1ስለዚህ ንጉሡና ሐማ በንግሥት አስቴር ለመጋበዝ ሄዱ።
2በዚህ በሁለተኛው ቀን፥ ወይን እየጠጡ እያሉ፥ ንጉሡ አስቴርን፥ "ልመናሽ ምንድነው ንግሥት አስቴር? እርሱ ይሰጥሻል። ጥያቄሽስ ምንድነው? እስከ መንግሥት አጋማሽ ድረስ ይሰጥሻል?" አላት።
3ንግሥት አስቴርም መልሳ፥ "ንጉሥ ሆይ፥ በዓይንህ ፊት ሞገስ አግኝቼ ከሆነና ደስ የምትሰኝበትም ከሆነ ሕይወቴ እንድትሰጠኝ ልመናዬ ይህ ነው፥ ስለ ሕዝቤም የምጠይቀው ይህንኑ ነው።
4እኔና ሕዝቤ ለመጥፋት፥ ለመሞትና ለመደምሰስ ተሽጠናልና። ወንድና ሴት ባሪያዎች እንድንሆን ለባርነት ብቻ ተሽጠን ቢሆን ኖሮ ዝም ባልኩኝ ነበር፥ ይህንን በመሰለው ጭንቀት ንጉሡን ማወክ አይገባምና።
5ከዚያም ንጉሥ አርጤክስስ ንግሥት አስቴርን፥ "ማነው እርሱ? እንዲህ ያለውን ነገር ለማድረግ ልቡ የሞላ ያ ሰው የት ነው የሚገኘው?" አላት።
6አስቴርም፥ "ያ ጠላትና ባላጋራው ሰው ይህ ክፉው ሐማ ነው!" ሐማም በንጉሡና በንግሥቲቱ ፊት ደነገጠ።
7ንጉሡም በቁጣ ወይን ከሚጠጣበት ግብዣ ተነሥቶ ወደ ቤተመንግሥቱ መናፈሻ ሄደ፥ ሐማ ግን ንግሥት አስቴር ሕይወቱን እንድትታደገው ሊለምናት በዚያው ቆይቶ ነበር። ከንጉሡ ጥፋት እንደተወሰነበት አይቷልና።
8ከዚያም ንጉሡ ከቤተመንግሥቱ መናፈሻ ወደ ወይን መጠጫው ክፍል ተመለሰ። ሐማ አስቴር በነበረችበት ድንክ አልጋ ላይ ልክ መደፋቱ ነበር። ንጉሡም፥ "በገዛ ቤቴ፥ በእኔው ፊት ንግሥቲቱን ሊደፍራት ነው እንዴ?" አለ። ልክ ይህ ቃል ከንጉሡ አፍ እንደወጣ፥ አገልጋዮቹ የሐማን ፊት ሸፈኑት።
9ከዚያም ንጉሡን ከሚያገለግሉት ሹማምንቶች አንዱ የሆነው ሐርቦና፥ "ሃምሳ ክንድ ቁመት ያለው መስቀያ በሐማ ቤት ቆሟል። ያቆመውም ንጉሡን ለመታደግ የተናገረውን መርዶክዮስን ለመስቀል ነው" አለ። ንጉሡም "በእርሱ ላይ ስቀሉት" አላቸው።
10ስለዚህ ሐማን ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው መስቀያ ላይ ሰቀሉት። ከዚያም የንጉሡ ቁጣ በረደ።