤቶችህም ውስጥ የዝንብ መንጋ እልካለሁ፡፡ የግብፃውያን ቤቶች በዝንብ መንጋ ይሞላሉ፤ የሚቆሙበት ምድርም እንኳ ዝንብ ብቻ ይሆናል፡፡
22ግን በዚያ ቀን የዝንብ መንጋ እንዳይገኝባ፣ ሕዝቤ የሚኖርባትን የጌሤምን ምድር በተለየ ሁኔታ እይዛታለሁ፡፡ እኔ እግዚአብሔር በዚህ ምድር እንዳለሁ እንድታውቅ ይህ ይሆናል፡፡
23በሕዝቤና በሕዝብህ መካከል ልዩነት እንዲኖር አደርጋለሁ፡፡ ይህ ተአምራዊ ምልክት ነገ ነው የሚሆነው፡፡»
24እግዚአብሔር እንዲሁ አደረገ፤ ጥቅጥቅ ያለ የዝንብ መንጋም ወደ ፈርዖን ቤትና ወደ አገልጋዮቹ ቤቶች መጣ፡፡ በመላው የግብፅ ውስጥ ምድሩ ከዝንቡ መንጋ የተነሣ ተበላሽቶ ነበር፡፡
25ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ፣ «ሂዱና በምድራችሁ ለአምላካችሁ ሠዉ» አላቸው፡፡
26እንዲህ ለማድረግ ለእኛ ትክክል አይደለም፤ ለአምላካችን በእግዚአብሔር የምንሠዋቸው መሥዋዕቶች ለግብፃውያን አስጸያፊዎች ናቸውና፡፡ ለግብፃውያን አስጸያፊ የሆኑትን መሥዋዕቶች እያን በፊታቸው ብንሠዋ፣ በድንጋይ አይወግሩንም?
27ባዘዘን መሠረት፣ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሠዋት ያለብን ወደ ምድረ በዳወ የሦስት ቀን ጕዞ ሄደን ነው» አለ፡፡
28«እንድትሄዱና በምድረ በዳው ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር እንድትሠዉ እፈቅድላችኋለሁ፡፡ ርቃችሁ መሄድ ግን የለባችሁም፡፡ ለእኔም ጸልዩልኝ» አለ፡፡
29«ከአንተ ወጥቼ እንደ ሄድሁ፣ የዝንቦቹ መንጋ አንተን ፈርዖንን፣ አገልጋዮችህንና ሕዝብህን ነገ ለቀው እንዲሄዱ ወደ እግዚአብሔር እጸልይልሃለሁ፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለመሠዋት ሕዝባችን እንዲሄድ ባለመፍቀድ ከእንግዲህ ወዲያ ልታታልለን አይገባም» አለ፡፡
30ከፈርዖን ወጥቶ ሄደና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡
31እግዚአብሔር ሙሴ እንደ ለመነው አደረገ፡- የዝንቡን መንጋ ከፈርዖን፣ ከአገልጋዮቹና ከሕዝቡ ላይ አስወገደ፡፡ አንድም አልቀረም፡፡
32ነገር ግን ፈርዖን በዚህም ጊዜ ልቡ አደነደነ፤ ሕዝቡም እንዲሄድ አልፈቀደም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።