መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 15

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ሕዝብ ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ውስጥ ጥሎአል።
2ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም ሆኖልኛል። እርሱ አምላኬ ነው፣ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፣ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
3ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።
4ሠረገሎችና ሠራዊት በባሕር ውስጥ ጥሎአል። የፈርዖን ምርጥ መኮንኖች በቀይ ባሕር ውስጥ ሰመጡ።
5ማዕበሎቹ ሽፈናቸው፤ እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቆቹ ወረዱ።
6እግዚአብሔር ሆይ፣ ቀኝ እጅህ ጠላትን ሰባበረ።
7ላይ የተነሡትን በታላቅ ግርማ ገለበጥሃቸው። ቊጣህን ላክህ፤ እንደ ገለባም አርጎ በላቸው።
8በአፍንጫህ እስትንፋስ ውሆች ተከመሩ፤ ፈሳሾች እንደ ክምር ቆሙ፤ የጥልቁ ውሃ በባሕሩ ውስጥ ረጋ።
9ጠላት፣ ‘አሳድዳቸዋለሁ፣ እይዛቸዋለሁ፣ ምርኮም እካፈላለሁ፤ ፍላጎቴ በእነርሱ ርዳታ ያገኛል፤ ሰይፌን እመዝዛለሁ፤ እጄም ታጠፋቸዋለች’ አለ።
10ግን በነፋስህ እፍ አልህ፣ ባሕሩም ሸፈናቸው፤ በኀይለኛ ውሆች ውስጥ እንደ ብረት ሰመጡ።
11ሆይ፣ ክአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና የከበረ፣ ተአምራትን በማድረግ በምስጋና ከፍ ያለ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
12እጅህን ዘረጋህ፤ ምድርም ዋጠቻቸው።
13ፍቅርህ የታደግሃቸውን ሕዝብህን መራህ። በብርታትህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ መራሃቸው።
14ይሰማሉ፣ ይንቀጠቀጣሉም፤ የፍልስጥኤምን ኗሪዎች ሽብር ይይዛቸዋል።
15ጊዜ የኤዶም እለቆች ይደነግጣሉ፤ የሞዓብ መሪዎች ይርበደበዳሉ፤ የከነዓን ኗሪዎች ሁሉ ይቀልጣሉ።
16ሆይ፣ ሕዝብህ እስከሚያልፉ፣ የታደግሃቸው ሕዝብህ ዐልፈው እስከሚሄዱ ድረስ፣ ሽብርና ድንጋቴ ይወድቅባቸዋል፤ ከክንድህ ብርታት የተነሣ፣ እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ።
17ሆይ፣ ማደሪያህ ባደረግኸው ስፍራ፣ ጌታችን ሆይ፣ እጆችህ በሠሩት መቅደስ፣ በርስትህ ተራራ ላይ ሕዝብህን ታመጣቸዋለህ፣ ትተክላቸዋለህም።
18ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል።”
19ፈረሶች ከሠረገሎቹና ከፈረሰኞቹ ጋር ወደ ባሕሩ ውስጥ ሲገቡ፣ እግዚአብሔር የባሕሩን ውሀ መልሶ በላያቸው አመጣባቸው። እስራኤላውያን ግን በባሕሩ መካከል በደረቅ መሬት ሄዱ።
20ይአሮን እኅት፣ ነቢይቱ ማርያም ከበሮ አነሣች፤ ሌሎቹ ሴቶችም በሙሉ ከበሮ ይዘው ከእርሷ ጋር እያሸበሸቡ ወጡ።
21“ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ውስጥ ጥሎአል፤ በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና፣ ለእግዚአብሔር ዘመሩ” እያለች ዘመረችላቸው።
22ሙሴ እስራኤላውያንን ከቀይ ባሕር እየመራቸው ወደ ሱር ምድረ በዳ ሄዱ። በምድረ በዳው ውስጥ ሦስት ቀን ሲጓዙ ውሀ አላገኙም።
23ማራም ደረሱ፤ ነገር ግን እዚያ የሚገኘው ውሀ መራራ ስለ ነበረ ሊጠጡት አልቻሉም። ቦታውን ማራ ያሉት ከዚህ የተነሣ ነው።
24ሕዝቡ፣ “ምን እንጠጣ?” ብለው በሙሴ ላይ አጕረመረሙ።
25ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፣ እግዚአብሔርም አንድ ዛፍ አሳየው። ሙሴም የዛፉን ዕንጨት ወደ ውሀው ውስጥ ጣለው፣ ውሀውም ጣፋጭ ሆነ። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሕግና ሥርዐት የሰጣቸውና የፈተናቸው በዚያ ስፍራ ነበር።
26እንዲህ አለ፤ “የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ድምፅ በጥንቃቄ ብትሰሙ፥ ትክክለኛ የሆነውንም በፊቱ ብታደርጉ፣ ትእዛዛቱንም ብታስተውሉና ሕግጋቱን ሁሉ ብትጠብቁ፣ ግብፃውያን ላይ ካመጣኋቸው በሽታዎች አንዱንም በእናንተ ላይ አላመጣም፤ እኔ ፈዋሻችሁ እግዚአብሔር ነኝና።”
27በኋላ ሕዝቡ ዐሥራ ሁለት ምንጮችና ሰባ የዘንባባ ዛፎች ወደ ነበሩበት ወደ ኤሊም መጡ። በዚያም በውሀው አጠገብ ሰፈሩ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።