1ስለዚህ የጌታ እስረኛ እንደመሆኔ በእግዚአብሔር ለተጠራችሁለት መጠራት የሚገባውን ሕይወት ትኖሩ ዘንድ እለምናችኋለሁ።
2ይኽውም እርስ በርስ በፍቅር ተቻችላችሁ በፍጹም ትሕትና፥በገርነትና በትዕግሥት እንድትኖሩ ነው።
3በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ አድርጉ።
4በተጠራችሁ ጊዜ በአንድ ተስፋ እንደተጠራችሁ ሁሉ፥ አንድ አካል እና አንድ መንፈስ አለ፤
5አንድ ጌታ፥አንድ እምነት፥አንድ ጥምቀት አለ ፤
6ደግሞም ከሁሉ በላይ የሆነ፥በሁሉ የሚሠራ፥ በሁሉ የሚኖር ፥የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ።
7ክርስቶስ ስጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጥቶናል
8ይህም የእግዚአብሔር ቃል «ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮኞችን ማረከ፤ለሰዎችም ስጦታ ሰጠ» በማለት እንደሚናገረው ነው።
9«ወደ ላይ ወጣ» ሲል ደግሞም «ወደ ምድር ጥልቅ ወረደ» ማለት ካልሆነ በቀር ሌላ ምን ሊያመለክት ይችላል?
10ታች የወረደው ሁሉንም ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ያው እርሱ ራሱ ነው።
11ወንጌል ሰባኪዎችን፥እረኞችን እና አስተማሪዎችን ስጦታ አድርጎ የሰጠ ክርስቶስ ራሱ ነው።
12ያደረገው የክርስቶስን አካል ለማነጽና ለአገልግሎት ሥራ ቅዱሳንን ለማስታጠቅ ነው።
13የሚሆነው ሁላችንም የእግዚአብሔርን ልጅ በማመን እና በማወቅ ወደ ሚገኘው አንድነት እንዲሁም ወደ ክርስቶስ ሙላት ልክ እንዳደጉት ሰዎች ሙሉ ሰው ወደ መሆን ደረጃ እስከምንደርስ ድረስ ነው።
14በሰዎች ረቂቅ ተንኮል እና ማታለል በተዘጋጀ የትምህርት ነፋስ ወዲያና ወዲህ የምንነዳ ሕጻናት መሆን አይገባንም
15ይልቁንም እውነትን በፍቅር የምንናገር እና ራስ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ በሁሉም መንገድ የምናድግ ሰዎች መሆን ይጠበቅብናል።
16የአማኞችን አካል ሁሉ በሚያገናኘው ጅማት እየተያያዘና እየተጋጠመ፥እያንዳንዱም ክፍል የራሱን ተግባር እያከናወነ በፍቅር ያድጋል።
17እየለመንኋችሁ ይህን የምናገረው፥ ከእንግዲህ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱት እንደ አሕዛብ እንዳትኖሩ ነው።
18እነርሱም አእምሮአቸው ጨልሞአል፤ካለማወቃቸውና ከልባቸው ደንዳናነት የተነሳ ከእግዚአብሔር ሕይወት ርቀዋል፤
19ስግብግብነት ሁሉ ለሞላበት ቅጥ ላጣ ብልግና ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል።
20ግን ስለ ክርስቶስ የተማራችሁት እንደዚህ አይደለም።
21እርሱ የሰማችሁ እና የተማራችሁ ከሆነም በርግጥ የተማራችሁት ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን እውነት ነው።
22ክፉ ምኞት የጎደፈውን አስቀድሞ ትኖሩበት የነበረውን አሮጌውን ሰው ልታስወግዱ ይገባል።
23በአእምሮአችሁ መንፈስ እንድትታደሱ
24እውነተኛ በሆነው ጽድቅና ቅድስና በእግዚአብሔር የተፈጠረውን አዲሱን ሰው እንድትለብሱ ነው።
25ውሸትን አስወግዱ፤ ሁላችንም የአንድ አካል ብልቶች ስለሆንን «እያንዳንዱ ከባልንጀራው ጋር እውነትን ይነጋገር»።
26«ተቆጡ፤ ነገር ግን ኀጢአት አትሥሩ» በቁጣችሁ ጸሓይ እስከሚገባ ድረስ አትቆዩ፤
27ዕድል አትስጡት።
28የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ፤ይልቁንም ለተቸገሩ ሰዎች ማካፈል ይችል ዘንድ በራሱ እጅ በተገቢው ሁኔታ እየሠራ ለማግኘት ጥረት ማድረግ ይገባዋል።
29ለማነጽ የሚያስፈልግ፥ ለሚሰሙትም ጸጋን የሚሰጥ ጠቃሚ ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከቶ ከአፋችሁ አይውጣ።
30ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑ።
31ሁሉ፥ቁጣንና ንዴትን፥ጭቅጭቅንና ስድብን ከማንኛውም ዓይነት ክፋት ጋር ከእናንተ ዘንድ አስወግዱ።
32በርሳችሁ ቸሮች፥ ርኅሩሆች ሁኑ፤ ደግሞም እግዚአብሔር በክርስቶስ እንዲሁ ይቅር እንዳላችሁ እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ።