መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 22

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅና ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፣ ለአንድ በሬ ዐምስት በሬ፣ ለአንድ በግም ዐምስት በግ መክፈል አለበት፥
2ሌባ በር ሰብሮ ሲገባ ቢገኝና ተደብድቦ ቢሞት፣ በማንም ሰው ላይ የደም ዕዳ አይኖርም።
3ነገር ግን ሰብሮ ከመግባቱ በፊት ፀሐይ ከወጣ፣ በገደለው ሰው ላይ የደም ተጠያቂነት ይኖራል። ሌባ የሰረቀውን መመለስ አለበት። ምንም ነገር ከሌለው፣ የሰረቀውን እንዲከፍል እርሱ ራሱ መሸጥ ይኖርበታል።
4ሆነ አህያ ወይም በግ ቢሆን የተሰረቀው እንስሳ በሕይወት እርሱ ዘንድ ከተገኘ፣ ዕጥፉን መልሶ መክፈል አለበት።
5ሰው ከብቱን መስክ ላይ ወይም የወይን ዕርሻ ውስጥ አሰማርቶ ቢለቅቀውና በሌላ ሰው ዕርሻ ውስጥ ገብቶ ቢግጥ፣ ምርጥ ከሆነው ከራሱ መስክና የወይን ዕርሻ መካስ ይኖርበታል።
6እሳት ቢነሣና በእሾኾችም ውስጥ ቢዛመት፣ ክምሩም፣ ያልታጨደውም እህል ወይም ዕርሻው ቢቃጠል፣ እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሣ ይካሥ።
7ሰው እንዲጠበቅለት ገንዘቡን ወይም ዕቃውን ለጎረቤቱ ቢሰጥ፣ በዐደራ ያስቀመጠውንም ከሰውዬው ቤት ሌባ ቢሰርቀውና ሌባውም ቢገኝ፣ ያ ሌባ ዕጥፍ መክፈል አለበት፤
8ባይገኝ ግን፣ የቤቱ ባለቤት እጁን በጎረቤቱ ንብረት ላይ መዘርጋቱንና አለመዘርጋቱን ለማየት፣ በዳኞች ፊት ሊቀርብ ይገባል።
9ስለ በሬ፣ ስለ አህያ፣ ስለ በግ፣ ስለ ልብስ ወይም አንድ ሰው፣ “ይህ የእኔ ነው” ስለሚለው ስለ ማንኛውም የጠፋ ነገር የሚነሣ ክርክር ሁሉ፣ የሁለቱም ወገን አቤቱታ በዳኞች ፊት መቅረብ አለበት። ዳኞች በደለኛ ሆኖ ያገኙት ሰው ለጎረቤቱ ዕጥፍ መክፈል ይኖርበታል።
10አንድ ሰው አህያ፣ በሬ፣ በግ፣ ወይም ማንኛውም እንስሳ እንዲጠበቅለት ለጎረቤቱ በዐደራ ቢሰጥና እንስሳው ቢሞት፣ ወይም ጕዳይ ቢደርስበት፣ ወይም ማንም ሳያይ ቢወሰድ፣
11ሰው በጎረቤቱ ንብረት ላይ እጁን መዘርጋቱን ወይም አለመዘርጋቱን ለመለየት፣ ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት መማል አለባቸው። ባለቤቱ ይህን ሊቀበል ይገባል፤ ሌላውም ሰው ካሣ አይክሥም።
12ነገር ግን እንስሳው ከእርፍሱ ተሰርቆ ከሆነ፣ ሌላው ሰው ለባለቤቱ ካሣ መካሥ አለበት።
13አንድን እንስሳ አውሬ ቢዘነጥለው፣ ሌላው ሰውዬ እንስሳውን ማስረጃ አድርጎ ያቅርብ። ለተዘነጣጠለው እንስሳ ካሣ መክፈል የለበትም።
14አንድ ሰው ከጎረቤቱ እንስሳ ቢዋስና እንስሳው ባለቤቱ በሌለበት ቢጎዳ ወይም ቢሞት፣ ሌላው ሰውዬ ካሣ መካሥ አለበት።
15ባለቤቱ ካለበት ከሆነ ግን፣ ሌላው ሰውዬ ካሣ መክፈል የለበትም፤ እንስሳ ተከራይቶ የነበረ ከሆነ፣ በተከራየበት ዋጋ ይከፈላል።
16አንድ ሰው ያልታጨች ልጃገረድን ቢያታልልና ዐብሯት ቢተኛ፣ ለዚህ ተገቢ የሆነውን ማጫ ከፍሎ ሚስቱ ሊያደርጋት ይገባል።
17አባቷ በሚስትነት አልሰጥህም ካለው፣ ልጃገረዶች ማጫ ከሚከፈለው ጋር እኩል የሆነ ገንዘብ መክፈል አለበት።
18መተተኛ ሴት በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድ።
19ከእንስሳት ጋር የወሲብ ግንኙነት የሚያደርግ መምት አለበት።
20ከእግዚአብሔር በቀር ለማንኛውም ባዕድ አምላክ መሥዋዕት የሚሠዋ ፈጽሞ መጥፋት ይኖርበታል።
21መጻተኛውን አትበድሉት ወይም አታስጨንቁት፤ እናንተም በግብፅ ምድር መጻተኞች ነበራችሁና።
22ማንኛዋንም መበለት ወይም አባትና እናት የሌለውን ልጁ ማስጨነቅ የለባችሁም።
23የምታስጨንቋቸው ከሆነና እነርሱም ወደ እኔ ከጮኹ፤ እኔ እግዚአብሔር ጩኸታቸውን እሰማለሁ።
24ቊጣዬ ይቀጣጠላል፤ በሰይፍም እገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ መበለታት፣ ልጆቻችሁም አባት ዐልባዎች ይሆናሉ።
25ከሕዝቤ መካከል ድኻ ከሆኑት ለአንዱ ገንዘብ ብታበድሩ፣ እንደ አራጣ አበዳሪ አትሁኑበት ወይም ወለድ አታስከፍሉት።
26የጎረቤትህን ልብስ በመያዣነት ብትወስድ፣ ፀሐይ ከመግባቷ በፊት ልትመልስለት ይገባል።
27ሰውነቱን የሚሸፍንበት ልብሱ እርሱ ብቻ ነውና። ምን ሌላ ልብስ ለብሶ መተኛት ይችላል? ወደ እኔ ሲጮኽ፣ ርኅሩኅ ነኝና እሰማዋለሁ።
28ፈራጆችንም አትስደብ፤ የሕዝብህን አለቃም አትርገም።
29ወይም ከወይን ጭማቂዎችህ የምታቀርባቸውን ስጦታዎች ማዘግየት የለብህም። የወንድ ልጆችህንም በኵር ለእኔ መስጠት አለብህ።
30በበጎችህ ላይም ይህንኑ ማድረግ ይኖርብሃል። ልጆቹ ሰባት ቀን ክአእናቶቻቸው ጋር መቆየት ይችላሉ፤ በስምንተኛው ቀን ግን ለእኔ መስጠት አለብህ።
31ለእኔ ቅዱስ ሕዝብ ትሆናላችሁ። ስለዚህ መስክ ላይ አውሬ የዘነጣጠለውን ሥጋ ለውሾች ጣሉት፣ ልትበሉት አይገባም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።