1ማንም ሰው የሐሰት ወሬ እትናገር። ሐሰተኛ ምስክር ለመሆን ከክፉ ሰው ጋር አትተባበር።
2ክፋት ለመፈጸም ሕዝብን አትከተል፤ ወይም ፍትሕን ለማጣመም ከሰዎች ጋር ተባብረህ ምስክርነት አትስጥ።
3ድኻውን በሙግቱ አታድላለት።
4በሬ ወይም አህያ ጠፍቶ ብታገኘው መልስለት።
5የሚጠላህን ሰው አህያ እንደ ተጫነ ከጭነቱ ሥር ወድቆ ብታየው፣ ያን ሰው ትተኸው አትሂድ። አህያውን ለማንሣት ልታግዘው ይገባል።
6ጊዜ ለድኻው ወገንህ የሚሰጠውን ፍትሕ አታጣምም።
7በሐሰት ክስ ከሌሎች ጋር አትተ ባበር፤ ንጹሑንም ወይም ጻድቁንም አትግደል፤ እኔ ኀጢአተኛውን ንጹሕ አላደርግምና።
8አትቀበል፤ ጕቦ የሚያዩ ሰዎችን ያሳውራል፤ የታማኝ ሰዎችን ቃልም ያጣምማልና።
9የመጻተኛነትን ስለምታውቁት፣ መጻተኛን አታስጨንቁ፤ እናንተም በግብፅ ምድር መጻተኞች ነበራችሁና።
10ስድስት ዓመት በመሬትህ ላይ ዘር ዝራ፤ መከሩንም ሰብስብ።
11በሰባተኛው ዓመት ግን በሕዝብህ መካከል ያሉ ድኾች መብላት እንዲችሉ ሳታርሰው ዕዳሪውን ተወው። ከድኾች የሚተርፈውንም የዱር እንስሳት ይበሉታል። በወይን ቦታዎችህና በወይራ ዛፎችህም ይህንኑ ታደርጋለህ።
12ቀን ሥራህን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ታርፋለህ። ይህን የምታደርገውም፦ በሬህ፣ አህያህ፣ የሴት አገልጋይህ ወንድ ልጅና መጻተኛው ሁሉ ዕረፍት እንዲያገኙና እንዲዝናኑ ነው።
13የነገርኋችሁን ሁሉ ጠብቁ። የሌሎች አማልክትን ስም አትጥሩ፤ ወይም ስማቸው ከአፋችሁ አይሰማ።
14በየዓመቱ ሦስት ጊዜ ልአእኔ በዓል ታከብራላችሁ።
15በዓልን አክብር። ባዘዝሁህ መሠረት ሰባት ቀን ቂጣ ትበላለህ። በዚያ ጊዜ፣ ለዚህ በተወሰነው በአቢብ ወር በፊቴ ትቀርባለህ። ከግብፅ የወጣኸው በዚህ ወር ነበር። ነገር ግን በፊቴ ባዶ እጅህን መቅረብ የለብህም።
16ላይ የዘራኸውን የእህልህን በኵራት፣ የመከርን በዓል አክብር። በዓመቱ መጨረሻ ምርትህን ከማሳ ስትሰበስብ፣ የመክተቻውን በዓል አክብር።
17ዘንድ ያለ ወንድ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ይቅረብ።
18የመሥዋዕቱን ደም እርሾ ካለበት ዳቦ ጋር ለእኔ አታቅርብ። በበዓሎቼ የሚቀርበው የመሥዋዕቴ ሥብ እስከ ንጋት ድረስ መቆየት የለበትም።
19የመሬትህን ምርጥ ፍሬ በኵራት ወደ እኔ፣ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።
20በመንገድ የሚጠብቅህንና ወዳዘጋጀሁልህ ስፍራ መርቶ የሚያስገባህን መልአክ በፊትህ እልካለሁ።
21ተከተለው፤ ታዘዝለትም። ኀጢአትህን ይቅር አይልህምና አታስቆጣው። ስሜ በእርሱ ላይ ነው።
22ድምፁን በእውነት ብትሰማና የምነግርህን ሁሉ ብታደርግ፣ ለጠላቶችህ ጠላት እሆናለሁ፤ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ።
23መልአክ በፊትህ ይሄዳል፤ አንተንም ወደ አሞራውያንና ወደ ኢያቡሳውያን ምድር ያስገባሃል። እኔ እነርሱን አጠፋቸዋለሁ።
24ለአማልክታቸው አትስገድ፤ አታምልካቸውም፤ ወይም ሕዝቡ እንደሚያደርጉት አታድርግ፤ ይልቁን ፈጽመህ ልታፈራርሳቸው፣ የድንጋይ ዐምዶቻቸውንም ልትሰባብራቸው ይገባል።
25እኔን አምላክህን እግዚአብሔርን አምልክ። ይህን ካደረግህ፣ የምትባውንና የምትጠጣውን እባርካለሁ። በሽታንም ከመካከልህ አጠፋለሁ።
26የምትጨነግፍ ወይም የምትመክን ሴት አትምርም። ለአንተ ረጅም ዕድሜ እሰጥሃለሁ።
27ምድር ሕዝብ ላይ ማስፈራቴን እልካለሁ። የሚያጋጥሙህን ሰዎች ሁሉ እገድላለሁ። ጠላቶችህን ሁሉ ከፍርሀት የተነሣ ጀርባቸውን ወደ አንተ እንዲያዞሩ አደርጋለሁ።
28ከነዓናውያንና ኬጤያውያንን ከፊትህ እንዲያበሯቸው ተርቦችን በፊትህ እሰድዳለሁ።
29ወና እንዳትሆንና የዱር አራዊትም እጅግ እንዳበዙብህ፣ የምድሪቱን ኗሪዎች በአንድ ዓመት ውስጥ ከፊትህ አላባርራቸውም።
30ነገር ግን አንተ እስክትበዛና ምድሪቱን እስክትወርሳት ድረስ በትንሽ በትንሹ አስወጣቸዋለሁ።
31ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፣ ከምድር በዳውም እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ አደርገዋለሁ። በምድሪቱ ኗሪዎች ላይ ድል እንድትጎናጸፍ አደርጋለሁ፤ ከፊትህም ታባርራቸዋለህ።
32ወይም ከአማልክታቸው ጋር ኪዳን አታድርግ።
33እነርሱ በምድርህ ውስጥ መኖር አይገባቸውም፤ አልዚያ በእኔ ላይ ኀጢአት እንድትሠራ ያደርጉሃል። አማልክታቸውን ብታመልክ፣ ይህ በእውነት ወጥመድ ይሆንብሃል።”