መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 20

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እነዚህን ቃሎች እንዲህ በማለት ተናገረ፦
2ከግብፅ ምድር፣ ከባርነት ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።
3ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።
4በላይ በሰማይ ያለውን፣ ወይም በታች በምድር ያለውን፣ ከምድርም በታች በውሀ ውስጥ ያለውን የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስልና ሥዕል ለራስህ ጣዖት አታብጅ።
5አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። የሚጠሉኝን ሦስትና አራት ትውልድ በልጆች ላይ ቅጣት በማምጣት የአባቶችን ኀጢአት እቀጣለሁ።
6በሚወዱኝና ትእዛዛቴን በሚጠብቁት በሺዎች ላይ ግን የኪዳን ታማኝነት አሳያለሁ።
7የአምላክህን የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አታንሣ፤ ስሜን በከንቱ የሚያነሣውን በደል ዐልባ አላደርገውምና።
8እንድትቀድሰው፣ የሰንበትን ቀን ዐስብ።
9ቀን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አከናውን።
10ቀን ለእኔ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው። በሰንበት ቀን አንተም ወንድ ልጅህም፣ ሴት ልጅህም፣ ወንድ አገልጋይህም፣ ሴት አገልጋይህም፣ እንስሳትህም፣ በግቢህ ያለ እንግዳም ሥራ አትሠሩም።
11እግዚአብሔር ሰማያትን፣ ምድርንና ባሕርን፣ በእነርሱ ውስጥ ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀን ፈጥሬ በሰባተኛው ቀን ዐርፌአለሁና። ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባረክሁት፤ ለራሴም ቀደስሁት።
12እኔ እግዚአብሔር አምላክህ በምሰጥህ ምድር ብዙ ጊዜ እንድትቆይ፣ አባትህንና እናትህን አክብር።
13አትግደል።
14አታመንዝር።
15አትስረቅ።
16በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
17የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት፣ ወንድ አገልጋዩን፣ ሴት አገልጋዩን፣ በሬውን፣ አህያውን፣ ወይም የባልንጀራህ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትመኝ።”
18ሰዎች ሁሉ ነጎድጓዱንና መብረቁን አዩ፤ የመለከቱን ድምፅም ሰሙ፤ የሚጨሰውንም ተራራ ተመለከቱ። ሕዝቡ ይህን ሲያዩ፣ ተንቀጠቀጡ፤ ርቀውም ቆሙ።
19ሙሴን፣ “አንተ ተናገረን፤ እኛም እንሰማሃለን፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲናገረን አታድርግ፤ አለዚያ እንሞታለን” አሉት።
20ሙሴም ሕዝቡን፣ “አትፍሩ፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር በእናንተ ዘንድ እንዲገኝና ኀጢአት እንዳትሠሩ ሊፈትናችሁ እግዚአብሔር መጥቶአልና” አላቸው።
21ስለዚህ ሕዝቡ ርቀው ቆሙ፤ ሙሴም እግዚአብሔር ወዳለበት ወደ ጨለማው ተጠጋ።
22ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ይህ ነው፦ ‘እኔ ከሰማይ ከእናንተ ጋር እንደ ተነጋገርሁ እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል።
23በቀር ሌሎች አማልክትን፣ የብር ወይም የወርቅ አማልክትን ለራሳችሁ አታብጁ።
24የጭቃ መሠዊያ ሥራልኝ፣ በእርሱም ላይ የሚቃጠሉትን መሥዋዕቶችህን፣ የኅብረት መሥዋዕቶችህን፣ በጎችህንና በሬዎችህን ሠዋበት። ስሜ እንዲከበር በማደርግበት ስፍራ ሁሉ፣ ወዳንተ እመጣለሁ፤ እባርክሃለሁም።
25መሠዊያ የምትሠራልኝ ከሆነ፣ በተጠረበ በድንጋይ አትሥራው፤ ለመጥረብ ስትል መሣሪያህን በላዩ ካሳረፍህበት ታረክሰዋለህና።
26ሆነህ እንዳትጋለጥ፣ በመሠዊያዬ ላይ በደረጃ አትውጣ።”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።