መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 17

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእስራኤል ማኅበር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመከተል ከሲን ምድረ በዳ ተነሡ፤ በራፊዲምም ሰፈሩ፤ ነገር ግን ሕዝቡ የሚጠጡት ውሀ አልነበረም።
2ሕዝቡ ሙሴን ወቀሡት፤ “የምንጠጣው ውሀ ስጠን” ብለውም ተናገሩት። ሙሴም፣ “ለምን እኔን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ?” አላቸው።
3ያ ሕዝቡ ውሀ በጣም ጠምቷቸው ስለ ነበር በሙሴ ላይ አጕረመረሙ። እንዲህም አሉት፤ “እኛንና ልጆቻችንን፣ ከብቶቻችንንም በውሀ ጥም ለመፍጀት ከግብፅ ለምን አወጣኸን?”
4እነዚህን ሰዎች ምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ? በድንጋይ ሊወግሩኝ ተዘጋጅተዋል” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
5እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች አንዳንዶችን፣ ወንዙን የመታህበትንም በትር ያዝና ከሕዝቡ ፊት ቀድመህ ሂድ።
6ኮሬብ ባለው ዐለት ላይ እኔ ከፊትህ እቆማለሁ፤ ዐለቱንም ትመታዋለህ። ከእርሱም ሕዝቡ የሚጠቱት ውሀ ይወጣል።” ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት የታዘዘውን አደረገ።
7ስላጕረመረሙና “እግዚአብሔር በመካከላችን አለ ወይስ የለም?” በማለት እግዚአብሔርን ስለ ተፈታተኑት ያን ስፍራ ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው።
8መጥተው እስራኤልን ራፊዲም ላይ ወጉ።
9ስለዚህም ሙሴ ኢያሱን፣ “ጥቂት ሰዎችን ምረጥና ውጣ፤ ከአማሌቃውያን ጋርም ተዋጋ። ነገ እኔ የእግዚአብሔን በትር ይዤ በኮረብታው ዐናት ላይ እቆማለሁ” አለው።
10ሙሴ ባዘዘው መሠረት አማሌቃውያን ተዋጋቸው፤ ሙሴ፣ አሮንና ሖርም ወደ ኮረብታው ዐናት ወጡ።
11እጁን ወደ ላይ ሲያነሣ፣ እስራኤላውያን ድል ያደርጉ ነበር፤ እጁን ሲያወርድ ግን አማሌቃውያን ለማሸነፍ ይጀምሩ ነበር።
12የሙሴ እጆች እየደከሙ ሲሄዱ፣ አሮንና ሖር ድንጋይ ወስደው እንዲቀመጥበት ከእርሱ ሥር አስቀመጡለት። በዚያውም ጊዜ አሮንና ሖር አንዳቸው በአንድ ጎኑ፣ የቀረውም በሌላው ጎኑ በኩል በመሆን የሙሴን እጆች ወደ ላይ ደግፈው ያዙ። የሙሴ እጆችም ፀሐይ እስክትገባ ድረስ ጠንክረው ቆዩ።
13ስለዚህም ኢያሱ አማሌቃውያንን በሰይፍ ድል አደረጋቸው።
14እግዚአብሔር ሙሴን፣ “የአማሌቃውያንን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ሙሉ በሙሉ ስለምደመስስ፣ ይህን በመጽሐፍ ጽፈህ ኢያሱ እየሰማ አንብበው” አለው።
15ሙሴም መሠዊያ ሠርቶ፣ “እግዚአብሔር አርማዬ ነው” ብሎ ሰየመው።
16“እጅ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ተነሥቶአልና፣ እግዚአብሔር በአማሌቃውያን ላይ ከትውልድ እስከ ትውልድ ጦርነት ያደርጋል” አለ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።