መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 36

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ስለዚህ ባስልኤልና ኤልያብ፣ የልብ ጥበበኞች የነበሩና እንዲፈጽሙት እግዚአብሔር ያዘዘውን በመከተል መቅደሱ እንዴት እንደሚሠራ ለማወቅ ብልኀትንና ማስተዋልን ያስቀመጠባቸውም ሁሉ ይሠራሉ።
2ባስልኤልንና ኤልያብን፣ እግዚአብሔር በልቡ ብልኀትን አስቀምጦበት የነበረ ጥበበኛ ስውን ሁሉ፣ መጥቶ ሥራውን ለመሥራት ልቡ ያነሣሣውንም ጠራ።
3የጠራቸውም ለመቅደሱ ሥራ እስራኤላውያን አምጥተውት የነበረውን ስጦታ ሁሉ ከሙሴ ተቀበሉ። ሕዝቡ የነጻ ፈቃድ ስጦታዎችን ጠዋት ጠዋት ወደ ሙሴ ማምጣት አላቋረጡም ነበር።
4ስለዚህ በመቅደሱ ሥራ ላይ የተሰማሩ ብልኀተኛ ሰዎች ሁሉ ከሚሠሩት ሥራ ተነሥተው መጡ።
5ሙሴን፣ “እግዚአብሔር እንድንሠራው ላዘዘን ሥራ ከሚበቃው በጣም የሚበልጥ ሕዝቡ እያመጡ ነው” አሉት።
6ሙሴም በሰፈሩ ውስጥ ያለ ማንም ሰው ለመቅደሱ ሥራ ሌላ ስጦታ እንዳያመጣ ትእዛዝ ሰጠ። ከዚያም በኋላ ሕዝቡ ስጦታ ማምጣቱን አቆሙ።
7ለሥራው ሁሉ ከሚበቃው በላይ ቍሳቍሶች ነበሯቸው።
8ያሉ ጥበበኞችም ሁሉ ከአማረ በፍታና ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግም ከተሠሩትና ኪሩቤልም ከተጠለፉባቸው ዕሥር መጋረጃዎች ጋር የመገናኛውን ድንኳን ሠሩት። ይህም እጅግ ጥበበኛ የነበረው የባስልኤል ሥራ ነው።
9መጋረጃ እርዝመት ሃያ ስምንት ክንድ፣ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ። ሁሉም መጋረጃዎች እኩል መጠን ነበራቸው።
10ባስልኤል ዐምስት ዐምስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ አድርጎ እርስ በርስ አገጣጠማቸው።
11መጋረጃዎች የመጨረሻ የውጭ ጠርዝ ላይና በሁለተኛውም ተገጣጣሚ መጋረጃ የመጨረሻ የውጭ ጠርዝ ላይ ሰማያዊ ቀለበቶችን አደረገ።
12በሁለተኛው መጋረጃ ጠርዞች ዐምሳ ዐምሳ ቀለበቶችን አበጀ። ስለሆነም ቀለበቶቹ እርስ በርስ ትይዩ ሆነው የተደረጉ ነበር።
13ባስልኤል ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዎችን ሠርቶ የመገናኛው ድንኳን ወጥ እንዲሆን መጋረጃዎቹን አያያዛቸው።
14ባስልኤል በማደሪያው ላይ ላለው ድንኳን ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎችን ሠራ።
15የእያንዳንዱ መጋረጃ እርዝመት ሠላሳ ክንድ፣ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ። ዐሥራ አንድ መጋረጃዎች እያንዳንዳቸው እኩል መጠን ነበራቸው።
16መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው፣ ስድስቱንም መጋረጃዎች እንደዚሁ እርስ በርሳቸው አያያዛቸው።
17ተገጣጣሚ መጋረጃዎች የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን በሁለተኛዎቹ ተገጣጣሚ መጋረጃዎች የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይም እንደዚሁ ዐምሳ ቀለበቶችን አበጀ።
18ባስልኤል ወጥ እንዲሆን ድንኳኑን ለማገጣጠም ዐምሳ የነሐስ ማያያዣዎችን ሠራ።
19ለድንኳኑ መሸፈኛ በቀይ ቅለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ ከበላዩም የሚህን የአቆስጣ ቆዳ ሠራ።
20ባስልኤል ከግራር ዕንጨት ወጋግራዎችን ለመገናኛው ድንኳን ሠራ።
21ወጋግራ እርዝመት ዐሥር ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ነበር።
22እርስ በርስ ለማያያዝ በያንዳንዱ ወጋግራ ሁለት ማያያዣዎች ነበር። የመገናኛውን ድንኳን ወጋግራዎች ሁሉ በዚህ መንገድ ሠራ።
23ባስልኤል በዚህ መንገድ ወጋግራዎችን ለመገናኛው ድንኳን ሠራ። ለደቡቡ ጎንም ሃያ ወጋግራዎችን አበጀ።
24ባስልኤል ከሃያዎቹ ወጋግራዎች ሥር የሚሆኑ አራ የብር መቆሚያዎችን አበጀ። ማያያዣዎች ለመሆን ከመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች ከያንዳንዱ ሌላ ወጋግራ በታችም እንደዚሁ ሁለት መቆሚያዎች ነበሩ።
25ጎን ላለው ለመገናኛው ድንኳን ሁለተኛ ጎን ሃያ ወጋግራዎችንና
26የብር መቆሚያዎቻቸውን አበጀ። በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለው ወጋግራ ሥርም እንዲሁ ሁለት ሁለት መቆሚያ አበጅቶአል።
27በስተ ምዕራብ ላለው ለመገናኛው ድንኳን ጀርባ ባስልኤል ስድስት ወጋግራዎችን ሠራ።
28ድንኳን የኋላ ማእዘኖች ሁለት ወጋግራዎችን አበጀ።
29እነዚህ ወጋግራዎች ከታች የተነጣጠሉ፣ ከላይ ደግሞ በአንድ ቀለበት የየያያዙ ነበር። ለሁለቱም የኋላ ማእዘኖች የተደረገው በዚህ መንገድ ነበር።
30ከብር መቆሚያዎቻቸው ጋር ስምንት ወጋግራዎች ነበሩ። በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለውም ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች ለያንዳንዱ ወጋግራ ሁለት ሁለት በመሆን ዐሥራ ስድስት መቆሚያዎች ነበሩ።
31ባስልኤል የግራር ዕንጨት አግዳሚዎችን አበጀ፦ ለመገናኛው ድንኳን አንድ ጎን ወጋግራዎች ዐምስት፣ አግዳሚዎችን፣
32የመገናኛው ድንኳን ጎን ወጋግራዎች አምስት አግዳሚዎችን፣ በምዕራብ በኩል ላለው ለመገናኛው ድንኳን የኋላ ጎን ወጋግራዎችም ዐምስት አግዳሚዎችን ሠራ።
33አግዳሚዎቹን የሥራቸውም በወጋግራዎች መካከል ላይ ከዳር እስከ ዳር እንዲደርሱ አድርጎ ነው።
34ወጋግራዎቹን በወርቅ ለበጣቸው። አግዳሚዎችን ለማያያዝ የወርቅ ቀለበቶችን ሠራ፣ አግዳሚዎችንም በወርቅ ለበጣቸው።
35በብልኀተኛ ሠራተኛ ሥራ ኪሩቤል የተጠለፉበትን መጋረጃ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ ካማረ በፍታም ሠራው።
36አራት የግራር ዕንጨት ምሰሶዎችን አበጅቶ በውርቅ ለበጣቸው። ለምሰሶዎችም የወርቅ ኵላቦችን ሠርቶ አራት የብር መቆሚያዎችን አደረገላቸው።
37ለድንኳኑ መግቢያ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ ካማረ በፍታም በጥልፍ ጠላፊ ሥራ የተዘጋጀ መጋረጃ አበጀለት።
38የመጋረጃውን ዐምስት ምሰሶዎች ከኵላቦች ጋር ሠራ። የምሰሶዎችን ዐናትና ዘንግ በወርቅ ለበጣቸው። ዐምስት መቆሚያዎቻቸውም ከነሐስ የተሰሩ ነበሩ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።