መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 29

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሆነው እንዲያገለግሉኝ እነርሱን ለእኔ ለመቀደስ አሁን የምታደርገው ይህ ነው። ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች፣
2የሌለበትን እንጀራና ዘይት የተቀላቀለበትን እንጎቻ ውሰድ፤ ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣም አድርግ።
3በአንድ ሌማት አድርጋቸውና ከወይፈኑና ከአውራ በጎቹ ጋር አቅርባቸው።
4አሮንንና ልጆቹንም ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ አቅርባቸው። በውሀም እጠባቸው።
5ውሰድና፦ ሸሚዙን፣ የኤፉዱን ቀሚስ፣ ኤፉዱን፣ የደረት ኪሱን፣ በብልኀት የተጠለፈውን የኤፉዱን መታጠቂያ በወገቡ ዙሪያ በማስታጠቅ አሮን አልብሰው።
6ቅዱሱን አክሊል በላዩ አስቀምጠህ መጠምጠሚያውን በአሮን ራስ አድርግ።
7ዘይቱንም ወስደህ በራሱ ላይ በማፍሰስ ቅባው።
8አምጥተህ ሸሚዞችን አልብሳቸው።
9መታጠቂያዎችን ለአሮንና ለልጆቹ ታስታጥቃቸዋለህ፤ የራስ ማሰሪያዎችንም ታደርግላቸዋለህ። የክህነቱ ሥራ በዘለዓለማዊ ሕግ የእነርሱ ይሆናል። እኔን እንዲያገለግሉኝ አሮንና ልጆቹን ትክናቸዋለህ።
10በመገናኛው ድንኳን ፊት አቅርብ፤ አሮንና ልጆቹም በወይፈኑ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ።
11በእኔ በእግዚአብሔር ፊት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ዕረደው።
12ከወይፈኑ ደም ጥቂት በጣትህ ወስደህ በመሠዊያው ቀንዶች ላይ ታደርጋለህ፤
13የሆድ እቃዎችን የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ ጉበቱን የሚሸፍነውንና ሁለቱን ኩላሊቶች በላያቸው ካለው ስብ ጋር ወስደህ ሁሉንም በመሰዊያው ላይ ታቃጥላቸዋለህ።
14ነገር ግን የወይፈኑን ሥጋ ግን ቁርበቱንና ፈርሱን ጭምር ከሰፈር ውጭ አውጥተህ ታቃጥላለህ። ያ የኀጢአት መሥዋዕት ይሆናል።
15የአውራ በግም ውሰድና አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውን ይጫኑበት።
16በጉን ዕረደው፤ ደሙንም ወስደህ በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን እርጨው።
17በጉን ለሁለት ክፈልና የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን እጠብ፤ የሆድ ዕቃውንም ከተቆራተጡ ብልቶችና ከራሱ ጋር
18ላይ አስቀምጥ። ከዚያም እውራ በጉን ሙሉ በሙሉ አቃጥለው። ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል። ይህም ለእኔ ጣፋጭ መዐዛ ያለው፣ በእሳት የቀረበልኝ መሥዋዕት ይሆናል።
19ሌላውንም አውራ በግ ወስደህ አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት።
20በኋላ አውራ በጉን ዕረደው፤ ከደሙም ጥቂት ውሰድና በአሮን ቀኝ ጆሮ ጫፍና በልጆቹ ቀኝ ጆሮዎች ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጆቻቸውና በቀኝ እግሮቻቸው አውራ ጣቶች ላይ አድርግ። ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን እርጨው።
21ካለው ደም፣ ከመቅቢያው ዘይትም ጥቂት ውሰድና በአሮንና በልብሶቹ፣ በልጆቹና በልብሶቻቸውም ላይ እርጨው። አሮንና ልብሶቹ፣ ልጆቹና ልብሶቻቸው ከእርሱ ጋር ይቀደሱልኛል።
22በጉን ሥብ፣ ላቱን፣ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ የጉበቱን መሸፈኛ፣ ሁለቱን ኵላሊቶችና በላያቸው የሚገኘውን ሥብ፣ የቀኙን ወርችም ውሰድ፤ ይህ አውራ በግ ካህኑ ለእኔ የሚቀደስበት ነውና።
23እንጀራ፣ አንድ በዘይት የተጋገረ እንጎቻና አንድ ስስ ቂጣ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ከሚሆነው ያለ እርሾ ከተጋገረው ኅብስት ሌማት ትወስዳለህ።
24እነዚህን በአሮን እጆችና በልጆቹ እጆች ታስቀምጣለህ። እነርሱ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዟቸው፤ መሥዋዕት አድርገውም ለእኔ ያቅርቧቸው።
25ከእጆቻቸው ወስደህ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር በመሠዊያው ላይ አቃጥለው። ለእኔ ጣፋጭ መዐዛ ያለው፣ በእሳት የቀረበልኝ መሥዋዕት ይሆናል።
26የአሮንን የክህነት አውራ በግ ፍርምባ ወስደህ ወዝውዘውና መሥዋዕት አድርገህ ለእኔ ለእግዚአብሔር አቅርበው። ይህም አንተ የምትበላው የአንተ ድርሻ ይሆናል።
27የመሥዋዕቱን ፍርምባና የቀረበውን የመሥዋዕቱን ወርች ለእኔ ቀድስልኝ፤ ሁለቱም አሮንና ልጆቹ ለእኔ ካህናት መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከአውራ በጉ የሚገኙ ናቸው።
28የሚሰጧቸው እነዚህ የሥጋ ክፍሎች ምንጊዜም የአሮንና የልጆቹ ናቸው። በኅብረቱ መሥዋዕቶች ሥርዐት፣ ከእስራኤላውያን ለካህናቱ፣ ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርቡ መሥዋዕቶች ይሆናሉ።
29የአሮን የተቀደሱ ልብሶች ከእርሱ በኋላ ለልጆቹም ይሆናሉ። በልብሶቹ የአሮን ልጆች ለእኔ መቀባትና መካን አለባቸው።
30በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ እኔን ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን የሚገባ፣ አሮንን ከልጆቹ መካከል የሚተካ እነዚያን ልብሶች ሰባት ቀን ይልበስ።
31የክህነቱን አውራ በግ ውሰድና ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ቀቅለው።
32ልጆቹ የአውራ በጉን ሥጋና በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር ባለው ሌማት የተቀመጠውን ኅብስት ይብሉት።
33ለማስተስረይና ለእኔ እንዲቀደሱ የቀረቡትን ሥጋውንና ኅብስቱን መብላት አለባቸው። ሌላ ሰው መብላት አይችልም፤ ምክንያቱም ምግቡን ለእኔ የተቀደሰ አድርገው ሊይዙት ይገባል።
34መሥዋዕቱ ሥጋ፣ ወይም ከኅብስቱ እስከሚቀጥለው ጠዋት ድረስ አንዳች የሚተርፍ ከሆነ፣ አቃጥለው። ለእኔ የተቀደሰ ስለ ሆነ መበላት የለበትም።
35በዚህ መንገድ እንድታደርገው ያዘዝሁህን ሁሉ በመከተል ለአሮንና ለልጆቹ ትፈጽምላቸዋለህ። እነርሱን ሰባት ፍቀን ቀድስልኝ።
36ለስርየት የሚሆን የኀጢአት መሥዋዕት በየቀኑ አንድ ወይፈን አቅርብ። ማስተሰረያውን በማድረግም መሠዊያውን አንጻ፤ ለእኔ ለመቀደስም ቅባው።
37ሰባት ቀን ማስተሰረያ አድርግለትና ለእግዚአብሔር ቀድሰው። ከዚያ በኋላ መሠዊያው ሙሉ በሙሉ የተቀደሰ ይሆናል፤ መሠዊያውን የሚነካውም ሁሉ ይቀደሳል።
38የአንድ ዓመት ጠቦቶችን ዘወትር በየቀኑ በመሠዊያው ላይ አቅርብ።
39ጠቦት ማለዳ፣ ሌላውን ደግሞ ምሽት ላይ ታቀርበዋህ።
40ከመጀመሪያው ጠቦታ ጋር የኢፍ አንድ ዐሥረኛን ያማረ ዱቄት ተወቅጦ ከተጠለለ ሩብ ኢፍ ዘይት ጋር በመለወስ፣ ሩብ ወይንንም የመጠጥ ቍርባን በማድረግ አቅርብ።
41ሁለተኛውን ጠቦት በምሽት ሠዋው። በማለዳ እንደ ተሠዋው ጠቦት ተመሳሳይ የእህልና የመጠት ቍርባን ማቅረብ አለብህ። እነዚህ መሥዋዕቶች ለእኔ ጣፋጭ መዐዛ ያላቸው በእሳት የቀረቡልኝ መሥዋዕቶች ናቸው።
42ትውልዶች ሁሉ ዘወትር የሚቀርቡ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ናቸው። ላናግራችሁ ከእናንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በእኔ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕቶቹን አቅርቧቸው።
43ከእስራኤላውያን ጋር የምገናኝበት ቦታ ያ ነው፤ ድንኳኑ በክብሬ ይቀደስልኛል።
44የመገናኛውን ድንኳንና መሠዊያውን የእኔ ብቻ እንዲሆኑ እቀድሳቸዋለሁ። ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ አሮንንና ልጆቹን እለያቸዋለሁ።
45በእስራኤላውያን መካከል እኖራለሁ፤ አምላካችውም እሆናለሁ።
46በመካከላቸው እንድኖር፣ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው እኔ እግዚአብሔር አምላካችው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።