መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 37

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ባስልኤል እርዝመቱ ሁለት ተኩል ክንድ፣ ወርዱ አንድ ተኩል ክንድ፣ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦታ ከግራር ዕንጨት ሠራ።
2ውስጡንና ውጩንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት።
3ለአራት እግሮቹም አራት የወርቅ ቀለበቶችን፣ በአንዱ ጎኑ ላይ ሁለት ቀለበቶችን፣ በሌላውም ጎኑ ላይ ሁለት ቀለበቶችን ጨምሮ ሠራ።
4ዕንጨት መሎጊያዎችን ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።
5ታቦቱን ለመሸከም በታቦቱ ጎኖች ላይ ባሉት ቀለበቶች ውስጥ መሎጊያዎቹን አስገባቸው።
6ሁለት ተኩል ክንድ፣ ወርዱም አንድ ተኩል ክንድ የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።
7ባስልኤል ለስርየት መክደኛው ሁለት ጫፎች ሁለት ኪሩቤልን ከተቀጠቀጠ ወርቅ አበጀ።
8አንዱ ኪሩብ ለአንዱ የስርየት መክደኛ፣ ሌላውም ለሌላው የስርየት መክደኛ ጫፍ ነበረ። ኪሩቤል ከስርየት መክደኛው ጋር ወጥ ሆነው ተበጅተው ነበር።
9ኪሩቤል ክንፎቻቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት የስርየት መክደኛውን በድንፎቻቸው ጋረዱት። እርስ በርስ ትይዩ ሆነውም ወደ ስርየት መክደኛው መካከል ይመለከቱ ነበር።
10ባስልኤል እርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ቁመቱም አንድ ተኩል ክንድ የሆነ ጠረጴዛ ከግራር ዕንጨት ሠራ።
11ወርቅ ለበጠው፤ ዙሪያውንም በንጹሕ ወርቅ ከፈፈው።
12አንድ ስንዝር ጠርዝ ከወርቅ ክፈፍ ጋር አበጀለት።
13የወርቅ ቀለበቶችንም ሠርቶ የጠረጴዛው እግሮች ካሉበት ማእዘኖች ጋር አያያዛቸው።
14ለመሸከም መሎጊያዎችን ማስገባት እንዲቻል ቀለበቶቹ ከጠርዙ ጋር ተያይዘው ነበር።
15ጠረጴዛውን መሸከም እንዲቻል መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።
16በጠረጴዛው ላይ የሚቀመጡ ዕቃዎችን፦ ድስቶችን፣ ዝርግና ጎድጓዳ ሳሕኖችን ጭልፋዎችን፣ ወጭቶችንና የመጠጥ መሥዋዕቱን ማፍሰሻ ማንቆርቆሪያዎች ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።
17ከነማቆሚያውና ከነዘንጉ ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ ሠራ። ጽዋዎቹ፣ ቀንበጦቹና አበባዎቹ በሙሉ ከመቅረዙ ጋር ወጥ ሆነው ነበር የተሠሩት።
18ቅርንጫፎች በመቅረዙ አንድ ጎን፣ ሦስት ቅርንጫፎች ደግሞ በሌላው የመቅረዙ ጎን ተሠርተው ስድስት ቅርንጫፎች ነበር።
19ቅርንጫፍ ከቀንበጥና ክአበባ ጋር የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች ነበሩት፤ በሌላውም ቅርንጫፍ እንደዚሁ የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች ከቀንበጥና ከአበባ ጋር ነበር። ከመቅረዙ ለሚወጡ ስድስት ቅርንጫፎች ሁሉ የተደረገው አንድ ዐይነት ነበር።
20በመቅረዙ መካከል ላይ ባለው ዘንግ ላይ የለውዝ አበቦችን የሚመስሉ እራት ጽዋዎች ከቀንበጦቻቸውና ከአበቦቻቸው ጋር ተሠርተዋል።
21በመጀመሪያ የቅርንጫፎች ጥንድ ሥር ወጥ ሆኖ ዐብሮት የተሠሩ ቀንበጦች ነበር። ከመቅረዙ በሚወጡ ስድስት ቅርንጫፎች ሁሉ የተደረገው አንድ ዐይነት ነበር።
22ቅርንጫፎቻቸው ከመቅረዙ ጋር ወጥ ሆነው ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበር።
23መቅረዙንና ሰባቱን መብራቶች፣ መኮስተሪያዎቹንና የኵስታሪ ማስቀመጫዎቻቸውን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።
24መቅረዙንና ዐባሪ ዕቃዎቹን ከአንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ሠራቸው።
25እርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ የሆነውን የዕጣኑን መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሠራ። አራት ማእዘንና ቁመቱም ሁለት ክንድ ነበር። ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበር።
26የዕጣኑን መሠዊያ፦ ዐናቱን፣ ጎኖቹንና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለበጣቸው። ለዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት።
27በሁለቱ ተነጻጻሪ ጎኖቹ ላይ ከክፈፉ ሥር እንዲያያይዙት ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠራ። ቀለበቶቹ መሠዊያውን ለመሸከም መሎጊያዎችን ለመያዝ የሚያገለግሉ ናቸው።
28ከግራር ዕንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።
29የተቀሰውን የመቅቢያ ዘይትና የሽቶ ቀማሚ ሥራ የሆነውን፣ ንጹሕና ጣፋጭ መዐዛ ያለውን ዕጣን ሠራ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።