መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 13

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሙሴን እንዲህ አለው፤
2‘በእስራኤላውያን ዘንድ ከሰውም ሆነ ከእንስሳት በመጀመሪያ የተወለደውን ወንድ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ። በኵር የእኔ ነው።”
3ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁበትን ይህን ቀን አስታውሱት፤ በዚህ ቀን እግዚአብሔር በብርቱ እጁ ከዚህ ስፍራ አውጥቶአችኋልና። እርሾ ያለበት ምግብ አይበላም።
4በዚህ ቀን፣ በአቢብ ወር ከግብፅ ወጥቷችኋል።
5ለእናንተ ለመስጠት ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው፣ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው፣ ወደ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ አሞራውያን፣ ኤውያውያን፣ ኢያቡሳውያን ምድር እግዚአብሔር ሲያስገባችሁ፣ ይህን አምልኮ በዚህ ወር ትፈጽማላችሁ።
6ቀን ቂጣ ትበላላችሁ፤ በሰባተኛውም ቀን እግዚአብሔርን የምታከብሩበት በዓል ይሆናል።
7ቀን ሁሉ መበላት ያለበት ቂጣ ነው፤ እርሾ ያለበት እንጀራ በእናንተ ዘንድ መታየት የለበትም። በአዋሳኞቻችሁም ዘንድ እርሾ አይኑር።
8ቀን፣ ‘ይህ እንዲህ የሚሆነው ከግብፅ ስወጣ እግዚአብሔር ለእኔ ካደረገው የተነሣ ነው’ ብላችሁ ለልጆቻችሁ ትነግሯቸዋላችሁ።’
9ይህም በእጃችሁና በግንባራችሁ ላይ መታሰቢያ ይሆናል። ይኸውም እግዚአብሔር በብርቱ እጁ ከግብፅ ስላወጣችሁ፣ የእግዚአብሔር ሕግ በአፋችሁ እንዲሆን ነው።
10ይህን ሕግ በየዓመቱ በተወሰነለት ጊዜ ልትጠብቁት ይገባል።
11ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በማለው መሠረት፣ እግዚአብሔር ወደ ከነዓናውያን ምድር ሲያስገባችሁ፣
12በመጀመሪያ የተወሰደውን፣ የእንስሶቻችሁንም በኵር ሁሉ ለእግዚአብሔር ቀድሱ። ወንዶች የእግዚአብሔር ናቸው።
13ከአህያ በመጀመሪያ የተወለደውን ሁሉ በጠቦት ትዋጁታላችሁ። ካልዋጃችሁት፣ ዐንገቱን ስበሩት። ከወንድ ልጆቻችሁ መካከል በኵር የሆኑትን ሁሉ ዋጇቸው።
14ልጅህ፣ ‘ይህ ምን ማለት ነው? ብሎ ወደፊት ቢጠይቅህ፣ እንደዚህ ትነግረዋለህ ‘ከባርነት ቤት፣ ከግብፅ እግዚአብሔር ያወጣን በብርቱ እጅ ነበር።
15እኛን ለመልቀቅ በግትርነት እንቢ ባለ ጊዜ፣ እግዚአብሔር በግብፅ ምድር ያለውን በኵር ሁሉ፣ የሰውንም ሆነ የእንስሳትን በኵር በሙሉ ገደለ። ከእንስሳት ሁሉ በመጀመሪያ የተወለደውን ለእግዚአብሔር የምሠዋውና ከወንድ ልጆችም በኵር የሆነውን የምዋጀውን በዚህ ምክንያት ነው።’
16ከግብፅ ያወጣን በብርቱ እጅ ነውና፣ ይህ በእጅህና በግንባር ላይ ማስታወሻ ይሆናል።”
17ሕዝቡን ሲለቅቃቸው፣ እግዚአብሔር ምንም እንኳ ቅርብ ቢሆንም፣ በፍልስጥኤማውያን ምድር ባለው መንገድ አልመራቸውም። እግዚአብሔር፣ “ሕዝብ ጦርነት ቢያጋጥማቸው፥ ምናልባት ሐሳባቸውን ይለውጣሉ፣ ወደ ግብፅም ይመለሳሉ” ብሎ ነበርና።
18እግዚአብሔር ሕዝቡን በምድረ በዳው ዙሪያ ውደ ቀይ ባሕር መራቸው። እስራኤላውያን ለውጊያ ተዘጋጅተው ከግብፅ ምድር ወጥተው ሄዱ፣
19ሙሴ የዮሴፍን ዐፅም ይዞ ሄደ፤ ምክንያቱም ዮሴፍ፣ “እግዚአብሔር በእርግጥ ይታደጋችኋልና ዐፅሜን ይዛችሁ እንድትሄዱ” በማለት እስራኤላውያንን አስምሎአቸው ነበር።
20ከሱኮት በመጓዝ ምድረ በዳው ዳር ላይ በሚገኘው በአታም ሰፈሩ።
21እግዚአብሔር ሕዝቡን በመንገድ ላይ ሊመራቸው ቀን ቀን በደመና ዐምድ በፊታቸው ሄደ። ሌሊት ሌሊት ደግሞ ብርሃን ሊሰጣቸው በእሳት ዐምድ ሄደ። በዚህ ዐይነት ሕዝቡ በቀንም በሌሊትም መጓዝ ቻሉ።
22እግዚአብሔር የቀኑን የደመና ዐምድ ወይም የሌሊቱን የብርሃን ዐምድ ከሕዝቡ ፊት አላነሣም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።