መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 26

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከተፈተለ በፍታ ድር፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ከተሠሩና ኪሩቤል ከተጠለፉባቸው ዐሥር መጋረጃዎች ጋር ማደሪያ ድንኳኑን ሥራ። ይህም ብልኅ ሠራተኛ የሚሠራው ሥራ ነው።
2የያንዳንዱ መጋረሣ እርዝመት ሃያ ስምንት ክንድ፣ ወርዱ አራት ክንድ ይሁን። መጋረጃዎቹ ሁሉ እኩል መጠን ይኑራቸው።
3ዐምስቱ መጋረጃዎች እርስ በርስ መያያዝ አለባቸው፤ ሌሎቹ ዐምስት መጋረጃዎችም እንደዚሁ እርስ በርሳቸው መገጣጠም ይኖርባቸዋል።
4በአንደኛው ወገን የመጨረሻ መጋረጃ የውጭ ጠርዝ ላይ የሰማያዊ ግምጃ ቀለበቶችን አድርግ። ለሁለተኛው ወገን የመጨረሻ መጋረጃ የውጭ ጠርዝም ይህንኑ አበጅለት።
5ዐምሳ ቀለበቶችን በአንደኛው የመጋረጃ ወገን፣ ዐምሳ ቀለበቶችን በሌላው የመጨረሻ መጋረጃ ላይ አድርግ። ይህን የምትሠራውም ቀለበቶቹ እርስ በርስ እንዲተያዩ በማድረግ ነው።
6ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዊችብ ሠርተህ ማደሪያ ድንኳኑ አንድ እንዲሆን፣ መጋረጃዎቹን በእነርሱ አያይዛቸው።
7ከማደሪያው በላይ ለድንኳን የሚሆኑ ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎችን ሥራ።
8መጋረጃ እርዝመት ሠላሳ ክንድ፣ ወርዱ አራት ክንድ ይሁን። ዐሥራ አንዱም መጋረጃዎች እኩል መጠን ይኑራቸው።
9ዐምስት መጋረጃዎችን በአንድነት፣ ስድስት መጋረጃውችንም እንዲሁ እርስ በርስ አያይዛቸው። ስድስተኛውን መጋረጃ በድንኳኑ ፊት ዕጠፈው።
10በመጀመሪያ ተገጣጣሚ የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን፣ ሁለተኛውን የመጋረጃ አካል በሚያገጣጥመው የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይም እንደዚሁ ዐምሳ ቀለበቶችን አድርግ።
11ዐምሳ የነሐስ ማያያዣዎችን ሥራና በቀለበቶቹ ውስጥ አስገ ባቸው። ከዚያም አንድ ወጥ እንዲሆን ድንኳኑን አገጣጥመው።
12መጋረጃዎች ተንጠልጥሎ ያለው ቀሪ ግማሽ መጋረጃ ከማደሪያ ድንኳኑ ጀርባ ይንጠልጠል።
13ከመጋረጃዎቹ እርዝመት የተረፈው በአንድ በኩል አንድ ክንድ ምጋረጃ፣
14በሌላው ጎንም አንድ ክንድ መጋረጃ ማደሪያው ድንኳን መሸፈኛ በቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና ከዚያም በላይ የሚሆን የአስቆጣ ቁርበት አዘጋጅ።
15ለማደሪያው ድንኳን የሚሆኑ ወጋግራዎችን ከግራር ዕንጨት አብጅ።
16ወጋግራ እርዝመት ዐሥር ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።
17በርስ የሚያገናኗቸው ሁለት ጕጣጕጦች በያንዳንዱ ወጋግራ ላይ ይኑር። የመገናኛ ድንኳኑን ወጋግራዎች ሁሉ በዚህ መንገድ ሥራ።
18ድንኳን ወጋግራዎችን ስታበጅ፣ በደቡብ መኩል ላለው ሃያ ወጋግራዎችን አብጅ።
19ወጋግራዎች የሚሆኑ አርባ የብር መቆሚያዎችን አብጅ። ከመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መጋጠሚያዎች እንዲሆኑ ሁለት መቆሚያዎች ይኑሩ። በሌሎች ወጋግራዎች በያንዳንዳቸው ሥርም ለሁለት መጋጠሚያዎቻቸው ሁለት መቆሚያዎች ይዘጋጁ።
20በሰሜን በኩል ላለው ለሁለተኛው የመገናኛው ድንኳን ጎን ሃያ ወጋግራዎችንና አርባ የብር መቆሚያዎቻቸውን ሥራ።
21በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለው ወጋግራ ሥርም እንደዚሁ ሁለት መቆሚያዎች. በእያንዳንዱ ሥር ይሁኑ።
22በምዕራብ በኩል ላለው ለመገናኛው ድንኳኑ የኋላ ጎን ስድስት ወጋግራዎችን አብጅ።
23ለኋላ ማእዘኖቹም ሁለት ወጋግራዎችን አብጅ።
24እነዚህ ወጋግራዎች ከታች ጥንድ፣ ከላይ ደግሞ በአንድ ቀለበት የተያያዙ መሆን አለባቸው። ለሁለቱም የኋላ ማእዘኖች የሚሆነው በዚህ መንገድ ነው።
25ወጋግራዎች ከብር መቆሚያዎቻቸው ጋር ሊኖሩ ይገባል። በሁሉም ዐሥራ ስድስት መቆሚያዎች ናቸው ያሉት፤ በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለው ወጋራ ሥርም ሁለት መቆሚያዎችና በእያንዳንዱም ሥር እንዲሁ።
26ድንኳኑ አንደኛ ጎን ወጋግራዎች ዐምስት አግዳሚዎችን ከግራር ዕንጨት አዘጋጅ፤
27ለማደሪያ ድንኳኑ ሌላ ጎንም ወጋግራዎች ዐምስት አግዳሚዎችን፣ በምዕራብ በኩል ላለው ለመገናኛ ድንኳኑ የኋላ ጎን ወጋግራዎችም ዐምስት አግዳሚዎችን እንዲሁ አብጅ።
28በወጋግራዎቹ መካከል ላይ ያለው አግዳሚ ከዳር እስከ ዳር መድረስ አለበት።
29ወጋግራዎቹን በወርቅ ለብጣቸው። አግዳምዎችን ደግፍ በመያዝ እንዲያገለግሉም የወርቅ ቀለበቶቻቸውን ሥራላቸው፤ አግዳሚዎችንም በወርቅ ለብጣቸው።
30ድንኳኑን መትከል ያለብህ በተራራው ላይ ያየኸውን ምሳሌ በመተከትል ነው።
31ብልኅ ሠራተኛ ኪሩቤልን የጠለፈበት፣ የሰማያዊ፣ የሐምራዊ፣ የቀይ ግምጃና አምሮ የተፈተለ በፍታ መጋረጃ አብጅ።
32በወርቅ በተለበጡ የግራር ዕንጨት አራት ዐምዶች ላይ ልትሰቅለው ይገባል። እነዚህ ዐምዶች በአራት የብር መቆሚያዎች ላይ የተቀመጡ የወርቅ ኵላቦች ይኖሯቸዋል።
33መጋረጃውን በማያያዣዎቹ አንጠልጥለው፤ የምስክሩንም ታቦት አግባው። መጋረጃው ቅድስቱን ከቅድስተ ቅዱሳን ይለየዋል።
34በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ባለ ውበምስክሩ ታቦት ላይ የስርየት መክደኛውን አስቀምጥ።
35ከመጋረጃው ውጭ፣ መቅረዙንም ከመገናኛው ድንኳን ደቡባዊ ጎን ከጠረጴዛው ትይዩ አስቀምጥ። ጠረጴዛው በሰሜናዊ ጎኑ በኩል መቀመጥ ይኖርበታል።
36መግቢያ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ በጥልፍ ብሚያስጌጥ ሠራተኛ የተሠራ መጋረጃ አብጅለት።
37ዐምስት ምሰሶዎችን ከግራር ዕንጨት አብጅና በወርቅ ለብጣቸው። ኵላቦቻቸውም የውርቅ መሆን እላቸው፤ ዐምስት የነሐስ መቆሚያዎችንም ሥራላቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።