መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሙሴ የምድያምን ካህን፣ የዐማቱን የየቶርን በጎች ጠብቅ ነበር፡፡ በጎቹን ወደ ምድረ በዳው ዳርቻ ነድቶ ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ኮሬብ ደረሰ፡፡
2በዚያም የእግዚአብሔር መልአክ በቊጥቋጦ ውስጥ በእሳት ነበልባል ተገለጠለት፡፡ ሙሴ ተመለከተ፣ እነሆም ቊጥቋጦው እየተቀጣጠለ ነበር፤ ነገር ግን ቊጥቋጦው አልተቃጠለም፡፡
3ሙሴም፣ «ልቅረብና ቊጥቋጦው ለምን እንዳልተቃጠለ ይህን አስደናቂ ነገር ልይ» አለ፡፡
4ሊመለከት እንደ ቀረበ እግዚአብሔር ሲያየው፣ ከቊጥቋጦው ውስጥ ጠራው፤ «ሙሴ፣ ሙሴ» አለውመ፡፡ ሙሴም፣ «እነሆኝ» አለ፡፡
5እግዚአብሔር፣ «አትቅረብ! የቆምህበት ምድር ለእኔ ተቀድሶአልና ጫማህን አውልቅ» አለው፡፡
6ደግሞም፣ «እኔ የአባትህ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ ነኝ» አለው፡፡ ከዚያም በኋላ ሙሴ እግዚአብሔርን ማየት ስለ ፈራ ፊቱን ሸፈነ፡፡
7እንዲህ አለ፤ «በግብፅ የሚኖሩትን የሕዝቤን ሥቃይ በእርግጥ አይቻለሁ፡፡ አሠሪ አለቆቻቸው ከሚያደርሱባቸው ጭቈና የተነሣ ጩኸታቸውን ሰምቻለሁ፤ ስለ ሥቃያቸው ዐውቃለሁና፡፡
8ከግብፃውያን አገዛዝ ነጻ ላወጣቸውና ከዚያም ጋር አውጥቼ ማርና ወተት ወደምታፈሰው መልካምና ለም ወደሆነችው፤ ወደ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ አሞራውያንን፣ ፌርዛውያን፣ ኤውያውያንና ኢያቡሳውያን ምድር ላሰገባቸው ወርጃለሁ አለ፡፡
9የእስራል ሕዝብ ጩኸት ወደ እኔ ደርሶአል፡፡ ይልቁንም ግብፃውያን ያደረሱባቸውን ጭቈና አይቻለሁ፡፡
10ስለዚህ ሕዝቤን፣ እስራኤላውያንን ከግብፅ እንድታወጣ ወደ ፈርዖን እልክልሃለሁ፡፡»
11ግን፣ እግዚአብሔርን «ወደ ፈርዖን የምሄድና እስራኤላውያንን ከግብፅ የማወጣቸው እኔ ማን ነኝ?» አለው፡፡
12ሙሴን መልሶ፣ «እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፡፡ ይህ እኔ እንደ ላክሁህ ምልክት ይሆናል፡፡ ሕዝቡን ከግብፅ ስታወጣቸው፣ በዚህ ተራራ ላይ ታመልኩኛላችሁ» አለው፡፡
13ሙሴም እግዚአብሔርን፣ «ወደ እስራኤላውያን ስሄድና ‹የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል› ብዬ ስነግራቸው፣ እነርሱም፣ «ስሙ ማን ነው? ሲሉኝ ምን እነግራቸዋሉ? አለው፡፡
14እግዚአብሔርም ሙሴን፣ «እኔ ያለሁ የምኖርም ነኝ፡፡ ያለና የሚኖር ወደ እናንተ ልኮኛል ብለህ ለእስራኤላውያን ንገራቸው» አለው፡፡
15ደግሞም እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ እግዚአብሔር የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል፡፡ ስሜ ለዘለዓለም ይህ ነው፤ ለትውልዶች ሁሉ የታስበውም በዚህ ነው ብለህ ለእስራኤላውያን ንገራቸው፡፡»
16ሂድና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሰብስብ፤ እንዲህም ብለህ ንገራቸው፤ የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ለእኔ ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ፣ «ጐብኝቻችኋለሁ፤ በግብፅ ውስጥ የደረሰባችሁንም አይቻለሁ፡፡
17በግብፅ ከደረሰባችሁ ጭቈና ነጻ ላወጣችሁና ማርና ወተት ወደምታፈሰው ወደ ከነዓናውያን፣ ወደ ኬጢያውያን፣ ወደ አሞራውያን፣ ወደ ፌርዛውያን፣ ወደኤዊያውያንና ወደ ኢያቡሳውያን ምድር ላገባችሁ ቃል ገብቻለሁ፡፡»
18ሽማግሌዎቹም ይሰሙሃል፡፡ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ግብፅ ንጉሥ ሂዱና፣ የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ተገለጠልን፡፡ ስለዚህም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሠዋት እንድንችል በምድረ በዳው ውስጥ የሦስት ቀን ጕዞ እንሂድ በሉት፡፡
19ነገር ግን የግብፅ ንጉሥ እጁ ካልተገደደ በቀር ለመሄድ እንደማይፈቅድላችሁ ዐውቃለሁ፡፡
20በመካከላቸው በማድረጋቸው ተአምራት ሁሉ ግብፃውያንን እመታቸዋለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ፣ እንድትሄዱ ይፈቅድላችኋል፡፡
21ሕዝብ ከግብፃውያን ዘንድ መወደድን እንዲያገኝ አደርጋለሁ፣ ስለዚህ ስትወጡ፣ ባዶ እጃችሁን አትወጡም፡፡
22ሴት ከግብፃውያት ጎረቤቶቿና በጎረቤቶቿ ቤቶች ውስጥ ከምትኖር ማንኛውም ሴት የብርና የወርቅ ጌጣጌጦች፣ ልብስም እንዲሰጣት ትጠይቃለች፡፡ እነርሱንም በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጓቸዋላችሁ፡፡ ግብፃውያንን በዚህ መንገድ ትበዘብዟቸዋላችሁ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።