መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 10

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «የፈርዖንና የአገልጋዮቹን ልብ አደነድናለሁና ወደ ፈርዖን ሂድ፡፡ እነዚህን የተአምራቴን ምልክቶች ለማሳየት ይህን አድርጌአለሁ፡፡
2ይህን ያደረግሁት ግብፃውያንን እንዴት በከባድ አያያዝ እንደያዝኋቸውና በመካከላቸውም የተአምራትን ልዩ ልዩ ምልክቶች እንዳሳየሁ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ እንድትነግሯቸው ነው፡፡ በዚህ መንገድ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፡፡
3አሮንም ወደ ፈርዖን ሄደው እንዲህ አሉት፤ «የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- ‹ራስህን በፊቴ ለማዋረድ እምቢ የምትለው እስከ መቼ ነው? እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡
4ግን ሕዝቤን አልለቅም ብትል፣ እነሆ፣ በነገው ቀን በአገርህ ላይ አንበጣዎችን አመጣለሁ፡፡
5ማንም ሰው መድሩን ማየት እስከማይችል ድረስ የምድሩን ገጽ ይሸፍኑታል፡፡ ከበረዶው አምልጦ የቀረውን ሁሉ ይበሉታል፡፡ መስክ ላይ የሚያድግላችሁንም ዛፍ ሁሉ ይበሉታል፡፡
6አንበጣዎቹ የአንተን፣ የአገልጋዮችህን ቤቶች ሁሉ ይሞሏቸዋል፤ ይህም፣ አባትህም አያትህም በዚህ ምድር ላይ መኖር ከጀመሩበት ቀን አነሥቶ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ነው፡፡» ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ወጥቶ ሄደ፡፡
7ፈርዖንን፣ «ይህ ሰው ወጥመድ የሚሆንብን እስከ መቼ ነው? አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዲያመልኩት እስራኤላውያን ይሂዱ፡፡ ግብፅ መጥፋቷን ገና አልተገነዘብህምን?» አሉት፡፡
8ሙሴና አሮን፣ «ሂዱ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ፡፡ ነገር ግን የሚሄዱት የትኞቹ ናቸው?» ወዳላቸው ወደ ፈርዖን እንደገና እንዲመጡ ተደረገ፡፡
9የምንሄደው ከወጣቶቻችንና ከሽማግሌዎቻችን፣ ከወንድና ከሴት ልጆችን ጋር ነው፡፡ ለእግዚአብሔር በዓል ማክበር ስለሚገባን፣ የበግና የፍየል መንጎቻችንን፣ የቀንድ ከብቶቻችንንም ይዘን እንሄዳለን» አለ፡፡
10ፈርዖንም እንዲህ አላቸው፤ «እናንተንና ታናናሽ ልጆቻችሁን ስለችሁ፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡ ነገር ግን ተመልከቱ፣ ክፉ ነገር ዐስባችኋል፡፡
11ከመካከላችሁ ወንዶች ብቻ ይሂዱና እግዚአብሔርን ያምልኩ፤ የምትፈልጉት ያንን ነውና፡፡» ከዚያም በኋላ ሙሴና አሮን ከፈርዖን ዘንድ እንዲወጡ ተደረገ፡፡
12እግዚአብሔርም ሙሴን፣ «አንበጣዎች የግብፅን ምድር እንዲወርሩትና ከበረዶው ተርፎ የቀረውን፣ በምድሩ ያለውን ተክል ሁሉ እንዲበሉት እጅህን በግብፅ ምድር ላይ ዘርጋ» አለው፡፡
13ሙሴም በትሩን በግብፅ ምድር ላይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም በዚያ ቀንና ሌሊት ሁሉ የምሥራቅ ነፋስ በምድሩ ላይ እንዲነፍስ አደረገ። ማለዳ ላይ የምሥራቁ ነፋስ አንበጣዎቹን አምጥቶ ነበር።
14በግብፅ ምድር ሁሉ ተሠራጩ፤ አገሩንም ሁሉ ወረሩት። እንደዚህ እጅግ የበዙ አንበጣዎች በምድሩ ውስጥ ከዚህ በፊት አልነበሩም፤ ወደፊትም አይኖሩም።
15ጨለማ እስኪሆን ድረስ የምድሩን ሁሉ ገጽ ሸፈኑት። በምድሩ ላይ ያለውን ማንኛውንም ተክልና ከበረዶው ተርፎ የቀረውን የዛፍ ፍሬ ሁሉ በሉት። በግብፅ ምድር ሁሉ ለምለም ቅጠል ያለው ተክል አልቀረም፤ በመስክም ላይ ምንም ዛፍ አልነበረም።
16ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአምላካችሁ በእግዚአብሔርና በእናንተ ላይ ኀጢአት ሠርቻለሁ።
17እንግዲህ አሁን ኀጢአቴን ይቅር በሉኝና ይህን ሞት ከእኔ እንዲያስወግድልኝ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ።”
18ስለዚህ ሙሴ ከፈርዖን ዘንድ ወጥቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
19አንበጣዎቹን ለቃቅሞ ወደ ቀይ ባሕር የሚከትታቸውን ብርቱ የምዕራብ ነፋስ አመጣ፤ በግብፅ ግዛት ሁሉ የቀረ አንድም አንበጣ አልነበረም።
20ነገር ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው፣ ፈርዖን እስራኤላውያንን አልለቀቃቸውም።
21ሙሴን፣ “በግብፅ ምድር ላይ የሚዳስስ ከባድ ጨለማ እንዲሆን እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ” አለው።
22እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በግብፅም ምድር ሁሉ ለሦስት ቀን ድቅድቅ ጨለማ ሆነ።
23ቀኖች አንዱ ሌላውን ማየት አልቻለም፤ ከቤቱም የወጣ ማንም የለም። ለእስራኤላውያን ግን በሚኖሩበት ስፍራ ብርሃን ነበራቸው።
24ፈርዖን ሙሴን አስጠርቶ፣ “ሂዱ እግዚአብሔርን አምልኩ። ቤተ ሰቦቻችሁም እንኳ ዐብረዋችሁ መሄድ ይችላሉ፤ በጎቻችሁና ከብቶቻችሁ ግን እዚህ መቅረት አለባቸው” አለው።
25እንዲህ አለው፤ “ለአምላካችን ለእግዚአብሔር እንድንሠዋቸው ለመሥዋዕትና ለሚቃጠል መሥዋዕት እንስሳቱንም ልትሰጠን ይገባል።
26ከብቶቻችንም ከእኛ ጋር መሄድ አለባቸው፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማምለክ ልንወስዳቸው ይገባልና ከእነርሱ ሰኮናም እንኳ እዚህ አይቀርም። ምክንያቱም እግዚአብሔርን በምን እንደምናመልከው እዚያ እስክንደርስ ድረስ አናውቅም።”
27ግን የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው ፈርዖን ሕዝቡን አልለቀቃቸውም።
28ሙሴን፣ “ሂድ ከእኔ ዘንድ! ፊቴን እንዳታይ ተጠንቀቅ፤ ፊቴን ባየህበት ቀን ትሞታለህና” አለው።
29ሙሴም፣ “አንተ ራስህ ተናግረሃል። ፊትህን እንደ ገና አላየውም” አለው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።