መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 19

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ወር፣ እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር በወጡበት በዚያው ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ።
2ከራፊዲም ከተነሡ በኋላ፣ ወደ ሲና ምድረ በዳ መጥተው በምድረ በዳው ውስጥ ከተራራው ፊት ለፊት ሰፈሩ።
3ወደ እግዚአብሔር ወጣ። እግዚአብሔርም ከተራራው ጠርቶት እንዲህ አለው፤
4“ለያዕቆብ ቤት፣ ለእስራኤል ሕዝብ እንደዚህ ብለህ ተናገር፦ በግብፃውያን ላይ ምን እንዳደረግሁ ፣ እናንተንም በርግም ክንፎች እንዴት እንደ ተከከምኋችሁና ወደ ራሴ እንዴት እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።
5ቃሌን በታዛዥነት ብትሰሙና ኪዳኔንም ብትጠብቁ፣ ከሕዝብ ሁሉ መካከል የእኔ ርስት ትሆናላችሁ፤ ምድር ሁሉ የእኔ ነውና።
6እናንተ ለእኔ የካህናት መንግሕትና ቅዱስ ሕዝብ ትሆናላችሁ። ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ቃሎች እነዚህ ናቸው።
7መጣ፤ የሕዝቡንም ሽማግሌዎች ጠርቶ እግዚአብሔር ያዘዘውን እነዚህን ቃሎች ሁሉ በፊታቸው ተናገረ።
8ሁሉ በአንድነት፣ “እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ እናደርጋለን” በማለት መልስ ሰጡ። ሙሴ ሕዝቡ የተናገሩትን ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ መጣ።
9ሙሴን፤ “እኔ ከአንተ ጋር ስነጋገር፣ መስማት እንዲችሉና አንተንም ሁልጊዜ እንዲያምኑህ፣ ወደ አንተ በከባድ ደመና እመጣለሁ” አለው። ሙሴም ሕዝቡ የተናገሯቸውን ቃሎች ለእግዚአብሔር ነገረው።
10ሙሴን፣ “ወደ ሕዝቡ ሂድ። ዛሬና ነገ ለእኔ ቀድሳቸው፤ ልብሳቸውንም እንዲያጥቡ አድርግ።
11ቀንም ይዘጋጁ፤ በሦስተኛው ቀን እኔ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ እወርዳለሁና።
12ዙሪያ ሁሉ ለሕዝቡ ወሰን አብጅና ለሕዝቡ እንዲህ በላቸው፤ ‘ወደ ተራራው እንዳትወጡ ወይም የተራራውን ግርጌ ጫፍ እንዳትነኩ ተጠንቀቁ። ተራራውን የነካ ይሞታል።’
13ዐይነቱን ሰው ማንም አይንካው። እንዲያውም የነካው በድንጋይ ይወገራል ወይም በቀስታ ይወጋል። ሰውም ሆነ እንስሳ ይሞታል። መለከቱ የማያቋርጥ ድምፅ ሲያሰማ፣ ሕዝቡ ወደ ተራራው መውጣት ይችላሉ” አለው።
14ሙሴም ከተራራው ወደ ሕዝቡ ወረደ። ሕዝቡን ለእግዚአብሔር ቀደሳቸው፤ ልብሳቸውንም አጠቡ።
15“በሦስተኛው ቀን ተዘጋጁ፤ ወደ ሚስቶቻችሁም አትጠጉ” አላቸው።
16ቀን ጠዋት ላይ ነጏድጓድና የመብረቅ ብልጭታ፣ ከባድ ደመና እና ጉሉሕ የመለከት ድምፅ በተራራው ላይ ነበሩ። በሰፈሩ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ተንቀጠቀጡ።
17ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኙ ሕዝቡን ከሰፈር አወጣቸው፤ በተራራው ግርጌም ቆሙ።
18እግዚአብሔር በእሳትና በጢስ ወርዶበት ስለ ነበረ፣ የሲና ተራራ ሙሉ በሙሉ በጢስ ተሸፈነ። ጢሱ እንደ ምድጃ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ጠቅላላ ተራራውም በኀይል ተናወጠ።
19ድምፅ እየጨመረና እየጎላ ሲሄድ፣ ሙሴ ተናገረ፤ እግዚአብሔርም በድምፅ መለሰለት።
20እግዚአብሔር በሲና ተራራ ጫፍ ላይ ወርዶ፣ ሙሴን ወደ ተራራው ጫፍ እንዲወጣ ጠራው። ሙሴም ወጣ።
21ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለማየት ዐልፈው ወደ እኔ እንድይመጡ፣ ሂድና ሕዝቡን አስጠንቅቃቸው፤ አለዚያ ብዙዎች ይሞታሉ።
22ወደ እኔ የሚቀርቡ ካህናትም ራሳቸውን ይቀድሱ፤ እንዳላጠፋቸውም ለእኔ መምጣት ራሳቸውን ያዘጋጁ።”
23እግዚአብሔርን፣ “ሕዝቡ ወደ ተራራው መውጣት አይችሉም፤ ምክንያቱም ‘በተራራው ዙሪያ ወሰን አብጅና ለእግዚአብሔር ቀድሰው’ ብለህ አዝዘኸናል” አለው።
24ሙሴን፣ “ከተራራው ወርደህ ሂድና አሮንን ክአንተ ጋር ይዘኸው ና፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን ወሰን ዐልፈው ወደ እኔ እንዲመጡ አትፍቀድላቸው፤ አለዚያ አጠፋቸዋለሁ” አለው።
25ስለዚህ ሙሴ ወደ ሕዝቡ ሄዶ ይህንኑ ነገራቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።