መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 39

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በመቅደሱ ውስጥ ለሚከናወነው አገልግሎት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ የተሠሩ ልብሶችን አበጁ። እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለቤተ መቅደሱ የሚሆኑ የአሮንን ልብሶች ሠሩ።
2ኤፉዱን ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ሠራ።
3ሠራተኛ እንደሚሠራው፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በአማረ በፍታ ለመ|ሥራት ወርቁን ቀጥቅጠው ወደ ሽቦነት ቆራረጡት።
4የትከሻ ንጣዮችን ሠርተው ከላይኛዎቹ ጠርዞቹ ጋር አያያዙት።
5በብልኀት የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያም እንደ ኤፉዱ ሲሆን፣ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው፣ አምሮ ከተፈተለ በፍታ ይኸውም ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ከኤፉድ ጋር ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ።
6የመረግድ ድንጋዮችን በወርቅ ፈርጥ ክፈፍ አበጁላቸው፤ እንደ ማኅተምም የዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ልጆች ስሞች ቀረጹባቸው።
7እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት፣ ባስልኤል በሴፉዱ የትከሻ ንጣዮች ላይ ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች አድርጎ አስቀመጣቸው።
8ኪሱንም ብልኅ ሠራተኛ እንደሚሠራው፣ እንደ ኤፉዱ አበጀው። ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከአማረ በፍታ ሠራው።
9ኪሱ አራት ማእዘን ነበረ። ርዝመቱም ወርዱም አንድ ስንዝር ሆኖ የተደረበ ዕጥፍ ነበረ።
10በውስጡም አራት የዕንቍ ድንጋዮች ፈድፎች አበጅተዋል። በመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፣ ቶጳዝዮንና አብራቅራቂ ዕንቍ ነበሩት።
11ረድፍ በሉር፣ ሰንፔር፣ አልማዝ፤
12በሦስተኛው ረድፍ ያክንት፣ ኬልቄዶን፣ አሜቴስጢኖስ፤
13በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያስጲድ ነበሩ። ድንጋዮቹ በወርቅ ፈርጥ ዙሪያቸውን የተከፈፉ ነበር።
14እያንዳንዳቸው በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ስሞች ቅደም ተከተል መሠረት የተቀመጡ ነበር። እያንዳንዱ ስም ከዐሥራ ሁለቱ ነገዶች አንዱን በመወከል በማተሚያ ቀለበት ላይ እንደሚቀረጽ የተቀረጸባቸው ነበሩ።
15ኪሱ ላይ ከንጹሕ ወርቅ እንደ ገመድ የተጎነጎኑ ድሪዎችን አበጁ።
16ሁለት የወርቅ ፈርጦችንና ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ሁለቱን ቀለበቶች ከደረት ኪሱ ሁለት ጠርዞች ጋር አያያዟቸው።
17ሁለቱን የተጎነጎኑ የወርቅ ድሪዎች በደረት ኪሱ ጠርዞች ሁለት ቀለበቶች ውስጥ አስቀመጧቸው።
18ሌሎች ሁለት ጫፎች ከሁለት ፈርጦች ጋር አያያዟቸው። ከኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ጋር በኤፉዱ ፊት አገናኗቸው።
19የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ከውስጠኛው ጠርዝ ቀጥሎ በሚገኘው ጎን በደረት ኪሱ ሌሎች ሁለት ጠርዞች ላይ አስቀመጧቸው።
20ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው፣ በመያዣው አጠገብ በብልኀት ከተሠራው የወገብ መታጠቂያ በላይ፣ ከአፉዱ ፊት ሁለት የትከሻ ንጣዮች ግርጌ ጋር አያያዟቸው።
21በብልኀት ከተሠራው ከኤፉዱ የወገብ መታጠቂያ በላይ መያያዝ እንዲችል፣ የደረት ኪሱን በራሱ ቀለበቶች ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ፈትል አሰሩት። ይህ የሆነው የደረት ኪሱ ከኤፉዱ የተነጠለ እንዳይሆን ነው። የተደረገውም እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት በነበረው መሠረት ነው።
22የኤፉዱን ቀሚስ ሙሉ በሙሉ የሸማኔ ሥራ ከሆነው ከሐምራዊ ጨርቅ ሠራው።
23መካከሉ ላይ ዐንገት ማስገቢያ ነበረው። እንዳይቀደድም ዙሪያውን የተዘመዘመ ጠርዝ ነበረው።
24በታችኛው የቀሚሱ ዘርፍ ላይም የሰማያዊ፣ የሐምራዊ፣ የቀይ ማግና የአማረ በፍታ ሮማኖችን አበጁ።
25ሻኵራዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠርተው በታችኛው የቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ ላይ በሮማኖቹም መካከል፣
26አገልግሎት በቀሚሱ ጠርዝ ላይ ሻኵራን ሮማን፣ ሻኵራና ሮማን እያደረጉ አስቀመጧቸው። ይህም የሆነው እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት በነበረው መሠረት ነው።
27ለአሮንና ለልጆቹ ሸሚዞችን ከአማረ በፍታ ሠሩ።
28የራስ መጠምጠሚያዎችን፣ ቆቦችንና ሱሪዎችን ከአማረ በፍታ፣
29መታጠቂያዎችንም ከአማረ በፍታ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ጥልፍ ጠላፊ እንደሚሠራው አድርገው አበጇቸው። ይህም የሆነው እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት በነበረው መሠረት ነው።
30አክሊል ሠሌዳ ከንጹሕ ወርቅ ሠርተው በቀለበት ላይ ማኅተም እንደሚቀረጽ በላዩ ቅዱስ ለእግዚአብሔርን ቀረጹበት።
31እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት እንደ ነበረው፣ በመጠምጠሚያው ዐናት ላይ ለማንጠልጠል ሰማያዊ ፈትል አሰሩበት።
32ድንኳን፣ የማደሪያው ሥራ ተጠናቀቀ። የእስራኤል ሰዎች እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጣቸውን መመሪያዎች በመከተል ሁሉንም አደረጉ።
33ድንኳኑንና ዕቃዎቹን ሁሉ፣ ካስማዎቹን፣ ወጋግራዎቹን፣ አግዳሚዎቹን፣ ምሰሶዎቹንና መቆሚያዎቹን፣
34በቀይ ቀለም የተነከረውን የአውራ በግ ቆዳ መሸፈኛ፣ የአስቆጣ ቆዳዊን መሸፈኛና የሚሸፍነውን መጋረጃ፣
35የምስክሩን ታቦት፣ መሎጊያዎቹንና የስርየት መክደኛውን ወደ ሙሴ አመጡ።
36ጠረጴዛውን፣ የጠረጴዛውን ዕቃዎች ሁሉና የገጽ ኅብስቱን፤
37የንጹሑን ወርቅ መቅረዝና የረድፍ መብራቶችን ከዐባሪ ዕቃዎቹና ከመብራቶቹ ዘይት ጋር፤
38መሥዐዊያውን፣ መቅቢያ ዘይቱንና ጣፋጭ መዐዛ ያለን ዕጣን፣ የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ መጋረጃ፤
39የነሐስ መሠዊያውን ከነሐስ ፍርግርጉና ከመሎጊያዎቹ፣ ከዕቃዎቹ፣ ከትልቁ የመታጠቢያ ሳሕንና ከመቆሚያው ጋር አመጡ።
40የአደባባዩን መጋረጃዎች ከምሰሶዎቹና ከመቆሚያዎቹ ጋር፣ የአደባባዩን መግቢያ መጋረጃም፣ ገመዶቹንና የድንኳን ካስማዎችን፣ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውለውን ዕቃ ሁሉ አመጡ።
41አገልግሎት በጥበብ የተሠሩትን ልብሶች፣ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ የካህኑን የአሮንንና የልጆቹን የተቀደሱ ልብሶችም አመጡ።
42ስለዚህም የእስራኤል ሰዎች እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሥራውን በሙሉ አከናወኑ።
43ሙሴ ሥራውን ሁሉ ሲፈትሽ፣ እነሆ ሁሉን አከናውነውታል። ያከናወኑትም እግዚአብሔር አዝዞት በነበረው በዚያው መንገድ ነው። ሙሴም ሕዝቡን ባረካቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።