መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሙሴም መልሶ፣ «ባያምኑኝስ ወይም ባይሰሙኝ ነገር ግን በምትኩ፣ እግዚአብሔር አልተገለጠልህም» ቢሉኝስ?
2እግዚአብሔር ሙሴን፣ «በእጅህ ያለው ምንድን ነው?» አለው፡፡ ሙሴም «በትር» አለ፡፡
3እግዚአብሔር፣ «መሬት ላይ ጣለው» አለው፡፡ ሙሴም በትሩን መሬት ላይ ጣለው፤ በትሩም እባብ ሆነ፡፡ ሙሴ ከእባቡ ሸሸ፡፡
4እግዚአብሔር ሙሴን፣ «እጅህን ዘርግተህ የእባቡን ጅራት ያዝ» አለው፡፡ ሙሴም እጁን ዘረገና እባቡን ያዘው፡፡ እባቡ በእጁ ላይ እንደ ገና በትር ሆነ፡፡
5«ይህ የሆነው የአባቶቻቸው አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር የተገለጠልህ መሆኑን እነዲያምኑ ነው፡፡»
6ደግሞም እግዚአብሔር ሙሴን፣ «እጅህን በብትህ ውስጥ አግባ» አለው፡፡ እጁን ሲያወጣው እነሆ፣ እንደ በረዶ ነጽቶ ለምጽ ሆኖአል፡፡
7እግዚአብሔር፣ «እጅህን እንደ ገና በብብትህ ውስጥ አግባ» አለው፡፡ ሙሴም እጁን በብብቱ ውስጥ አገባ፣ ከብብቱ ሲወጣውም እንደ ሌላው ሰውነቱ ጤናማ ሆኖ አየው፡፡
8እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ «ባያምኑህ፣ የመጀመሪያውን የተአምር ምልክት ባይቀበሉ ወይም ባያምኑበት፣ ሁለተኛውን ያምናሉ፡፡
9እነዚህን ሁለት የተአምር ምልክቶች ባያምኑም እንኳ፣ ወይም ባይሰሙህ፣ ከወንዙ ጥቂት ውሀ ወስደህ በደረቁ መሬት ላይ አፍስሰው፡፡ ያፈሰስኸውም ውሀ በደረቁ መሬት ላይ ደም ይሆናል፡፡»
10እግዚአብሔርን፣ «ጌታ ሆይ፣ በፊትም፣ አንተ ለባሪያህ ከተናገርህ ወዲህም ርቱዕ አንደበት ያለኝ አይደለሁም፡፡ ኮልታፋና ንግግር የማልችል ሰው ነኝ» አለው፡፡
11እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ «የሰውን አንደበት የፈጠረ ማን ነው? ሰውን ዲዳ ወይም ደንቈሮ ወይም እንዲያይ ወይም እንዲታወር የሚያደርግስ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለምን?
12አሁን ሂድ፤ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ፤ ምን እንደምትናገርም አስተምርሃለሁ፡፡»
13ሙሴ ግን፣ «ጌታ ሆይ፣ እባክህ ልትልከው የምትፈልገውን ሌላ ሰው ላክ» አለ፡፡
14በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን ተቈጣው፡፡ እንዲህም አለው፤ «ሌዋዊው ወንድምህ አሮንስ? እርሱ በሚገባ መናገር እንደሚችል ዐውቃለሁ፡፡ እንዲያውም ከአንተ ጋር ለመገናኘት እየመጣ ነውና ሲያይህ በልቡ ደስ ይሰኛል፡፡
15አንተ ለእርሱ ትናገራለህ፤ የሚናገራቸውንም ቃላት በአፉ ውስጥ ታስቀምጣለህ፡፡ እኔ በአፍህና በአፉ እሆናለሁ፣ ምን እነደምታደርጉም አሳያችኋለሁ፡፡
16ለሕዝቡ ይናገርልሃል፡፡ እርሱ የአንተ አፍ ይሆናል፤ አንተም ለእርሱ እንደ እኔ፣ አምላክ ትሆነዋህ፡፡
17ይህን በትር በእጅህ ትይዛለህ፣ በእርሱም ተአምራትን ታደርጋለህ፡፡»
18ሙሴም ወደ ዐማቱ ወደ የቶር ተመልሶ ሄደ፤ «ግብፅ ውስጥ ወዳሉት ዘመዶቼ ተመልሼ እንድሄድና አሁንም ድረስ በሕይወት መኖራቸውን እንዳይ ፍቀድልኝ» አለው፡፡ ዮቶርም ሙሴን፣ «በሰላም ሂድ» አለው፡፡
19ምድያም ውስጥ እያለ እግዚአብሔር «ሂድ፣ ወደ ግብፅ ተመለሰ፤ ሊገድሉህ የሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ ሞተዋል» አለው፡፡
20መሴም ሚስቱንና ልጆቹን ይዞ፣ በአህያ ላይም አስቀምጦ ወደ ግብፅ ተመለሰ፤ የእግዚአብሔርን በትርም በእጁ ይዞ ነበር፡፡
21ሙሴን እንዲህ አለው፤ «ወደ ግብፅ ተመልሰህ ስትሄድ፣ በእጅህ ያስቀመጥኋቸውን ተአምራት ሁሉ በፈርዖን ፊት እንደምታደርግ ዐስብ፡፡ ነገር ግን እኔ ልቡን አደነድነዋለሁ፤ ሕዝቡ እንዲሄዱም አይፈቅድም፡፡
22እንዲህ ብለህ ንገረው፤ «እግዚአብሔር እየተናገረ ያለው ይህን ነው፤ እስራኤል ልጄ፣ በኵሬ ነው፤
23«እንዲያመልከኝ ልጄን ልቀቅ ብዬ እነግርሃለሁ፡፡» ነገር ግን ለመልቀቅ እምቢ ስላለህ፣ በኵር ልጅህን እገድላለሁ፡፡»
24ላይ ለምሽቱ ዐርፈው ሳለ፣ እግዚአብሔር ሙሴን አግንኝቶ ሊገድለው ነበር፡፡
25ግን ስለታም ቢላዋ ይዛ የልጇን ሸለፈት ገረዘች፤ እግሩንም አስነካችው፡፡ ከዚያም በኋላ «አንተ ለእኔ በእውነት የደም ሙሽራዬ ነህ» አለች፡፡
26እግዚአብሔር ሙሴን ተወው፡፡ «አንተ የደም ሙሽራ ነህ» ብላ የተናገረችው በግርዘቱ ምክንያት ነው፡፡
27አሮንን፣ «ወደ ምድረ በዳ ሂድና ከሙሴ ጋር ተገናኝ» አለው፡፡ አሮን ሄደ፣ ሙሴንም በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አግኝቶ ሳመው፡፡
28እንዲናገር የላከለትን የእግዚአብሔር ቃሎች ሁሉና እንዲፈጽማቸው ያዘዘውን ተአምራት በሙሉ ለአሮን ነገረው፡፡
29በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ሰበሰቡ፡፡
30እግዚአብሔር ተአምራትም በሕዝቡ ፊት አሳየ፡፡
31አመኑ፡፡ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን የጐበኛቸውና የደረሰባቸውን ጭቈና የተመለከተ መሆኑን ሲሰሙም ሰገዱ፣ አመለኩትም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።