1የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሠራ። ዐምስት ክንድ እርዝመትና ዐምስት ክንድ ስፋት፣ አራት ማእዘንና ሦስት ክንድ ቁመት ነበረው።
2ማእዘኖችም የበሬ ቀንዶችን የሚመስሉ ቅርጾችን በመሥራት አስረዘማቸው። ቀንዶቹ ከመሠዊያው ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፤ መሠዊያውንም በነሐስ ለበጠው።
3ለመሠዊያው የሚያስፈልገውን ዕቃ ሁሉ፦ ለዐመድ ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ጎድጓዳ ሳሕኖችን፣ ሜንጦዎችንና ማንደጃዎችን በሙሉ ከነሐስ ሠራ።
4ከደረጃው ሥር ከመሠዊያው እኩሌታ እስከ ታች የሚደርስ እንደ መረብ የተሠራ የነሐስ ፍርግርግ ለመሠዊያው አበጀ።
5ፍርግርግ አራት ማእዘኖች ለመሎጊያዎቹ መያዣ አራት ቀለበቶችን ሠራላቸው።
6ዕንጨት መሎጊያዎችን ሠርቶ በነሐስ ለበጣቸው።
7መሎጊያዎቹን መሠዊያውን ለመሸከም በመሠዊያው ጎኖች ላይ ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው። መሠዊያውን ክፍት አድርጎ በሳንቃዎች ሠራው።
8ባስልኤል ትልቁን የመታጠቢያ ሳሕን ከነሐስ መቆሚያ ጋር ሠራ። ሳሕኑን የሠራውም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ የሚያገለግሉት ሴቶች ይጠቀሙባቸው ከነበሩ መስተዋቶች ነው።
9ሠራው። በአደባባዩ ደቡብ ጎን ላይ የነበሩት መጋረጃዎች ከአማረ በፍታ የተሠሩና አንድ መቶ ክንድ እርዝመት ያላቸው ነበሩ።
10መጋረጃዎቹ ሃያ ምሰሶዎችና ሃያ መቆሚያዎች ነበሯቸው። ከምሰሶዎቹና ከብር ዘንጎቹ ጋር የተያያዙ ኵላቦችም ነበሩ።
11ጎን በኩልም እንደዚሁ አንድ መቶ ክንድ እርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ከሃያ ምሰሶዎችና ከሃያ የነሐስ መቆሚያዎች፣ ከምሰሶዎቹ ጋር ከተያያዙ ኲላቦችና ከብር ዘንጎች ጋር ነበር።
12የምዕራቡ ጎን መጋረጃዎች ዐምሳ ክንድ የሚረዝሙ፣ ዐሥር ምሰስዎችና መቆሚያዎች ያሏቸው ነበሩ። የምሰሶዎቹ ኵላቦችና ዘንጎች ብር ነበሩ።
13አደባባዩም በምሥራቁ ጎን ላይ ዐምሳ ክንድ ይረዝም ነበር።
14የመግቢያው አንድ ጎን መጋረጃዎች እርዝመት ዐሥራ ዐምስት ክንድ ነበረ። ሦስት ምሰሶዎች ከሦስት መቆሚያዎች ጋር ነበሯቸው።
15በአደባባዩ መግቢያ ሌላ ጎን ላይም ዐሥራ ዐምስት ክንድ የሚረዝሙና ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው መጋረጃዎች ነበሩ።
16በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት መጋረጃዎች ሁሉ አምሮ ከተፈተለ በፍታ የተሠሩ ነበሩ።
17የምሰሶዎቹ መቆሚያዎች ከነሐስ፣ የምሰሶዎቹ ኵላቦችና ዘንጎቻቸው፣ የዐናታቸውም መሸፈኛ ከብር የተሠሩ ነበሩ። የአደባባዩ ምሰሶዎች ሁሉ በብር የተለበጡ ነበር።
18የአደባባዩ በር መጋረጃቅ እርዝመት ሃያ ክንድ ነበረ። ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ የተሠራ ነበረ። እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች ሃያ ክንድ እርዝመትና ዐምስት ክንድ ቁመት ነበረው።
19የነሐስ መቆሚያዎችና የብር ኵላቦች ነበሩት። የዐናታቸው መሸፈኛና ዘንጎቹ ከብር የተሠሩ ነበሩ።
20የመገናኛው ድንኳን ካስማዎች ሁሉ የተሠሩት ከነሐስ ነበር።
21የሙሴን ትእዛዝ በመከተል በተመዘገበው መሠረት የመገናኛው ድንኳን፣ ይኸውም የምስክሩ ድንኳኝ ቆጠራ ይህ ነው። በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታማር መሪነት ይህ የሌዋውያኑ ሥራ ነበረ።
22ከይሁዳ ነገድ የሆነው፣ የሖር የልጅ ልጅ፣ የኡሪ ልጅ ባስልኤል እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ትእዛዝ ሁሉ ፈጸመ።
23ከባስልኤልም ጋር ከዳን ነገድ የሆነው የአሂሳሚክ ልጅ ኤልያብ ቅርጽ አውጪ ሠራተኛ፣ የእጅ ጥበብ ሙያተኛ፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ግምጃና በአማረ በፍታ ጥልፍ ጠላፊም ሆኖ ዐብሮት ሠራ።
24ከመቅደሱ ሥራ ጋር ለተያያዘው ተግባር ሁሉ ጥቅም ላይ የዋለው ወርቅ ማለትም፣ ከስጦታው የተገኘው ወርቅ ሁሉ በመቅደሱ ሰቅል መጠን መሠረት ሃያ ዘጠኝ መክሊትና ሰባት መቶ ሠላሳ ሰቅል ነበረ።
25ማኅበረ ሰቡ የሰጠው ብር በመቅደሱ ሰቅል መጠን ተመዝኖ አንድ መቶ መክሊትና አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሰባ ዐምስት ሰቅል፣
26በአንድ ሰው አንድ ቤካ ይኸውም በመቅደሱ ሰቅል መጠን ግማሽ ሰቅል ነበረ። ይህ ቍጥር የተደረሰበት በሕዝብ ቆጠራው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆናቸው ተቆጥረው በተገኘው ስድስት መቶ ሦስት ሺሕ ዐምስት መቶ ዐምሳ ወንዶች ቍጥር በያንዳንዱ ሰው ተሰልቶ ነው።
27የመቅደሱንና የመጋረጃዎችን መቆሚያዎች ለመሥራት አንድ መቶ የብር መክሊት ወጪ ሆኖአል፦ መቆሚያዎቹ በጠቅላላ አንድ መቶ ሆነው፣ ለያንዳንዱ መቆሚያ አንድ መክሊት ተከፍሎአል ማለት ነው።
28በቀሩት አንድ ሺሕ ሰባቶ መቶ ሰባ ዐምስት የብር ሰቅሎች ባስልኤል የምሰሶዎቹን ኵላቦች ሠርቶ ዐናታቸውን ሸፈነባቸው፤ ዘንጎችንም ለምሰሶዎቹ ሠራባቸው።
29ከስጦታ የተገኘው ነሐስ ተመዝኖ ሰባ ታለንትና ሁለት ሺሕ አራት መቶ ሰቅል ሆነ።
30በዚህም የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ መቆሚያዎች፣ የነሐስ መሠዊያውን፣ የእርሱንም የነሐስ ፍርግርግ፣ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ፣
31የአደባባዩን መቆሚያዎች፣ የአደባባዩን መግቢያ መቆሚያዎች፣ የመገናኛውን ድንኳንና የአደባባዩን ድንኳን ካስሞች ሁሉ ሠራበት።