መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

አስቴር 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1መርዶክዮስ የተደረገውን ሁሉ ባወቀ ጊዜ ልብሶቹን ቀደደ፥ ማቅ ለብሶም በራሱ ላይ አመድ ነሰነሰ። ወደ ከተማይቱ መካከል በመሄድም በታላቅ ጩኸት መራራ ልቅሶ አለቀሰ።
2ማቅ ለብሶ በንጉሡ በር በኩል ማለፍ አይፈቀድም ነበርና እስከ አቅራቢያው ድረስ ብቻ ሄደ።
3የንጉሡ ዐዋጅና ትዕዛዝ በደረሰበት አውራጃ ሁሉ በአይሁድ መካከል ከጾም፥ ከልቅሶና ከዋይታ ጋር ታላቅ ሀዘን ሆነ። ብዙዎቹም በማቅና በአመድ ላይ ተኙ።
4የአስቴር ወጣት ሴቶችና አገልጋዮቿ መጥተው ስለ ሁኔታው በነገሯት ጊዜ ንግሥቲቱ እጅግ አዘነች። እርሷም መርዶክዮስን እንዲያለብሱት (ማቁን አውጥቶ እንዲጥል ነበር) ልብሶችን ላከችለት፥ እርሱ ግን አልተቀበለም።
5ከዚያም አስቴር እርሷን ለማገልገል የተመደበውንና ከንጉሡ ሹማምንት አንዱ የሆነውን ሀታክን ጠራችው። ምን እንደ ተፈጠረና ምን ማለትም እንደሆነ ያጣራ ዘንድ ወደ መርዶክዮስ እንዲሄድ አዘዘችው።
6ስለዚህ ሀታክ በንጉሡ በር ፊት ለፊት ወደሚገኘው የከተማው አደባባይ ወደ መርዶክዮስ ሄደ።
7መርዶክዮስም የገጠመውን ነገር ሁሉ፥ አይሁድን ለመግደል ሐማ ወደ ንጉሡ ግምጃ ቤት ለማስገባት ቃል የገባውን የገንዘብ መጠን አስታወቀው።
8በተጨማሪም አይሁድን ለማጥፋት በሱሳ የታወጀውን የዐዋጁን ቅጅም ሰጠው። ይህንንም ያደረገው ሀታክ ለአስቴር እንዲያሳያትና ወደ ንጉሡ ሄዳ ስለ ሕዝቧ ምህረት እንዲያደርግ እንድትለምነውና እንድትማልደው ኃላፊነት እንዲሰጣት ነበር።
9ሀታክ ሄደና መርዶክዮስ ነግሮት የነበረውን ለአስቴር ነገራት።
10ከዚያም አስቴር ሀታክ ተመልሶ ወደ መርዶክዮስ እንዲሄድ ነገረችው።
11እንዲህም አለችው፥ "ወንድ ሆነ ሴት ማንኛውም ሰው ሳይጠራ ወደ ውስጠኛው አደባባይ ቢገባ አንድ ሕግ ብቻ እንዳለ የንጉሡ አገልጋዮች ሁሉና በንጉሡ አውራጃዎች የሚኖሩ ሕዝቦች ያውቃሉ፥ ሕጉም በሕይወት እንዲኖር ንጉሡ የወርቅ በትሩን ከሚዘረጋለት በስተቀር መገደል አለበት የሚል ነው። እነዚህን ሠላሳ ቀናት ወደ ንጉሡ ለመቅረብ አልተጠራሁም።"
12ስለዚህ ሀታክ የአስቴርን ቃል ለመርዶክዮስ አስታወቀው።
13መርዶክዮስም እንዲህ የሚል መልዕክት መለሶ ለከባት፥ "በንጉሡ ቤተመንግሥት ውስጥ ስለሆንሽ ከሌሎቹ አይሁዶች ሁሉ ይልቅ እንደምትድኚ ማሰብ የለብሽም።
14አንቺ በዚህ ጊዜ ዝምታን ብትመርጪ ለአይሁድ እርዳታና መዳን ከሌላ ሥፍራ ይነሣላቸዋል፥ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ። ወደ ንግሥትነት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ቀን እንደሆነስ ማን ያውቃል?"
15ከዚያም አስቴር ይህን መልዕክት ወደ መርዶክዮስ ላከች፥
16"ሂድ፥ በሱሳ የሚኖሩትን አይሁድ ሁሉ በአንድ ላይ ሰብስባቸውና ስለ እኔ ጹሙ። ለሦስት ቀንና ሌሊት አትብሉ፥ አትጠጡም። እኔና ወጣት ልጃገረዶቼም እንደዚሁ እናደርጋለን። ከዚያም ከሕጉ ውጪ ቢሆንም ወደ ንጉሡ እገባለሁ፥ ከጠፋሁም እጠፋለሁ።"
17መርዶክዮስም ሄዶ አስቴር ያለችውን ሁሉ አደረገ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።