መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 25

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሙሴን እንዲህ አለው፤
2“እያንዳንዱ ሰው ልቡ በፈቀደለት መሠረት ስጦታ ለእኔ እንዲያመጣ ለእስራኤላውያን ንገር። እነዚህን ስጦታዎች ተቀበልልኝ።
3ከእነርሱ የምትቀበላቸውም ስጦታዎች እነዚህ ናቸው፦ ወርቅ፣ ብርና ነሐስ፤
4ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የበፍታ ድር ልብስ፣ የፍየል ጠጕር፣
5ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና የአቆስጣ ቁርበት፣ የግራር ዕንጨት፤
6ለመቅደሱ መብራቶች ዘይት፣ ለመቅቢያው ዘይት ቅመሞችና ጣፋጭ መዐዛ ያለው ዕጣን፤
7ለኤፉድና ለደረት ኪሱ የሚሆኑ መረግዶችና ሌሎች ዕንቆች።
8እንዳድር ሕዝቡ መቅደስ ይሥሩልኝ።
9ለመገናኛው ድንኳንና ለዕቃዎቹ ሁሉ እኔ ባሳየሁህ ምሳሌ መሠረት ሥሩት።
10ሁለት ክንድ ተኩል፣ ስፋቱ አንድ ክንድ ተኩል፣ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦት ከግራር ዕንጨት ይሠሩ።
11ውስጡንም ውጭውንም በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አድርግለት።
12የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተህለት በታቦቱ አራት እግሮች ላይ፣ ሁለቱን በአንድ ጎኑ፣ ሁለቱን ደግሞ በሌላው ጎኑ አስቀምጣቸው።
13መሎጎያዎችን ከግራር ዕንጨት ሥራና አወርቅ ለብጣቸው።
14ታቦቱን ለመሸከም መሎጊያዎቹን በታቦቱ ጎን ባሉ ቀለበቶች ውስጥ አስገባ።
15መሎጊያዎቹ ምንጊዜም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ ይቀመጣሉ እንጂ ከዚያ አይወጡም።
16የኪዳኑን ምስክሮች በታቦቱ ውስጥ ታስቀምጣለህ።
17ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሥራ።
18ለሁለቱ የስርየት መክደኛ ጫፎች ሁለት ኪሩቤልን ከተቀጠቀጠ ወርቅ ትሠራለህ።
19ኪሩብ ለስርየት መክደኛው አንድ ጫፍ፣ ሌላውን ኪሩብ ደግሞ ለሌላው ጫፍ በማድረግ ከስርየት መክደኛው ጋር ወጥ ሆነው መሠራት አለባቸው።
20ክንፎቻቸውን ወደ ላይ መዘርጋትና የስርየት መክደኛውን በክንፎቻቸው መጋረድ ይኖርባቸዋል። እርስ በርሳቸው መተያየትና ወደ ስርየት መክደኛውም መመልከት አለባቸው።
21መክደኛውን በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ፤ በታቦቱ ውስጥም የምሰጥህን የኪዳኑን ምስክሮች ታስቀምጣለህ።
22እኔ ከአንተ ጋር የምገናኘው በታቦቱ ነው። በስርየት መክደኛው ላይ ሆኜ ከአንተ በተናገርሁበት በምስክሩ ታቦት ላይ ባሉት በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ነው።
23እርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ፣ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ጠረጴዛ ከግራር ዕንጨት ሥራ።
24ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አድርግለት።
25አንድ ስንዝር ስፋት ያለው ጠርዝ ለጠርዙ በዙሪያው ከሚኖረው የወርቅ ክፈፍ ጋር አብጅለት።
26አራት የወርቅ ቀለበቶችን ሥራለትና ቀለበቶችን አራቱ እግሮቹ ባሉበት ከሚገኙት አራት ማዕዘኖች ጋር አያይዛቸው።
27ለማስቀመጥና ጠረጴዛውን መሸከም እንዲቻል፣ ቀለበቶቹ ከክፈፉ ጋር መያያዝ አለባቸው።
28የጠረጴዛው መሸከሚያ እንዲሆኑም መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት ሥራና በወርቅ ለብጣቸው።
29ቊርባኑን ለማፍሰስ ጥቅም እንዲሰጡ ወጭቶችን፣ ጭልፋዎችን፣ ማንቆርቆሪያዎችንና ጎድጓዳ ሣህኖችን ከንጹህ ወርቅ ሥራ።
30በጠረጴዛውም ላይ የገጽ ኅብስት ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ።
31መቆሚያና ዘንግ አበጅተህበት ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ መቅረዝ። ጽዋዎቹ፣ ቀንበጦቹና አበባዎቹ ሁሉ ወጥ ሆነው ከመቅረዙ ጋር ይሠራሉ።
32ሦስት ቅርንጫፎች በአንድ ጎን፣ ሦስት ቅርንጫፍ ደግሞ በሌላው ጎን፣ ስድስት ቅርንጫፎች ለመቅረዙ ይውጡለት።
33የመጀመሪያው ቅርንጫፍ የለውዝ አበቦችን መስለው የተሠሩ ሦስት ጽዋዎች ከቀንበጥና ክአበባ ጋር፣ በሌላው ቅርንጫፍም እንደዚሁ የለውዝ አበቦችን የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች የተቀረጹበት ከቀንበጥና ከአበባ ጋር ሊኖሩት ይገባል። ከመቅረዙ በሚወጡት በስድስት ቅርንጫፎች ሁሉ ላይ የሚሆነውም እንደዚሁ አንድ ዐይነት ነው።
34ላይ የለውዝ አበባ መስለው የተቀረጹ አራት ጽዋዎች ከቀንበጦቹና ከአበባዎቹ ጋር ሊኖሩበት ይገባል።
35በመጀመሪያዎቹ ቅርንጫፎች ጥንድ ሥር ወጥ ሆኖ ዐብሮ የተሠራ ቀንበጥ፣ በሁለተኛው የቅርንጫፎች ጥንድ ሥርም እንደዚሁ ወጥ ሆኖ ዐብሮ የተሠራ ቀንበጥ ይኖረዋል። በሦስተኛው የቅርንጫፎቹ ጥንድ ሥርም ወጥ ሆኖ ዐብሮ የተሠራ ቀንበጥ ይበጅለታል። ከመቅረዙ በሚወጡ በስድስቱ ቅርንጫፎች ሁሉ የሚሆነውም ይኸው አንድ ዐይነት ነው።
36ቀንበጦቻቸውና ቅርንጫፎቻቸው ሁሉ አንድ ወጥና ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መሆን አለባቸው።
37መቅረዙንና ሰባት መብራቶችን ሠርተህ ፊት ለፊት ላለው ስፍራ ብርሃን እንዲሰጥ አድርግ።
38የኵስታሪ መሰብሰቢያ ሣህኖቻቸው ከንጹሕ ወርቅ መሠራት አለባቸው።
39መቅረዙንና የመቅረዙን ዕቃ ሁሉ ለመሥራት አንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ተጠቀም።
40ላይ ባሳየሁህ ምሳሌ መሠረት የሠራሃቸው ስለ መሆንህ እርግጠኛ ሁን።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።