መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 34

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ሁለት የድንጋይ ጽላትን እንደ መጀመሪያዎቹ ጽላት አድርገህ ጥረብ። በሰበርሃቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላት ላይ ተጽፈው የነበሩ ቃሎችን በእነዚህ ጽላት ላይ እጽፍባቸዋለሁ።
2ማለዳ ላይ ተዘጋጅተህ ወደ ሲና ተራራ ውጣና በዚያ በተራራው ዐናት ላይ በፊቴ ቁም።
3ከአንተ ጋር ማንም ሰው አይምጣ። በተራራው ላይ በየትኛውም ስፍራ ማንም እንዲታይ አታድርግ። የበግና የፍየል መንጋዎች፣ የቀንድ ከብቶችም እንኳ በተራራው ፊት ለፊት ሣር መጋጥ የለባቸውም።”
4ሁለት የድንጋይ ጽላትን እንድ መጀመሪያዎቹ አድርጎ ጠረበ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ሲና ተራራ ወጣ። ሙሴ ሁለቱን የድንጋይ ጽላት በእጁ ይዞ ነበር።
5እግዚአብሔር በደመና ወርዶ ከሙሴ ጋር በእዚያ ቆመ፤ ስሙን እግዚአብሔርንም ዐወጀ።
6በሙሴ ፊትም እንዲህ እያለ በማወጅ ዐለፈ፤ “እግዚአብሔር፣ ርኅሩኅም ቸርም አምላክ እግዚአብሔር፣ ለቊጣ የዘገየ፣ በጽኑዕ ፍቅርና በታማኝነት ባለ ጸጋ፣
7ጽኑዕ ፍቅሩን ለሺሕ ትውልድ የሚጠብቅ፣ ክፋትን፣ ዐመፅንና ኀጢአትን ይቅር የሚል፤ በደለኛውን ግን ከቶ ንጹሕ አያደርገውም። ለአባቶች ኀጢአት ልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውን እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ይቀጣል።”
8ሙሴ ወዲያውኑ ወደ መሬት ዝቅ ብሎ ሰገደ።
9አለ፤ “ጌታዬ ሆይ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ እባክህ ዐብረኸን ሂድ፤ ይህ ሕዝብ ግትር ሕዝብ ቢሆንም፣ ክፋታችንና ኀጢአታችንን ይቅር በለን፤ ርስትህም አድርገህ ውሰደን።”
10እንዲህ አለ፤ “እነሆ፣ ኪዳን እገባለሁ። በምድር ሁሉ አየትኛውም ሕዝብ ዘንድ ተደርገው የማያውቁ ድንቆችን በሕዝብህ ሁሉ ፊት አደርጋለሁ። በአንተ ዘንድ የማደርገው የሚያስፈራ ነውና፣ ዐብሮህ ያለው ሕዝብ ሁሉ ሥራዬን ያያል።
11የማዝዝህን ፈጽም። አሞራውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ኬጤያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኢዊያውያንንና ኢያቡሳውያንን በፊትህ አስወጣቸዋለሁ።
12አገር ኗሪዎች ጋር ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ አለዚያ በመካከልህ ወጥመድ ይሆኑብሃል።
13ሰባብሩ፤ የማምለኪያ ዐምዶቻቸውን አድቅቋቸው፤ የአሼራ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ።
14ስሜ ‘ቀናተኛ’ የሆነ እኔ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝና ሌላ አምላክ አታምልክ።
15ስለዚህም ከምድሪቱ ኗሪዎች ጋር ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም አማልክታቸውን በመከተልያመነዝራሉና፣ መሥዋዕትም ያቀርቡላቸዋልና አንተንም አንዱ ስለሚጋብዝህና ከመሥዋዕቱም ጥቂት ስለምትበላ፣
16ከዚያም ከሴቶች ልጆቹ የተወሰኑትን ለወንዶች ልጆችህ ትወስዳለህ፤ ሴት ልጆቹም አማልክታቸውን በመከተል ያመነዝራሉ፤ ወንዶች ልጆችህንም ለአማልክታቸው እንዲያመነዝሩ ያደርጓቸዋል።
17የተሠሩ አማልክትን ለራስህ አታብጅ።
18የቂጣ በዓልን አክብር። ባዘዝሁህ መሠረት እርሾ ያልገባበትን ዳቦ በተወሰነው ጊዜ በአቢብ ወር ሰባት ቀን ብላ፤ ከግብፅ የወጣሃው በአቢብ ወር ነበርና።
19በኵር ሁሉ፣ የከብትህም እንኳ ተባዕት በኵር በሙሉ፣ የበሬዎችህም የበጎችም በኵር የእኔ ነው።
20የአህያውን በኵር በጠቦት ዋጀው፤ ካልዋጀኸው ግን ዐንገቱን ስበረው። በኵር ወንድ ልጆችህን ሁሉ ዋጃቸው። ባዶ እጁን በፊቴ የሚቀርብ ማንም እይኑር።
21ቀን ሥራ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ዕረፍ። በዕርሻና በመከር ጊዜም እንኳ ዕረፍ።
22ሱባዔ በዓል ከስንዴው በኵራት ጋር፣ የመክተቻውንም በዓል በዓመቱ መጨረሻ አክብር።
23በአንተ ዘንድ ያለ ወንድ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በእኔ በእስራኤል አምላክ ፊት ይቅረብ።
24በፊትህ አስወጣቸዋለሁ፤ ወሰንህንም አሰፋዋለሁ። በዓመት ሦስት ጊዜ በእኔ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ስትወጣ፣ ምድርህን ለመውረርና ለመቆጣጠር ማንም አይመኝም።
25ደም ከእርሾ ጋር አታቅርብ፤ ወይም በፋሲካ በዓል የቀረበው መሥዋዕት ሥጋ እስከ ማለዳ ተርፎ አይቆይ።
26የዕርሻህ ምርጥ በኵራት ወደ ቤቴ አምጣ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።”
27እግዚአብሔር ሙሴን፣ “እነዚህን ቃሎች ጻፋቸው፤ በተናገርሏቸው በእነዚህ ቃሎች ክአንተና ከእስራኤል ጋር ኪዳን አድርጌአለሁና አለው።
28አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከእግዚአብሔር ጋር እዚያው ነበረ። ምግብም አልበላም፤ ውሃም አልጠጣም።
29ሁለቱን የምስክሩን ጽላት በእጁ ይዞ ከሲና ተራራ ወረደ። ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገረ ሳለ፣ ፊቱ የሚያበራ ምሆኑን አላወቀም።
30እስራኤላውያን ሙሴን ሲያዩት፣ ፊቱ ይበራ ነበር፤ ስለዚህም ወደ እርሱ ለመጠጋት ፈሩ።
31ግን ጠራቸው፤ አሮንና የሕዝቡ መሪዎችም ወደ እርሱ መቱ፣ ሙሴም ከእነርሱ ጋር ተነጋገረ።
32ከዚያ በኋላም፣ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ሙሴ መጡ፤ እርሱም በሲና ተራራ ላይ እግዚአብሔር ሰጥቶት የነበረውን ትእዛዝ ሁሉ ነገራቸው።
33ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ፣ በፊቱ ላይ መሸፈኛ አደረገ።
34ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር በፊቱ በሚቀርብበት ጊዜ ሁሉ፣ እስከሚወጣበት ጊዜ ድረስ መሸፈኛውን ያወልቀው ነበር። ሲወጣ ምን እንዲል እንደታዘዘ ለእስራኤላይዋን ይነግራቸዋል።
35እስራኤላውያን የሚያበራውን ፊቱን ሲያዩ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ተመልሶ እስኪሄድ ድረስ መሸፈኛውን እንደ ገና በፊቱ ላይ ያደርገዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።