1እንግዲህ እንደ ተወደዱ የእርሱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትመስሉ ሁኑ፤
2እንደ ወደደን፥ ራሱንም ስለ እኛ መልካም መዓዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር እንዳቀረበ ሁሉ እናንተም በፍቅር ኑሩ።
3የሚገባ ባለመሆኑ ዝሙት፥ማንኛውም ርኩሰትና ስስት በእናንተ ዘንድ ሊኖር አይገባም፤
4ጸያፍ ንግግር፥ዋዛ ወይም ውርደትን የሚያስከትል ቀልድ ለእናንተ ስለማይገባ ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ከዚህ ይልቅ የምታመሰግኑ ሁኑ።
5አመንዝራ፥ርኩስ፥ ስግብግብ የሆነ ይኽውም ጣዖት አምላኪ ሰው በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት እንደማይኖረው ርግጠኛ ልትሆኑ ይገባል።
6ከንቱ በሆነ ንግግር ማንም አያታላችሁ፤በእነዚህ ነገሮች ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ ይመጣል
7ስለዚህ የእነርሱ ተባባሪዎች አትሁኑ።
8ወቅት ጨለማ ነበራችሁና፤ አሁን ግን በክርስቶስ ብርሃን ናችሁ። ስለዚህ እንደ ብርሃን ልጆች ኑሩ።
9ምክንያቱም ከብርሃኑ የሚገኘው ፍሬ መልካም ነገር ሁሉ፥ ጽድቅና እውነት ነው
10እንዲሁም ጌታን ደስ የሚያሰኝ ነገር ለማድረግ አስቡ፤
11ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፤ይልቁን ልትገልጡት ይገባል።
12በስውር ያደረጉትን ነገር ለመግለጽ እንኳ አሳፋሪ ነውና።
13በሚኖርበት ጊዜ ማንኛውም ነገር በግልጽ ይታያል።
14ብርሃኑ በላዩ ላይ ስለሚያበራ ነው። ስለዚህ፥ «አንተ የምትተኛ ንቃ፤ከሙታን ተነሳ፤ክርስቶስም ያበራልሃል» ተብሎ ተነግሯል።
15ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን፥እንደ ጥበብኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ።
16ክፉዎች ስለሆኑ ዘመኑን ዋጁ።
17ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።
18ሕይወታችሁን ለጥፋት ስለሚዳርግ፥በወይን ጠጅ አትስከሩ፤ይልቁንስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ።
19እርስ በርሳችሁ በመዝሙር፥በቅኔና በመንፈሳዊ ዝማሬ ተነጋገሩ፤ ጌታንም በልባችሁ አመስግኑ፤ለእርሱም ተቀኙ።
20በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉም ነገር ሁልጊዜ እግዚአብሔር አብን አመስግኑ
21ክርስቶስን ለማክበር ስትሉ አንዳችሁ ለሌላችሁ ተገዙ።
22ሚስቶች ሆይ! ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ።
23ክርስቶስ አካሉ ለሆነችውና አዳኟ ለሆናት ቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ ሁሉ ባልም የሚስቱ ራስ ነውና።
24ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ ሁሉ ሚስቶችም በማንኛውም ነገር ለባሎቻቸው ሊገዙ ይገባል።
25ባሎች ሆይ፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ስለ እርስዋም ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ፥ እናንተም ሚስቶቻችሁን ውደዱ።
26ይህንንም ያደረገው በቃሉ አማካይነት በውሃ አጥቦ በማንጻት እንድትቀደስ፥
27ጉድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ነገር ሳይታይባት ቅድስት የሆነችና ነውር የሌለባት ክብርት ቤተ ክርስቲያን አድርጎ ለራሱ ሊያቀርባት ነው።
28ባሎች የገዛ ሥጋቸውን እንደሚወዱ ሚስቶቻቸውን መውደድ ይገባቸዋል። ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል።
29የራሱን ሥጋ የሚጠላ ማንም የለም፤ ይልቁን ይመግበዋል፤ ይንከባከበዋልም። ይህም ክርስቶስ ልክ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚወድ ነው።
30እኛ የእርሱ ብልቶች ነን።
31ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ከሚስቱም ጋር አንድ ይሆናል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
32ታላቅ ምስጢር ነው፤ እኔም ይህን የምናገረው ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያኑ ነው።
33ግን ከእናንተ እያንዳንዱ ደግሞ ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ መውደድ ይገባዋል፤ ሚስትም ባልዋን ታክብር።