መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 12

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በግብፅ ምድር ለሙሴና ለአሮን እንዲህ ብሎ ነገራቸው፤
2ወር ለእናንተ የወሮች መጀመሪያ፣ የዓመቱም የመጀመሪያ ወር ይሁናችሁ።
3ጉባኤ ይህን ንገሩ፤ ‘በዚህ ወር ዐሥረኛ ቀን ላይ እያንዳንዳቸው ለራሳቸው አንድ ጠቦት የሚያንስ ከሆነ፣
4የቅርብ ጎረቤቱ ከቊጥራቸው ጋር የሚመጣጠን ጠቦት ያዘጋጁ። የሚመገቡትን በቂ ሥጋ መውሰድ እንዲችሉ፣ ጠቦቱ ለሁሉም የሚበቃ መሆን አለበት።
5ወይም የፍየል ጠቦታችሁ እንከን የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ሊሆን ይገባል። ከበጎቹ ወይም ከፍየሎቹ አንዱን ልትወስዱ ትችላላችሁ።
6እስከ ወሩ ዐሥራ አራተኛ ወር ድረስ አቆዩአቸው። ከዚያም መላው የእስራኤል ጉባኤ እነዚህን እንስሳት ፀሐይ ስትጠልቅ ይረዷቸው።
7ከዚያም ከደሙ ጥቂት ውሰዱና ሥጋውን በምትበሉበት ቤት በር መቃንና ጉበን ላይ አድርጉት።
8በእሳት ከጠበሳችሁት በኋላ፣ በዚያው ሌሊት ከቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ብሉት።
9ወይም ቅቅሉን አትብሉት። ይልቁን ከጭንቅላቱ፣ ከእግሮቹና ከሆድ ዕቃው ጋር በእሳት ጠብሳችሁ ብሉት።
10ድረስ ከሥጋው አንዳችም አታስቀሩ። የተራረፈ ነገር ቢኖር፣ በእሳት ይቃጠል።
11ወገባችሁን ታጥቃችሁ፣ ጫማችሁን አጥልቃችሁና በትራችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ ነው። ተጣድፋችሁ ልትበሉት ይገባል። የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው።
12በዚያ ሌሊት በግብፅ ምድር ሁሉ ዐልፋለሁ፤ በግብፅ ምድርም የሰውንና የእንስሳትን በኵር በሙሉ እመታለሁ። በግብፅ አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
13ደሙ እኔ ወደ እናንተ በቤቶቻችሁ ላይ ምልክት ይሆናል። ደሙንም በማይበት ጊዜ የግብፅን ምድር ስመታ እናንተን ዐልፌአችሁ እሄዳለሁ። ይህ መቅሠፍት በእናንተ ላይ አይመጣም፤ አያጠፋችሁምም።
14ቀን የእግዚአብሔር በዓል ቀን አድርጋችሁ የምታከብሩት የመታሰቢያ ቀን ይሆንላችኋል። ቀኑን እንድታከብሩት ለእናንተ፣ ለትውልዶቻችሁም ሁሉ ቋሚ ሥርዐት ይሆናችኋል።
15ቀን ቂጣ ትበላላችሁ። በመጀመሪያው ቀን እርሾውን ከቤታችሁ ታስወግዳላችሁ። ከመጀመሪያው ቀን እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የበላ ሰው ሁሉ ከእስራኤል ይወገድ።
16በመጀመሪያው ቀን ለእኔ የተቀደሰ ጉባኤ ይደረጋል፤ በሰባተኛውም ቀን እንደዚሁ ያለ ሌላ ጉባኤ ይሆናል። ሁሉም የሚበላውን ከመቀቀል በቀር፣ በእነዚህ ቀኖች ሥራ አይሠራም። የምትሠሩት የምግብ ዝግጅቱን ሥራ ብቻ ነው።
17በዓልን አክብሩት ምክንያቱም ሕዝባችሁን ሰራዊት በሰራዊት አድርጌ ከግብፅ ምድር ያወጣሁት በዚህ ቀን ነው። ስለዚህ ይህን ቀን በትውልዶቻችሁ ሁሉ አክብሩት፤ ለእናንተ ቋሚ ሥርዓት ይሆናችኋል።
18የመጀመሪያ ወር ዐሥራ አራተኛ ቀን ፀሐይ መጥለቅ አንሥቶ፣ እስከ ወሩ ሃያ አንደኛ ቀን ፀሐይ መጥለቅ ድረስ ቂጣ ትበላላችሁ።
19በሰባቱ ቀኖች በቤታችሁ ውስጥ እርሾ መገኘት የለበትም። እርሾ ያለበት እንጀራ የሚበላ እንግዳም ሆነ በምድራችሁ የተወለደ ሰው ከእስራኤል ማኅበረ ሰ ይወገዳል።
20የተጋገረ አንዳችም መብላት የለባችሁም። የትም ብትኖሩ፣ መብላት የሚገባችሁ እርሾ የሌለበትን ነው።”
21በኋላ ሙሴ የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ሂዱና ቤተ ሰቦቻችሁን ለመመገብ የሚበቁ ጠቦቶችን ወይም ግልገሎችን መርጣችሁ የፋሲካን በግ ዕረዱ።
22ጭብጥ የሂሶጵ ቅጠል ያዙና በሳሕን ውስጥ በሚቀመጠው ደም ውስጥ በመንከር፣ የቤታችሁን ጉበን ዐናትና ሁለቱን መቃኖች እርጩ። እስኪነጋ ድረስ ከእናንተ አንድም ከቤቱ አይወጣ።
23ለመቅሠፍት እግዚአብሔር ስለሚያልፍ፣ ደሙን በጉበኑ ዐናትና በሁለቱ መቃኖች ላይ ሲያይ፣ በበራፋችሁ ላይ ያልፋል፣ ቀሣፊውም ወደ ቤታችሁ እንዲገባና እናንተን እንዲቀሥፋችሁ አይፈቅድም።
24ይህ ሥርዐት ለእናንተም ለልጆቻችሁም የሁልጊዜ ሥርዐት ስለ ሆነ ልታከብሩት ይገባል።
25ቃል በገባላችሁ መሠረት፣ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፣ ይህን የአምልኮ ሥርዐት ጠብቁት።
26‘ይህ የአምልኮ ሥርዐት ምን ትርጕም አለው?’ ብለው በሚጠይቋችሁ ጊዜ፣
27እንደዚህ ብላችሁ ልትነግሯቸው ይገባል፤ ‘ይህ የእግዚአብሔር ፋሲካ መሥዋዕት ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ግብፃውያንን ሲቀሥፍ፣ በግብፅ ውስጥ በእስራኤላውያን ቤቶች ዐልፎ ሄዶአል። ቤተ ሰቦቻችንን ነጻ አውጥቷቸዋል።” ከዚያም ሕዝቡ ሰገዱ፣ እግዚአብሔርንም አመለኩት።
28ሄደው እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዝዛቸው አደረጉ።
29እኩለ ሌሊት ላይ በዙፋኑ ላይ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኵር ልጅ ጀምሮ፣ በእስር ቤት ውስጥ እስካለው ሰው በኵር ልጅና እስከ እንስሳት በኵር ሁሉ ድረስ፣ እግዚአብሔር በግብፅ ምድር የሚገኝን በኵር በሙሉ ቀሠፈ።
30አገልጋዮቹ ሁሉና ግብፃውያን በሙሉ ሌሊት ላይ ተነሡ። በግብፅ ውስጥ ጕልሕ የልቅሶ ጩኸት ነበረ፤ ሰው ያልሞተበት እንደም ቤት አልነበረምና።
31ሙሴንና አሮንን በሌሊት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ተነሡ፤ እናንተና እስራኤላውያን ከሕዝቤ መካከል ውጡ። ማድረግ የምትፈልጉትን እንደ ተናገራችሁ ሂዱ፣ እግዚአብሔርን አምልኩ።
32እንደ ተናገራችሁት፣ የበግና የፍየል መንጎቻችሁን፣ የቀንድና የጋማ ከብቶቻችሁንም ይዛችሁ ሂዱ፤ እኔንም ባርኩኝ።”
33እስራኤላውያንን ከአገራቸው ለማባረር በትልቅ ጥድፊያ ላይ ነበሩ፤ “ሁላችንም ማለቃችን ነው” ብለው ነበርና።
34ሕዝቡ እርሾ ያልተጨመረበትን ሊጣቸውን ያዙ። የቡሆ እቃዎቻቸውን ቀድሞውኑ በጨርቃቸው አስረው በትከሾቻቸው ተሸክመዋቸዋል።
35ሕዝብ ሙሴ እንደ ነገራቸው አደረጉ። የወርቅና የብር ዕቃዎችን፣ ልብስም እንዲሰጧቸው ግብፃውያንን ጠየቁ።
36ደስ ለማሰኘት እግዚአብሔር ግብፃውያንን አነሣሣ። ስለዚህ እስራኤላውያን የጠየቋቸውን ሁሉ ግብፃውያን ሰጧቸው። በዚህ መንገድ፣ እስራኤላውያን ግብፃውያንን በዘበዟቸው።
37ከራምሴ በመነሣት ወደ ሱኮት ተጓዙ። ቊጥራቸው ከሕፃናቱና ከሴቶቹ ሌላ ስድስት መቶ ሺሕ ያህል እግረኛ ነበር።
38እስራኤላዊ ያልሆነ ድብልቅ ሕዝቤም፣ ከበግና ከፍየል፣ እጅግ ብዙ ከሆነ የከብት መንጋ ጋር ዐብሯቸው ሄደ።
39ከግብፅ ያመጡትን እርሾ ተባርረው ስለ ወጡና ምግብ ማዘጋጀት ስላልቻሉ ነው።
40እስራኤላውያን በግብፅ ውስጥ የኖሩት አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነበር።
41መቶ ሠላሳው ዓመት ፍጻሜ፣ በዚያው ቀን፣ ሁሉም የእግዚአብሔር ሰራዊት ከግብፅ ምድር ወጣ።
42ሌሊት እግዚአብሔር ከግብፅ ምድር እንዲያወጣቸው ለእስራኤላውያን ነቅቶ የመቆያ ሌሊት ነበር። ይህ ሌሊት እስራኤላውያን ሁሉ፣ መላ ትውልዶቻቸው ሊያከብሩት የሚገባ ሌሊት ነው።
43እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “የፋሲካ ሕግ እነሆ፦ ባዕድ ሰው ፋሲካን አይበላውም።
44የተገዛ እያንዳንዱ የእስራኤል ባሪያ ግን ከገረዛችሁት በኋላ መብላት ይችላል።
45ቅጥር አገልጋዮች መብላት አይገባቸውም።
46ምግቡ በአንድ ቤት ውስጥ መበላት አለበት። ሥጋ ከቤት ማውጣት፣ ዐጥንትም መስበር የለባችሁም።
47የእስራኤል ማኅበረ ሰብ በዓሉን ሊያከብር ይገባል።
48ባዕድ ሰው ከእናንተ ጋር ቢኖርና ፋሲካን ለእግዚአብሔር ለማክበር ቢፈልግ፣ ወንድ ዘመዶቹ ሁሉ መገረዝ አለባቸው። ከዚያም በኋላ፣ ሰውየው መምጣትና በዓሉን ማክበር ይችላል። በምድሩ እንደ ተወለዱት ሰዎች ይሆናል። ይሁን እንጂ፣ ያልተገረዘ ሰው የፋሲካን ምግብ አይበላም።
49አንድ ዐይነት ሕግ ተግባራዊ የሚሆነው በሁለቱም ማለት በአገሬው ተወላጅና በመካከላችሁ በሚኖረው ባዕድ ሰውም ላይ ነው።”
50እስራኤላውያን ሁሉ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ።
51በዚያው ቀን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በየሰራዊታቸው ከግብፅ ምድር አወጣቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።