1እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተ፣ ናዳብ፣ አብድዩና ሰባው የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ እኔ ኑ፤ በርቀት ሆናችሁም ስገዱልኝ።
2ሙሴ ብቻ ወደ እኔ መቅረብ ይችላል። ሌሎች መቅረብ የለባቸውም፤ ወይም ሕዝቡ ከሙሴ ጋር መምጣት አይችሉም።”
3ሙሴ ወደ ሕዝቡ ሄዶ እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎችና ሕጎቹን ሁሉ ነገራቸው። ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ፣ “እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እናደርጋለን” ብለው መለሱ።
4ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ሁሉ ጻፈ። ማለዳ ላይም በተራራው ግርጌ መሠዊያ ሠራ፤ ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ነገዶች እንዲወክሉም፣ ዐሥራ ሁለት የድንጋይ ዐምዶችን አቆመ።
5የሚቃጠልና የኅብረት መሥዋዕቶችን ከበሬዎች ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡም፣ ጥቂት የእስራኤል ወጣት ወንዶችን ላከ።
6ሙሴ የደሙን እኩሌታ በሣህን አደረገው፣ የቀረውንም እኩሌታ በመሠዊያው ላይ ረጨው።
7መጽሐፍ ወስዶ ለሕዝቡ ጮኽ ብሎ አነበበላቸው። ሕዝቡም፣ “እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉእናደርጋለን፤ እንታዘዛለንም” ብለው ተናገር።
8ሙሴ ደሙን ወስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው። “ይህ፣ ይህን የተስፋ ቃል ከእነዚህ ቃሎች ጋር ለእናንተ በመስጠት፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባው የኪዳኑ ደም ነው” በማለትም ተናገረ።
9ከዚያም በኋላ ሙሴ፣ አሮን፣ ናዳብ፣ አብድዩና ሰባው የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ተራራው ወጡ።
10የእስራኤልን አምላክ አዩት። ከእግሮቹ ሥርም እንደ ንጹሕ ሰማይ ከጠራ የሰንፒር ድንጋይ የተሠራ ወለል ነበረ።
11በእስራኤላውያን ሽማግሌዎች ላይ ተቆጥሮ እጅ አላሳረፈባቸውም። እነርሱ እግዚአብሔርን አዩ፤ በሉ፣ ጠጡም።
12እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ተራራው ላይ ወደ እኔ ና፤ በዚያም ቆይ። የድንጋይ ጽላቱን ሕዝቡን እንድታስተምራቸውም የፋጽሏቸውን ሕጉንና ትእዛዛቱን እሰጥሃለሁ” አለው።
13ስለዚህ ሙሴ ከረዳቱ ከኢያሱ ጋር ወደ እግዚአብሔር ተራራ ሄደ።
14ሙሴ ሽማግሌዎቹን፣ “ተመልሰን ወደ እናንተ እስክንመጣ ድረስ እዚህ ቆዩን። አሮንና ሖር ከእናንተ ጋር ናቸው። ክርክር የሚኖርበት ሰው ካለ፣ ወደ እነርሱ ይቅረብ” አላቸው።
15ወደ ተራራው ወጣ፤ ደመናውም ተራራውን ሸፈነው።
16የእግዚአብሔር ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ ደመናውም ተራራውን ስድስት ቀን ሸፈነው። በሰባተኛው ቀን እግዚአብሔር ከደመናው ውስጥ ሙሴን ጠራው።
17የእግዚአብሔርን ክብር እስራኤላውያን ሲያዩት እንደሚያጋይ እሳት ነበር።
18ሙሴ ደመናው ውስጥ ገብቶ ወደ ተራራው ወጣ። በተራራውም ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቆየ።