መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 35

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእስራኤልን ማኅበረ ሰብ ሁሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፤ “እንድትፈጽሟቸው እግዚአብሔር የሰጣችሁ ትእዛዝት እነዚህ ናቸው።
2ስድስት ቀን ሥራ ትሠራላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የፍጹም ዕረፍት የሰንበት ቀን ይሁንላችሁ። በዚያ ቀን ሥራ የሚሥዐራ ሁሉ ይሞታል።
3በሰንበት ቀን በማንኛችሁም ቤት ውስጥ እሳት አይንደድ።”
4ሁሉን የእስራኤል ማኅበረ ሰብ እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው።
5ከልብ ፈቃደኛ የሆናችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቅርቡ። ሁሉም ለእግዚአብሔር የወርቅ፣ የብር፣ የነሐስ መባያምጣ፤
6ሐምራዊና ቀይ ማግ፣ ቀጭን በፍታ፣ የፍየል ጠጒር፣
7በቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና የአቆስጣ ቆዳ፣ የግራር ዕንጨት፣
8መብራቶች ዘይት፣ ለመቅቢያ ዘይቱ ቅመምና ጣፋጭ መዐዛ ያለው ዕጣን፣
9መረግዶችና ለኤፉዱና ለደረት ኪሱ የሚሆኑ ሌሎች ዕንጨቶችንም መባ አድርጎ ያቅርብ።
10በመካከላችሁ ያሉ ብልኀተኛ ሰዎች ሁሉ ይምጡና እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ይሥሩ፦
11ከድንኳኑ ጋር፣ መደሪያውን፣ ማያያዣዎቹን፣ ክፈፎቹን፣ አግዳሚዎቹን፣ ቋሚዎቹንና መሠረቶቹን፤
12ታቦቱንም ከነመሎጊያዎቹ፣ የስርየት መክደኛውንና የሚሸፍነውን መጋረጃ፤
13ከመሎጊያዎቹ ጋር፣ ዕቃዎቹንም ሁሉን ኣየገጽ ኅብስቱን፤
14የመብራቶቹን መቅረዝ ከዐባሪ ዕቃዎቹ ጋር፣ መብራቶቹንና የመብራቶቹን ዘይት፤
15የዕጣኑን መሠዊያ ከመሎጊያዎቹ ጋር፣ መቅቢያ ዘይቱንና ጣፋጭ መዓዛ ያለውን ዕጣን፣ የመገናኛ ድንኳኑን መግቢያ መጋረጃ፣
16የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን መሠዊያ ከነሐስ መጫሪያው፣ ከመሎጊያዎቹና ከዕቃዎቹ ጋር፤ ትልቁን የመታጠቢያ ሰን እስከ ማስቀመጫው፤
17የአድደባባዩን መጋረጃዎች ከምሰሶዎቹና ከመሠረቶቹ ጋር፣ የአደባባዩን መግቢይ ኣመጋረጃ፤
18የማደሪያውን ድንኳን ካስማዎች ከነገመዶቻቸው፤
19ውስጥ ለማገልገል በብልኀት የተሠሩ ልብሶችን፣ ካህናት ሆነው ለማገልገል ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹ የሚሆኑ የተቀደሱ ልብሶችን ያምጡ።”
20ከዚያም ሁሉም የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጥተው ሄዱ።
21ልቡ የተነሣሣና ፈቃደኛ የሆነ ሁሉ በመምጣት ለመገናኛው ድንኳን ሥራ፣ ለውስጡም ለሚደረገው አገልግሎትና ለተቀደሱ ልብሶች የሚሆን ስጦታን ሰጡ።
22ፈቃደኛ የነበሩ ወንዶችም ሴቶችም መጥተው የአፍንጫ ጌጦችን፣ የጆሮ ጌጦችን፣ ቀለበቶችን፣ ድሪዎችንና ሁሉንም ዓይነት የወርቅ ጌጣጌጦች አመጡ።
23ሐምራዊ፣ ቀይም ቀይ ማግ፣ ያማረ በፍታ፣ የፍየል ጠጕር፣ በቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ ወይም የአስቆጣ ቆዳ የነበራቸውም አመጡ።
24ለማንኛውም ተግባር የሚጠቅም የግራር ዕንጨት የነራቸው፣ የብርና የነሐስ ስጦታ ማድረግ የሚፈልጉ ሁሉ በስጦታነት ለእግዚአብሔር አቀረቡ።
25ብልኀተኛ ሴቶችም ሁሉ ማግ ፈትለው፣ የፈተሉትን ሰማያዊ፣ ሕዐምራዊ፣ ወይም ቀይ ማግ አመጡ።
26ያነሣሣቸውና ብልኀተኛ የሆኑ ሴቶች ሁሉ የፍየል ጠጕር ፈተሉ።
27ለአፉዱና ለደረት ኪሱ የሚሆኑ መረግዶችንና ሌሎች ዕንቆችን አመጡ፤
28ለመቅቢያው ዘይትና ጣፋጭ መዐዛ ላለው ዕጣን ዘይትና ቅመምም አመጡ።
29የነጻ ፈቃድ ስጦታ ለእግዚአብሔር በሙሴ በኩል እንዲፈጸም አዝዞት ለነበረው ሥራ ሁሉ ቍሳቍሶችን አመጡ።
30እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፣ እግዚአብሔር የሖር የልጅ ልጅ የሆነውን የኡሪን ልጅ ባስልኤልን ከይሁዳ ነገድ በስም ጠርቶታል።
31ለሁሉም ዐይነት የጥበብ ሥራ ጥበብን፣ ማስተዋልንና ዕውቀትን ሊሰጠው ባስልኤልን በመንፈሱ ሞልቶታል፤
32የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ጥበባዊ ሥራዎችን ለመሥራት፣
33የጥበባዊ ሥራ ዐይነቶችን ሁሉ ለመሥራት ድንጋዮችን እንዲጠርብና ዕንጨትም እንዲቀርጽ ነው።
34እግዚአብሔር በባስልኤልና ከዳን ነገድ በሆነው በአሂሳሚክ ልጅ በኤልያብ ልብ ይህን ችሎታ አስቀመጠ።
35ጥበበኛ ሰዎች፣ እንደ ቀራጺዎች፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ማግ፣ ባማረ በፍታም እንደ ጥልፍ ጠላፊዎችና እንደ ሸመና ሠራተኞች እንዲሠሩም ብልኀትን ሞላባቸው። እነርሱ በሥራ ዐይነቶች ሁሉ ጥበበኞች የሆኑ የጥበብ ባለሙያዎች ናቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።