መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 14

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ለሙሴ እንዲህ ብሎ ተናገር፤
2በሚግዶልና በባሕሩ መካከል ባለው በፊሀሒሮት ፊት፣ በበኣልዛፎንም አንጻር እንዲሰፍሩ ለእስራኤላውያን ንገር። በፊሀሒሮት ትይዩ በባሕሩ አጠገብ ትሰፍራላችሁ።
3ፈርዖን ስለ እስራኤላውያን፣ ‘በምድሪቱ እየተንከራተቱ ነው፤ ምድረ በዳውም ዘግቶባቸዋል’ ይላል።
4የፈርዖንን ልብ እኔ አደነድነዋለሁ፤ እርሱም እስራኤላውያንን ይከታተላቸዋል። በፈርዖንና በመላው ሰራዊቱ ምክንያት እኔ እከብራለሁ። ግብፃውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።” ስለዚህ እስራኤላውያን በተነገራቸው መሠረት ሰፈሩ።
5ንጉሥ እስራኤላውያን እንደ ሄዱ ሲነገረው፣ ፈርዖንና አገልጋዮቹ ሐሳባቸውን በመለወጥ፣ እስራኤላውያን ለእኛ ከመሥራት ነጻ ሆነው እንዲሄዱ መፍቀዳችን ምን ማድረጋችን ነው? አሉ።
6ሠረገላዎቹ እንዲዘጋጁለት አደረገ፤ ሰራዊቱንም ከእርሱ ጋር ይዞ ሄደ።
7መቶ ምርጥ ሠረገሎችንና የግብፅን ሌሎች ሠረገሎች በሙሉ፣ በያንዳንዳቸው ላይ መኮንኖች ያሉባቸውን ይዞ ተንቀሳቀሰ።
8እግዚአብሔር የግብፅን ንጉሥ፣ የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው፣ ንጉሡ እስራኤላውያንን ተከታተላቸው። አሁን እስራኤላውያን በድል ወጥተው ሄደዋል።
9ነገር ግን ግብፃውያን፣ ሁሉም የፈርዖን ፈረሶችና ሠረገሎች፣ የፈርዖን ፈረሰኞችና ሰራዊቱ እስራኤላውያንን አሳደዷቸው። በበኣልዛፎን አንጻር በባሕሩ አጠገብ ፊሀሒሮት ጥግ ሰፍረው እንዳሉ ደረሱባቸው።
10ፈርዖን በቀረ ጊዜ፣ እስራኤላውያን ወደ ላይ ተመለከቱ፣ ተደነቁም። ግብፃውያን ከኋላ እየተከተሏቸው ነበርና ፈሩ። እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
11እንዲህ አሉት፤ “እዚህ ያመጣኸንና በምድረ በዳ እንድንሞት ያደረግኸው በግብፅ መቃብር ታጥቶ ይህን ነግረንህ አልነበረምን?
12ሠራተኞች እንድንሆን ተወን’ ብለንህ ነበር። በምድረ በዳ ከምንሞት፣ ለእነርሱ ሠራተኞች ሆነን ብንቀር ይሻል ነበር።’”
13እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ። ጸንታችሁ ቁሙና ዛሬ እግዚአብሔር ለእናንተ የሚያደርግላችሁን ትድግና ታያላችሁ። ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ዳግም አታዩአቸውም።
14እግዚአብሔር ለእናንተ ይዋጋል፤ እናንተ መታገሥ ብቻ ነው ያለባችሁ።”
15እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተ ሙሴ ለምን ትጮኽብኛለህ? እስራኤላውያን ወደ ፊት እንዲሄዱ ንገራቸው።
16የእስራኤል ስዎች በባሕሩ ውስጥ በደረቅ መሬት እንዲሻገሩ በትርህን አንሣና እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርግተህ ለሁለት ክፈለው።
17ተከትለዋቸው እንዲገቡ እኔ የግብፃውያንን ልብ የማደነድን መሆኔን ዕወቅ። ከፈርዖንና ከሰራዊቱ ሁሉ፣ ከሠረገሎቹና ከፈረሰኞቹ የተነሣ እኔ እከብራለሁ።
18በፈርዖን፣ ሠረገሎቹና በፈረሰኞቹ ምክንያት ክብርን ሳገኝ፣ ግብፃውያኑ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”
19ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ በስተ ኋላቸው ሄደ። የደመናውም ዐምድ ከፊታቸው ተንቀሳቅሶ በስተኋላቸው ሄዶ ቆመ።
20በግብፅ ሰራዊትና በእስራኤል መካከል መጣ። ለግብፃውያን የጨለማ ደመና ሲሆን፣ ለእስራኤላውያን ግን ሌሊቱን ብሩህ ያደረገ ደመና ነበር፤ ይህም ሌሊቱን ሙሉ አንደኛው ወገን ወደ ሌላው እንዳይጠጋ አደረገ።
21እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ። እግዚአብሔርም በዚያ ሌሊት ባሕሩን በብርቱ የምሥራቅ ነፋስ ወደ ኋላ እንዲሄድ በማድረግ ባሕሩን ደረቅ መሬት አደረገው። በዚህ መንገድ ውሃው ተከፈለ።
22እስራኤላውያን በባሕሩ መካከል ገብተው በደረቅ መሬት ዐለፉ። ውሃው በቀኛቸውና በግራቸውና በኩል ግድግዳ ሆነላቸው።
23ተከታትለዋቸው መጡ። እነርሱ፣ የፈርዖን ፈረሶች ሠረገሎችና ፈረሰኞች ሁሉ እስራኤላውያኑ ተከትለው በባሕሩ መካከል ገቡ።
24ላይ እግዚአብሔር በእሳቱና በደመናው ዐምድ ውስጥ የግብፃውያንን ሰራዊት ወደ ታች ተመለከተ። በግብፃውያን መካከልም ሽብር እንዲፈጠር አደረገ።
25የሠረገሎቻቸው መንኯራኵሮች ተቆላለፉ፤ ፈረሰኞችም ለመንቀሳቀስ እጅግ ተቸገሩ። ስለዚህ ግብፃውያኑ፣ እግዚአብሔር እኛን እየወጋላቸው ነውና፣ ከእስራኤል እንሽሽ” አሉ።
26ሙሴን፣ “ውሃው በግብፃውያኑ፣ በሠረገሎቻቸውና በፈረሰኞቻቸው ላይ ተመልሶ እንዲመጣባቸው እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርጋ” አለው።
27እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ ንጋት ላይም ባሕሩ ወደ ተለመደ ስፍራው ተመለሰ። ግብፃውያኑ ከባሕሩ ሸሹ፤ እግዚአብሔር ግን ወደ ባሕሩ መካከል አስገባቸው።
28ውሃው ተመስሎ በመምጣት የፈረዖንን ሠረገሎች፣ ፈረሰኞችን ሠረገሎቹን ተከትለው ወደ ባሕሩ የገቡትን ጠቅላላ ሰራዊቱን ሸፈናቸው። አንድም ሳይሰምጥ የቀረ አልነበረም።
29ግን በባሕሩ መካከል በደረቅ መሬት ላይ ተራምደው ሄዱ። ውሃው በቀኛቸውም በግራቸውም በኩል ለእነርሱ ግድግዳ ሆናላቸዋል።
30እግዚአብሔር በዚያ ቀን እስራኤላውያንን ከግብፃውያን እጅ ታደጋቸው፤ እስራኤላውያኑም የግብፃውያኑን ሬሳ በባሕሩ ዳር አዩ።
31እግዚአብሔር በግብፃውያኑ ላይ የገለጠውን ታላቅ ኀይል ሲያዩ፣ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አከበሩ፣ በእግዚአብሔርና በአገልጋዩ በሙሴም ታመኑ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።