1ሙሴን እንዲህ አለው፤ «ልብ በል፤ አንተን ለፈርዖን እንደ አምላክ አድርጌሃለሁ፡፡ ወንድምህ አሮን ነቢይህ ይሆናል፡፡
2እንድትናገር ያዘዝሁህን ሁሉ ትናራለህ፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ከምድሩ እንዲለቀ፣ ወንድምህ አሮን ለፈርዖን ይናገራል፡፡
3ነገር ግን እኔ የፈርዖንን ለብ አደነድነዋሁ፤ የተአምራቴን ብዙ ምልክቶች፣ ብዙ ድንቆችም በግብፅ ምድር አሳያለሁ፡፡
4ነገር ግን ፈርዖን አይሰማችሁም፤ ስለዚህ እጄን በግብፅ ላይ አደርጋሁ፤ ሰራዊቱን፣ ሕዝቤን፣ የእስራኤልን ልጆች በታላቅ ፍርድ ከግብፅ ምድር አወጣለሁ፡፡
5በግብፅ ላይ ስዘረጋና እስራኤላውያንን ከመካከላቸው ሳወጣ፣ ግብፃውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፡፡»
6አሮን እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ፈጸሙ፡፡
7ባጋገሩት ጊዜ፣ የሙሴ ዕድሜ ሰማንያ፣ የአሮን ደግሞ ሰማንያ ሦስት ነበር፡፡
8ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤
9‹ተአምር አሳዩ› ሲላችሁ፣ አሮንን እንዲህ በለው፤ ‹በትርህን ውሰድና በፈርዖን ፊት ጣለው፤ እባብም ይሀናል፡፡»›
10ሙሴ አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው፣ እግዚአብሔር አዝዞአቸው የነበረውን አደረጉ፡፡ አሮን በትሩን በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት ጣለው፤ እባብም ሆነ፡፡
11ደግሞ ለጥበበኛ ሰዎቹና ለጠንቋዮቹ ጥሪ አደረገ፡፡ እነርሱም በምትሀታቸው ያንኑ አደረጉ፡፡
12እያንዳንዱ ሰው በትሩን ጣለ፤ በትሮቹም እባብ ሆኑ፣ ነገር ግን የአሮን በትር የእነርሱን እባቦች ዋጣቸው፡፡
13አስቀድሞ እንደ ተናገረው፣ የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ አልሰማምም፡፡
14እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «የፈርዖን ልብ ደንድኖአል፤ ሕዘቡም እንዲሄዱ አይፈቅድም፡፡
15ወደ ውሃው በሚሄድበት ጊዜ፣ በጠዋት ወደ ፈርዖን ሂድ፡፡ እንዳገኘውም በወንዙ ዳር ቁም፤ ወደ እባብነት ተለውጦ የነበረውን በትርህን ውሰድ፡፡
16እንዲህ በለው፤ ‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ይህን እንድናገር ወደ አንተ ላከኝ፤ «በምድረ በዳ እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፤ እስካሁን ድረስ አልሰማህም፡፡»
17የሚናገረው ይህ ነው፤ «እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፡፡ የአባይን ወንዝ ውሀ በእጄ በያዝሁት በትር እመታዋለሁ፣ ወንዙም ወደ ደምነት ይለወጣል፡፡
18ውስጥ የሚገኙት ዓሦች ይሞታሉ፤ ወንዙ ይከረፋል፡፡ግብፃውያኑም ከወንዙ ውሀ መጠጣት አይችሉም፡፡»
19ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ አሮንን፣ ‹በትርህን ውሰድና ውሀቸው ደም እንዲሆን፣ በግብፅ ውሀዎች ላይ፣ በወንዞቻቸውም፣ በምንጮቻቸውም፣ በውሀ ማጠራቀሚያዎቻቸውና በኩሬዎቻቸው ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ ብለህ ንገረው፡፡ በመላው የግብፅ ምድር፣ ከዕንጨትና ከድንጋይ በተሠሩ ውሀ መያዣዎች ያለው ውሀም እንኳ ደም እንዲሆን ይህን አድርግ፡፡»›
20ሙሴና አሮን እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ አሮን በትሩን አንሥቶ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት የወንዙን ውሀ መታው፡፡ የወንዙ ውሀ በሙሉ ወደ ደምነት ተለወጠ፡፡
21ውስጥ ያለው ዓሣ ሞተ ወንዙም መከርፋት ጀመረ፡፡ ግብፃውያኑ ከወንዙ ውሀ መጠጣት አልቻም፤ ደሙም በግብፅ ምድር በየትኛውም ስፍራ ነበረ፡፡
22የግብፅ ጠንቋዮችም በምትሀታቸው ያንኑ ዐይነት ነገር አደረጉ፡፡ ስለዚህ የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ እግዚአብሔር ይሆናለ ብሎ ተናግሮት እንደ ተናገረውም ሙሴንና አሮንን ለመስማት እምቢ አለ፡፡
23ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ለዚህ ጉዳይ ትኵረትም እንኳ አልሰጠም፡፡
24ግብፃውያኑ ሁሉ በወንዙ ዙሪያ የሚጠጣ ውሀ ለማግኘት ቈፈሩ፤ ነገ ርግን የወንዙን ውሀ መጠጣት አልቻሉም፡፡
25እግዚአብሔር ወንዙን ከመታው በኋላ ሰባት ቀን ዐለፈ፡፡