መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 27

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ዐምስት ክንድ ወርዱም ዐምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ። መሠዊያው አራት ማእዘንና ሦስት ክንድ ከፍታ ይኑረው።
2ማእዘኖች የበሬ ቀንድ ቅርጽ እንዲኖራቸው ታደርጋለህ። ቀንዶቹ ከመሠዊያው ጋር አንድ ወጥና በነሐስ የተለበጡ ይሆናሉ።
3የመሠዊያውን ዕቃዎች፦ የዐምድ ማስወገጃ ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ጎድጓዳ ሳሕኖችን፣ የሥጋ ሜንጦዎችንና የፍም መያዣዎችን ሁሉ ከነሐስ አብጃቸው።
4ለመሠዊያው ከነሐስ እንደ መረብ የተሠራ ፍርግርግ አብጅለት። በፍርግርጉ አራት ማእዘኖች በያንዳንዳቸው ላይም የነሐስ ቀለበት አድርግ።
5አጋማሽ ወገብ እስከ ታች እንዲደርስ ፍርግርጉን ከመሠዊያው እርከን ሥር አድርገው።
6ለመሠዊያው መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት አበጅተህ በነሐስ ለብጣቸው።
7በቀለበቶቹ ውስጥ መግባትና መሠዊያውን ለመሸከም በሁለቱ ጎኖቹ ላይ መቀመጥ አለባቸው።
8ባዶ እንዲሆን ከሳንቃዎች አብጀው። በተራራው ላይ ባየኸው መሠረት ልትሠራው ይገባል።
9ድንኳን አደባባይ ሥራለት። በአደባባዩ ደቡብ ጎንም አንድ መቶ ክንድ እርዝመት ያላቸው የአማረ በፍታ መጋረጃዎች ይደረጉ።
10መጋረጃዎቹ ከሃያ የነሐስ መቆሚያዎች ጋር ሃያ ምሰሶዎች ይኑሯቸው። ከምስሶዎቹ ጋር የተያያዙ የብር ኵላቦችና ዘንጎችም መኖር አለባቸው።
11በሰሜን በኩልም እንደዚሁ አንድ መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ከሃያ ምሰሶዎች፣ ከሃያ የነሐስ መቆሚያዎችም ጋር ከምሰሶውቹ ጋር የተያያዙ የብር ኵላቦችና ዘንጎች ሊኖሩ ይገባል።
12በአደባባዩ ምዕራብ ጎንም ዐምሳ ክንድ ርዝመት ያለው መጋረጃ ይደረግ። ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር መቆሚያዎችም ይኑሩት።
13በምሥራቅም በኩል አደባባዩ ዐምሳ ክንድ እርዝመት ይኑረው።
14የመግቢያው አንድ ጎን መጋረጃዎች ዐሥራ ዐምስት ክንድ እርዝመት ሊኖራቸው ይገባል። ሦስት ምሰዎችም ከሦስት መቆሚያዎች ጋር ይኖሯቸዋል።
15ሌላው ጎንም ዐሥራ ዐምስት ክንድ እርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይኖሩታል። የራሳቸው ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ይኖሯቸዋል።
16መግቢያ መጋረጃ ሃያ ክንድ እርዝመት ያለው፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ጠላፊ ጠልፎበት የተሠራ ይሁን። አራት ምሰሶዎች ከአራት መቆሚያዎች ጋር ሊኖሩት ይገባል።
17የአደባዩ ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎችና ኵላቦች፣ የነሐስ መቆሚያዎችም ይኑሯቸው።
18የአደባባዩ እርዝመት አንድ መቶ ክንድ፣ ወርዱ ዐምሳ ክንድ፣ ቁመቱ ዐምስት ክንድ ይሁን፤ የበፍታ መጋረጃዎችና የነሐስ መቆሚያዎችም ይኑሩት።
19በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አገልግሎት የሚሰጥ ዕቃ ሁሉ፣ የድንኳኑ ካስማዎችም በሙሉ፣ አደባባዩም ከነሐስ መሠራት አለባቸው።
20ሁልጊዜ እንዲበሩ ለመብራቶቹ የወይራ ጭማቂ ንጹሕ ዘይት እንዲያመጡ እስራኤላውያንን እዘዛቸው።
21በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፣ ከመጋረጃው ውጭ በምስክሩ ታቦት ፊት፣ አሮንና ልጆቹ መብራቶቹን ከማታ እስከ ንጋት ድረስ በእግዚአብሔር ፊት እንዲበሩ ያድርጉ። ይህም ለእስራኤል ትውልድ ሁሉ የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።