1ሆነው እንዲያገለግሉኝ ወንድምህን ዘሮንንና ልጆቹን ናዳብን፣ አብድዩን፣ አልዓዛርንና ኢታምርን ከእስራኤል መካከል ወደ አንተ ጥራ።
2ለወንድምህ ለአሮን ለእኔ የተቀደሱ ልብሶችን አዘጋጅ። እነዚህ ልብሶች ለአሮን ክብርና ማዕርግ የሚሆኑ ናቸው።
3ካህኔ ሆኖ እንዲያገለግለኝ የአሮንን ልብሶች የሚሠሩለትን፣ በልባቸው ጥበበኛ የሆኑትን፣ የጥበብን መንፈስም የሞላሁባቸውን ሰዎች ሁሉ አነጋግር።
4የሚሠሯቸው ልብሶችም የደረት ኪስ፣ ኤፉድ፣ ቀሚስ፣ ጥልፍ የተጠለፈበት ሸሚዝ፣ መጠምጠሚያና መታጠቂያ ናቸው። ለእኔ የተቀደሱትን እነዚህን ልብሶች መሥራት አለባቸው። ልብሶቹ ካህናት ሆነው እንዲያግለግሉኝ ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናሉ።
5ወርቅ፣ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የአማረ በፍታ ይጠቀሙ።
6ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግን ኣአምሮ ከተፈተለ በፍታ ይሥሩት። ሥራው የብልኀተኛ ሙያተኝ ሥራ ሊሆን ይገባል።
7ኤፉዱ ከሁለቱ ጠርዞቹ ጋር የሚያያዙ ሁለት የትከሻ ንጣዮች ይኑሩት።
8በብልኀት የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያም እንደ ኤፉድ መሆን አለበት፦ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ወጥ ሆኖ የተሠራ ይሁን።
9ሁለት የመረግድ ድንጋዮችን ወስደህ የዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ልጆች ስሞች ቅረጽባቸው።
10ስድስቱ ስሞቻቸው በአንድ ድንጋይ፣ ስድስቱ ሌሎች ደግሞ በሌላው ድንጋይ ላይ እንደየልጁ ልደት ቀደም ተከተል ይቀረጹ።
11ሠራተኛ ማኅተም እንደሚቀርጽ የእስራኤልን ዐሥራ ሁለት ልጆች ስሞች በሁለቱ ድንጋዮች ላይ ቅረጽ። ድንጋዮቹንም በወርቅ ክፈፋቸው።
12ሁለቱን ድንጋዮች የእስራኤልን ልጆች አምላክ የሚያስታውሱ ድንጋዮች እንዲሆኑ በኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ላይ አስቀምጥ። መታሰቢያ እንዲሆኑ አሮን ስሞቻቸውን በሁለቱ ትከሻዎቹ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ይሸከማል።
13ፈርጦችንና
14እንደ ገመድ የተጎነጎኑ የንጹሕ ወርቅ ድሪዎችን አበጅተህ ከፈርጦቹ ጋር አያይዛቸው።
15ብልኅ ሠራተኛ እንደሚሠራው፣ ኤፉዱ በተሠራበት መንገድ ፍርድ የሚሰጥበትን የደረት ኪስ አብጅ። ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ሥራው።
16አራት ማእዘን ያለ ውይሁን። የደረት ኪሱን ዐጥፈህ ድርብ አድርገው። አንድ ስንዝር እርዝመት፣ አንድ ስንዝር ስፋትም ይኑረው።
17ዕንቆችን በአራት ረድፍ አስቀምጥ። የመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፣ ቶነዝዮንና አብረቅራቂ ዕንቊ ሊኖሩት ይገባል።
18ሁለተኛው ረድፍ በሉር፣ ሰንፔርና አልማዝ ይኑሩት።
19ሦስተኛው ረድፍ ያክንት፣ ኬልቄዶንና አማቴስጢኖስ ይገኙበታል።
20አራተኛው ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያስጲድ ይኑሩት። በወርቅ ፈርጥ ክፈፍ ሊደረግላቸው ይገባል።
21ድንጋዮቹ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ስሞች ቅደም ተከተል መሠረት መቀመጥ፣ ከእስራኤል ነገዶች አንዱን በመወከልም በቀለበት ማተሚያ እንደሚቀረጽ እያንዳንዱ ስም የተቀረጸባቸው መሆን አለባቸው።
22ኪሱ ከንጹሕ ወርቅ እንደ ገመድ የተጎነጎኑ ድሪዎችን አብጅለት።
23ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሥራና ከደረት ኪሱ ሁለት ጎኖች ጋር አያይዛቸው።
24የወርቅ ድሪዎች ከደረት ኪሱ ሁለት ማእዘኖች ጋር አያይዛቸው።
25ጕንጕን ድሪዎች ሌሎች ጎኖች ከሁለቱ የወርቅ ፈርጦች ጋር አገናኛቸው። ከኤፉፉ የትከሻ ንጣዮች ጋርም በፊቱ በኩል አያይዛቸው።
26የወርቅ ቀለበቶችን ሥራና ከውስጠኛው የኤፉዱ ጎን ቀጥሎ ባለው ጠርዝ ላይ፣ በደረት ኪሱ ሌሎች ሁለት ጎኖች ላይ አድርጋቸው።
27ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን አብጅና በብልኀት ከተጠለፈው ከሴፉዱ መታጠቂያ በላይ፣ መጋጠሚያው አጠገብ ከኤፉዱ ፊት ሁለት የትከሻ ንጣዮች ግርጌ ጋር አያይዛቸው።
28ከኤፉዱ መታጠቂያ በላይ መያያዝ እንዲችሉ፣ የደረት ኪሱን ቀለበቶቹ ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ገመድ ማሰር አለባቸው። ይህም የሚሆነው የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ጋር ሳይያያዝ እንዳይቀር ነው።
29አሮን ወደ መቅደሱ በገባ ጊዜ፣ የዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ልጆች ስሞች በደረት ኪሱ ላይ ለፍርድ በልቡ ላይ ይሸከም። ይህም በእግዚአብሔር ፊት የዘለዓለም መታሰቢያ ሆኖ ያገለግላል።
30በፍርድ መስጫው የደረት ኪስ ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አስቀምጥ። አሮን ወደ እግዚአብሔር ፊት ሲቀርብ፣ ኡሪምና ቱሚም በደረቱ ላይ መኖር አለባቸው፤ አሮንም ለእስራኤል ፍርድ መስጫውን በእግዚአብሔር ፊት ሲቀርብ ሁልጊዜ መሸከም ይኖርበታል።
31ቀሚስ ሙሉ በሙሉ ሰማያዊ ይሁን።
32ለራስ ማስገቢያ ክፍተት ይኑረው፤ ክፍተቱም እንዳይቀደድ ዙሪያውን የተዘመዘመ ጠርዝ ይኑረው። ይህ ሥራ የሸማኔ ሥራ መሆን አለበት።
33የግርጌ ጠርዝ ላይ የሰማያዊ፣ የሐምራዊና የቀይ ማግ ሮማኖችን በዙሪያው አድርግ። በመካከላቸውም ዙሪያውን የወርቅ ሻኵራዎችን አብጅ።
34የወርቅ ሻኵራዎቹና ሮማኖቹ በቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ እየተፈራረቁ መቀመጥ አለባቸው።
35ወደ መቅደሱ ሲገባና በእግዚአብሔር ፊት ሲሆን፣ ከመቅደስ ሲወጣም፣ ድምፁ እንዲሰማ ቀሚሱን አሮን ሲያገለግል ይልበሰው። ይህም የሚደረገው አሮን እንዳይሞት ነው።
36ከንጹሕ ወርቅ ሳሕን አብጅና በቀለበት ላይ ማኅተም እንደሚቀረጽ፣ “ቅዱስ ለእግዚአብሔር” ብለህ በላዩ ቅርጽበት።
37ሳሕን ከመጠምጠሚያው ፊት ጋር በሰማያዊ ገመድ አያይዘው።
38ሁልጊዜም በአሮን ግንባር ላይ ይሁን፤ አሮን እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ለይተው ከሚያቀርቧቸው የተቀደሱ ስጦታዎች ጋር የሚያያዝ ማንኛውንም በደል ይሸከማል። እግዚአብሔር ስጦታዎቻቸውን እንዲቀበል፣ መጠምጠሚያ ሁልጊዜ በአሮን ግንባር ላይ መሆን አለበት።
39ሸሚዙንም፣ መጠምጠሚያውንም ከአማረ በፍታ ትሠራለህ። መታጠቂያውም በጥልፍ ጠላፊ እንዲሠራ ታደርጋለህ።
40ለአሮን ልጆችም ሸሚዞቹን፣ መታጠቂያዎችንና የራስ ማሰሪያዎችን ለክብራቸውና ለማዕረጋቸው ታደርጋለህ።
41ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ አልብሳቸው። ቅባቸው፣ ሹማቸውም፤ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝም ለእኔ ቀድሳቸው።
42እስከ ጭን የውስጥ ሰውነታቸውን የሚሸፍን የውስጥ ልብሶችን ከበፍታ ሥራ።
43ልጆቹ ውደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ፣ ወይም መቅደሱ ውስጥ ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ እነዚህን የውስጥ ልብሶች መልበስ አልባቸው። በደል እንዳይገኝባቸውና እንዳይሞቱ ይህን ማድረግ ይገባቸዋል። ይህ ለአሮንና ከእርሱም በኋላ ለሚመጡት ዘሮቹ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።