1የእስራኤል ማኅበር አባላት ከኤሊም ተንሥተው፣ ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ወር ዐሥራ አምስተኛ ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወዳለው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ።
2በዳው ውስጥም ጠቅላላ የማኅበሩ አባላት በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ።
3ሙሴንና አሮንንም፣ “በሥጋ ምንቸቶች ዙሪያ ተቀምጠን እስክንጠግብ ምግብ በምንበላበት በግብፅ ምድር በእግዚአብሔር እጅ ምነው በሞትን ኖሮ፤ ከዚያ አውጥታችሁ ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁን መላውን ማኅበራችንን በረኃብ ልትጨርሱ ነውና” አሏቸው።
4ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እንጀራ ከሰማይ አዘንብላችኋለሁ። በሕጌ የሚመሩ ወይም የማይመሩ መሆናቸውን እንድፈትናቸው፣ ሕዝቡ ይውጡና በየቀኑ ለአንድ ቀን የሚሆነውን ይሰብስቡ።
5ቀን በየቀኑ ከሚሰበስቡት ዕጥፍ ይሰብስቡ፤ ያመጡትንም ያዘጋጁ።”
6ከዚያም ሙሴና አሮን ለእስራኤል ሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አሉ፤ “ከግብፅም ምድር ያወጣችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ማታ ታውቃላችሁ።
7በእርሱ ላይ ያጕረመረማችሁትን ሰምቶአልና፣ የእግዚአብሔርንም ክብር ጠዋት ታያላችሁ። በእኛ ላይ ልታጕረመርሙ እኛ ለእናንተ ምንድን ነን?”
8ደግሞ እንዲህ አለ፤ በእርሱ ላይ ያጕረመረማችሁትን ሰምቶታልና፣ እግዚአብሔር ማታ ሥጋ፣ ጠዋትም ምግብ እስክትጠግቡ ሲሰጣችሁ፣ ይህን ታውቁታላችሁ። አሮንና እኔ ምንድን ነን? የምታጕረመርሙት በእኛ ላይ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ላይ ነው።”
9ሙሴ አሮንን፣ “‘ጕርምርምታችሁን ሰምቶታልና ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ’ በልህ ለእስራኤል ሕዝብ ማኅበር ሁሉ ተናገር’” አለው።
10አሮን ለእስራኤል ሕዝብ ማኅበር ሁሉ እንደ ተናገረ፣ ወደ ምድረ በዳው ተመለከቱ፤ እነሆም፣ የእግዚአብሔር ክብር በደመናው ውስጥ ታየ።
11እግዚአብሔርም ለሙሴ እንዲህ ብሎ ነገረው፤
12“የእስራኤልን ሕዝብ ጕርምርምታ ሰምቻለሁ። እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ማታ ሥጋ ትበላላችሁ፤ ጠዋት ደግሞ እንጀራ ትበሉና ትጠግባላችሁ። ከዚያም በኋላ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።
13ላይ ድርጭቶች መጡና ሰፈሩን ሸፈኑት። በጠዋቱም የሰፈሩን ዙሪያ ጤዛ ተኝቶበታል።
14ሲጠፋ፣ እንደ ዐመዳይ ያለ ስስ ቅርፊት በምድረ በዳው ላይ ታየ።
15ሰዎች ሲያዩት፣ አንዳቸው ለአንዳቸው፣ “ምንድን ነው?” ተባባሉ። ምን እንደ ነበረ አላወቁም። ሙሴም እንዲህ አላቸው፤ “ይህ እንድትበሉት እግዚአብሔር የሰጣችሁ እንጀራ ነው።
16እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ሰጥቶአል፦ ‘ለመብላት የምትፈልጉትን መጠን በሕዝባችሁ ቊጥር ለያንዳንዱ ሰው አንድ ጎሞር ሰብስቡ። የምትሰበስቡት እንደዚህ ነው፦ በድንኳናችሁ ውስጥ ለሚኖር ለእያንዳንዱ ሰው ለመብላት የሚበቃውን ሰብስቡ።”
17የተነገራቸውን አደረጉ። አንዳንዶች የበለጠ፣ አንዳንዶችም ያነሰ ሰበሰቡ።
18በጎሞር መጠን ሲለኩት፣ ብዙ የሰበሰቡት የተረፈ አላገኙም፤ ትንሽ የሰበሰቡትም ያጡትናየጎደለባቸው አልነበረም። እያንዳንዱ ሰው የሰበሰበው ለፍላጎቱ የሚበቃውን ያህል ነበር።
19“ማንም ሰው ለነገ ከእርሱ ምንም ማስተረፍ የለበትም” አላቸው።
20ግን ሕዝቡ ሙሴን አልሰሙትም። አንዳንዶቻቸው ከሰበሰቡት እስከሚቀጥለው ጠዋት የተወሰነ አስቀሩ፤ ያስቀሩት ምግብ ግን ተላ፣ ሸተተም። ሙሴ ተቆጣቸው።
21የሰበሰቡት ጠዋት ጠዋት ነበር። እያንዳንዱ ሰው ለቀኑ የሚበቃውን ሰበሰበ። ፀሐይ ስትሞቅ ቀለጠ።
22ቀን ለያንዳንዱ ሰው ሁለት ሁለት ጎሞር እንጀራ አድርገው ዕጥፍ ሰበሰቡ። የማኅበረ ሰቡ አለቆችም በሙሉ መጥተው ለሙሴ ነገሩት።
23“እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል፦ ‘ነገ ፍጹም ዕረፍት፣ ለእግዚአብሔር ክብር የተቀደሰ ሰንበት ነው። መጋገር የምትፈልጉትን ጋግሩ፤ መቀቀል የምትፈልጉትንም ቀቅሉ። ተርፎ የሚቀረውን ሁሉ እስከ ጠዋት ለራሳችሁ አስቀምጡት’” አላቸው።
24የተረፈውን ሙሴ በነገራቸው መሠረት እስከ ጠዋት አቆዩት። አልሸተተም፤ ትልም አልነበረበትም።
25እንዲህ አለ፤ “ዛሬ እግዚአብሔርን ለማክበር የተቀደሰ ሰንበት ነውና፣ ያስተረፋችሁትን ያን ምግብ ዛሬ ብሉት። ዛሬ ሜላ ላይ አታገኙትም።
26ቀኖች ትሰበስቡታላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን የሰንበት ቀን ነው። በሰንበት ቀን መና የለም።”
27ቀን አንዳንዶች መና ሊሰበስቡ ወጡ፣ ነገር ግን ምንም አላገኙም።
28ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ትእዛዛቴንና ሕገጋቴን ለመጠበቅ እንቢ የምትሉት እስከ መቼ ነው?
29በሉ፤ እግዚአብሔር ሰንበትን ሰጥቶአችኋል። ስለዚህ በስድስተኛው ቀን የሰጣችሁ ለሁለት ቀን የሚሆን እንጀራ ነው። ከእናንተ እያንዳንዱ በገዛ ስፍራው ይቆይ፤ በሰባተኛው ቀን ማንም ሰው ከስፍራው መውጣት የለበትም።”
30በሰባተኛው ቀን ዐረፉ።
31ምግቡን “መና” ብለው ጠሩት። ምግቡም እንደ ድንብላል ዘር ነጭ፣ ጣዕሙም በማር በስሱ እንደ ተጋገረ ቂጣ ነበረ።
32ሙሴም፣ “እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፦ ‘ከግብፅ ምድር ካወጣኋችሁ በኋላ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን እንጀራ ልጆቻችሁ ማየት እንዲችሉ፣ አንድ ጎመር መና ለትውልዶቻችሁ ሁሉ ይቀመጥ” አለ።
33አሮንን፣ “አንድ ማሰሮ ውሰድና አንድ ጎሞር መና አስቀምጥበት፤ ለትውልዶች ሁሉ ተጠብቆ እንዲቆይም በእግዚአብሔር ፊት አስቀምጠው” አለው።
34ሙሴን ባዘዘው መሠረት፣ አሮን መናውን በምስክሩ ፊት አስቀመጠው።
35ወደሚኖሩበት ምድር እስከሚመጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ። ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስከሚመጡ ድረስ የተመገቡት እርሱን ነው።
36አንድ ጎመር የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ነው።