መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 21

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የምትመሠርታቸው ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፦
2አገልጋይ ብትገዛ፣ ስድስት ዓመት ያገልግልህና በሰባተኛው ዓመት ያለ ክፍያ ነጻ ይውጣ።
3ከመጣ፣ ብቻውን ነጻ ይውጣ፤ ሚስት ያገባ ከሆነ፣ ሚስቱም ዐብራው ነጻ ትውጣ።
4ጌታው ሚስት አጋብቶት ከሆነና እርሷም ወንዶች ወይም ሴቶች ልጆችን ከወለደችለት፣ ሚስቲቱና ልጆቿ የጌታዋ ይሆናሉ፤ ባልዮው ግን ብቻውን በነጻ ይሂድ።
5ግን አገልጋይ፣ “ጌታዬን፣ ሚስቴንና ልጆቼን እወድዳለሁ፤ ነጻ ወጥቼ አልሄድም” ቢል፣
6ውደ ዳኞች ይውስደው፥ ወደ በሩ ወይም ወደ መቃኑ ወስዶም ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ከዚያም አገልጋይ ጌታውን ለዘለዓለም ያገለግለዋል።
7ሰው ሴቶ ልጁን በአገልጋይነት ቢሸጣት፣ እንደ ወንዶቹ አገልጋዮች በነጻ መሄድ የለባትም።
8ለራሱ የመረጣትን ጌታዋን ደስ ባታሰኝ፣ በዎጆ ይልቀቃት። ለባዕዳን እንዲሸጣት መብት የለውም፤ ምክንያቱም አታልሎአታል።
9ለልጁ አያያዝ ያድርግለት።
10ሌላ ሚስት ቢያጋባውም፣ የመጀመሪያዋን ሚስቱን ምግብ፥ ልብስ፣ ወይም ቊሳዊ መብት ማጕደል የለበትም።
11ነገር ግን እነዚህን ሦስት ነገሮች የማይሰጣት ቢሆን፣ ያለ ምንም የገንዘብ ክፍያ በነጻ መሄድ ትችላለች።
12ሰው ሰውን ቢደበድብና ቢገድል፣ ሊሞት ይገባዋል።
13ሰውየው ዐስቦ ሳይሆን ድንገት አድርጎት ከሆነ፣ የሚሸሽበት ስፍራ አዘጋጃለሁ።
14አንድ ሰው ባልንጀራውን ሆነ ብሎ በተንኮል ቢያጠቃውና ቢገድለው፣ ከእግዚአብሔር መሠዊያም እንኳ ተወስዶ ይገደል።
15ወይም እናቱን የሚመጣ ይገደል።
16የሚጠልፍና የሚሸጥ፣ ወይም የተጠለፈው ሰው በእጁየሚገኝበት ይገደል።
17ወይም እናቱን የሚሳደብ ይገደል።
18ቢጣሉና እንደኛው ሌላውን በድንጋይ ወይም በቡጢ ቢመታው፣ የተመታው ሰውም ባይሞትና ዐልጋው ላይ ቢቀር፤
19በኋላም ቢያገግምና በትሩን ተደግፎ በአካባቢው መንቀሳቀስ ቢችል፣ ለባከነበት ጊዜ የመታው ሰውን ይክፈል፤ ያገገመበትንም በሙሉ ይክፈል። ነገር ግን ያ ሰው የነፍስ ተጠያቂ አይደለም።
20አንድ ሰው ወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን በበትር ሲመታና አገልጋዩም ከድብደባው የተነሣ ቢሞት፥ ያ ሰው መቀጣት አለበት።
21ነገር ግን አገልጋዩ አንድ ወይም ሁለት ቀን በሕይወት ቢቆይ፣ ጌታው መቀጣት የለበትም፤ አገልጋዩ የግል ንብረቱ ነውና።
22ሰዎች ቢጣሉና ነፍሰ ጡር ሴት ቢጎዱ፣ እርሷም ብትጨነግፍ፣ ሆኖም ሌላ ጉዳት ባይደርስባት፣ በደለኛው ሰውዬ የሴትዮዋ ባል የሚጠብቅበትንና ዳኞቹ የሚወስኑትን መክፈል አለበት።
23ጉዳት ካደረሰ ግን፣ ሕይወትን ለሕይወት፣
24ዐይንን ለዐይን፣ ጥርስን ለጥርስ፣ እጅን ለእጅ፣ እግርን ለእግር፣
25ቃጠሎን ለቃተሎ፣ ቊስልን ለቊስል፣ ወይም ግርፋትን ለግርፋት በቅጣት ታስከፍላለህ።
26አንድ ሰው የወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን ዐይን ቢመታና ቢያጠፋው፣ አገልጋዩን ስለ ዐይኑ ካሣ ነጻ ሊያደርገው ይገባል።
27የወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን ጥርስ ቢያወልቅ፣ አገልጋዩን ለጥርሱ ካሣ ነጻ ሆኖ እንዲሄድ ማድረግ አለበት።
28በሬ አንድን ሰው ወይም ሴት ቢወጋና የሞት አደጋ ቢያደርስ፣ በሬው በድንጋይ ይወገር፣ ሥጋውም አይበላ፤ የበሬው ባለቤት ግን ከተጠያቂነት ነጻ ይሁን።
29ግን በሬው የመዋጋት ልማድ ከቀድሞ ጀምሮ ካለበትና ባለቤቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በሬውን ሳይጠብቀው ቀርቶ፣ በሬው አንድ ወንድ ወይም ሴት ወግቶ ቢገድል፣ ያ በሬ በድንጋይ ይወገር፤ ባለቤቱም በሞት ይቀጣ።
30ለሕይወቱ ካሣ እንዲከፍል ካስፈለገ፣ የተጠየቀውን ይክፈል።
31በሬው የአንድን ሰው ወንድ ወይም ሴት ልጅ ቢወጋ፣ የበሬው ባለቤት ይህ ሕግ የሚጠብቅበትን ያድርግ።
32ወንድ ወይም ሴት አገልጋይን ቢወጋ፣ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለአገልጋዩ ጌታ መክፈልና በሬውም በድንጋይ መወገር አለበት።
33ሰው ጕድጓድ ቢከፍት ወይም ቢቆፍርና ሳይደፍነው ቀርቶ በሬ ወይም አህያ ቢገባበት፣
34ባለቤት ለጠፋው መክፈል ይኖርበታል። ለሞተው እንስሳ ባለቤት ገንዘብ መክፈል አለበት፤ የሞተው እንስሳም የእርሱ ይሆናል።
35የአንድ ሰው በሬ የሌላ ሰውን በሬ ቢወጋና ቢሞት፣ የበሬዎቹ ባለቤቶች በሕይወት ያለውን በሬ ሽጠው የተሸጠበትንና የሞተውንም በሬ ይካፈሉ።
36ነገር ግን በሬው ከቀድሞ ጀምሮ የመውጋት ልማድ ያለበት መሆኑ ከታወቀና ባለቤቱም ያልጠበቀው ከሆነ፣ በበሬው ፈንታ በሬውን መክፈል አለበት፤ የሞተው እንስሳም የእርሱ ይሆናል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።