1ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን፣ «በፈርዖን ላይ የማደርገውን አሁን ታያለህ፡፡ ከጽኑዕ እጄ የተነሣ ሕዝቡን ይለቃቸዋልና፣ ይህን ታያለህ፡፡ ከጽኑዕ እጄ የተነሣ ሕዝቡን ከምድሩ ያስወጣቸዋል» አለው፡፡
2ለሙሴ እንዲህ አለው፤ «እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡
3እኔ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን በስሜ፣ በእግዚአብሔር ለእነርሱ አልታወቅሁላቸውም ነበር፡፡
4የተሰደዱባትን፣ በእንግድነት የኖሩባትን የከነዓንን ምድር ልሰጣቸው፣ ከእነርሱ ጋር ኪዳን አጽንቻለሁ፡፡
5ደግሞም ግብፃውያን ባሪያ ያደረጓቸውን የአስራኤላውያንን ጩኸት ሰምቻለሁ፤ ኪዳኔንም አስታውሻለሁ፡፡
6ስለዚህ ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‹እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡ በግብፃውያን ሥር ከምትኖሩባት ባርነት እታደጋችኋለሁ፤ ከአገዛዛቸውም ነፃ አወጣችኋለሁ፡፡ በታላቅ ፍርድና ኀይሌን በማሳየት እታደጋችኋለሁ፡፡
7አድርጌ ወደ ራሴ እወስዳችኋለሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፡፡ ግብፃውያን ከጫኑባችሁ ባርነት ነፃ ያወጣኋችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፡፡
8ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ልሰጥ ቃል ወደገባሁባት ምድር አስገባችኋለሁ፡፡ ምድሪቱን ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ፡፡ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡»
9ይህን ለእስራኤላውያን በነገራቸው ጊዜ፣ በአስከፊው ባርነታቸው ተስፋ ከመቊረጣቸው የተነሣ አላደመጡትም፡፡
10ሙሴን እንዲህ አለው፤
11ሂድና ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን የእስራኤልን ሕዝብ ከምድሩ እንዲለቅ ንገረው፡፡
12ሙሴም እግዚአብሔርን፣ «ተብታባ በመሆኔ እስራኤላውያን ካልሰሙኝ፣ ፈርዖን እንዴት ይሰማኛል?
13እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን አናገራቸው፡፡ እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር እንዲያስወጡ ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖንና ስለ እስራኤላውያንም ትእዛዝ ሰጣቸው፡፡
14የአባቶቻቸውም ቤት አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ የእስራኤል በኵር ልጅ የሮቤል ልጆች ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮንና ከርሚ ነበሩ፡፡ እነዚህ የሮቤል ነገድ ናቸው፡፡
15የስምዖን ልጆች ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ዱሐርና የከነዓናዊቷ ሴት ልጅ ሳኡል ነበሩ፡፡ እነዚህ የስምዖን ነገድ አባቶች ናቸው፡፡
16የሌዊ ልጆች ስሞች ከትውልዶቻቸው ጋር እነዚህ ናቸው፤ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ነበሩ፡፡ ሌዊ መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፡፡
17የጌድሶን ልጆች ሉቤኒና ሰሜኢ ነበሩ፡፡
18የቀዓት ልጆች እንበረም፣ ይሰዓር፣ ኬብሮንና ዑዝኤል ነበሩ፡፡ ቀዓት መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ኖረ፡፡
19የሜራሪ ልጆች ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ፡፡ እነዚህ በትውልዶቻቸው መሠረት፣ የሌዋውያን የነገድ አባቶች ሆኑ፡፡
20የአባቱን እኅት ዮካብድን አገባ፤ እርሷምአሮንንና ሙሴን ወለደችለት፡፡ እንበረም መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖሮ ሞተ፡፡
21የይስዓር ልጆች ቆሬ፣ ናፌግና ዝክሪ ነበሩ፡፡
22ልጆች ሚሳኤል፣ ኤልዳፋንና ሥትሪ ነበሩ፡፡
23የአሚካዳብን ልጅ፣ የነኦሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፡፡ እርሷም ናዳብንና አብዩድን፣ አልዓዛርንና ኢተምርን ወለደችለት፡፡
24የቆሬ ልጆች አሴር፣ ሕልቃናና አብያሳፍ ነበሩ፡፡ እነዚህ የቆሬ ነገድ አባቶች ናቸው፡፡
25ልጅ አልዓር ከፏትኤል ልጆች አንዲቱን አገባ፡፡ እርሷም ፊንሐስን ወለደችለት፡፡ እነዚህ በየትውልዶቻቸው የሌዋውያን አባቶች ቤቶች አለቆች ናቸው፡፡
26ሁለት ሰዎች፣ «እስራኤላውያንን በየተዋጊ ሰራዊታቸው ከግብፅ ምድር አውጡ» ብሎ እግዚአብሔር ያዘዛቸው አሮንና ሙሴ ነበሩ፡፡
27ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብፅ ለማውጣት እንዲፈቅድላቸው ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ተናገሩ፡፡ እነዚህ ሙሴና አሮን እነዚያው ራሳቸው ነበሩ፡፡
28እግዚአብሔር በግብፅ ውስጥ ሙሴን ባናገረው ጊዜ፣
29«እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡ የምነግርህን ሁሉ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገረው» አለው፡፡
30ግን እግዚአብሔርን፣ «እኔ ተብታባ ነኝ፤ ፈርዖን ታዲያ እንዴት ይሰማኛል? አለው፡፡