1ልጆች ሆይ፤ በጌታ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤ ይህ ተገቢ ነውና።
2«አባትህንና እናትህን አክብር» በሚለው የመጀመሪያ ትእዛዝ ውስጥ ያለው ተስፋ
3እንዲሆንልህ፥ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም» የሚል ነው።
4እናንተም አባቶች ሆይ፤ ልጆቻችሁን አታስቆጡአቸው፤ ይልቁንስ በጌታ ሥርዓትና ምክር አሳድጓቸው።
5ባሮች ሆይ፤ ለክርስቶስ እንደምትታዘዙት ለምድራዊ ጌቶቻችሁም በታላቅ አክብሮት፥ በመንቀጥቀጥና በልባችሁ ቅንነት ታዘዙ፤
6ለታይታ እነርሱን ደስ ለማሰኘት ብላችሁ ሳይሆን፥ እንደ ክርስቶስ አገልጋዮች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከልብ በመፈጸም ታዘዙአቸው።
7ሰውን ሳይሆን ጌታን እንደምታገለግሉ እያሰባችሁ በደስታ አገልግሉ።
8ባሪያም ይሁን ነጻ ሰው እያንዳንዱ ሰው ለሚያደርገው መልካም ነገር ከጌታ ሽልማት እንደሚቀበል ልብ በሉ።
9እናንተም ጌቶች ሆይ፤ ለባሮቻችሁ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የእነርሱና የእናንተም ጌታ የሆነው እርሱ በሰማይ እንዳለና ለሰው ፊትም እንደማያዳላ ተረድታችሁ አታስፈራሯቸው።
10በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ የበረታችሁ ሁኑ።
11የዲያብሎስን ተንኮል አዘል ዕቅድ መቋቋም ትችሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ሁሉ ልበሱ።
12ውጊያችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከአለቆች፥ ከሥልጣናት፥ ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦችና በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ርኩሳን መናፍስት ጋር ነው።
13በክፉ ቀን ክፉውን በመቃወም ጸንታችሁ ትቆሙ ዘንድ የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ሁሉ ልበሱ፤ ጸንታችሁ ለመቆምም ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ።
14ወገባችሁን በእውነት ቀበቶ ታጥቃችሁ፥የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ ጸንታችሁ ቁሙ፤
15የሰላምን ወንጌል ለማወጅ እግሮቻችሁ በዚያ ተጫምተው ዝግጁ ይሁኑ
16የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ማጥፋት ትችሉ ዘንድ ሁል ጊዜ የእምነትን ጋሻ አንሱ።
17የመዳንን ራስ ቁር አድርጉ፤የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ፤ይህም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
18ዓይነት ጸሎትና ልመና ሁልጊዜ በመንፈስ በመጸለይና መልሱን ከእርሱ በመጠበቅ፥ ለቅዱሳንም ልመና በማቅረብ ትጉ።
19ምስጢር በድፍረት ለመናገር አፌን በምከፍትበት ጊዜ ሁሉ ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ለእኔም ጸልዩልኝ።
20መናገር እንደሚገባኝ በድፍረት እናገር ዘንድ በሰንሰለት የታሰረ መልእክተኛ የሆንሁት ለዚሁ ነውና።
21ሁኔታ እንዳለሁና ምን እያደረግሁ እንደምገኝ፥ የተወደደ ወንድምና በጌታ ታማኝ አገልጋይ የሆነው ቲኪቆስ ሁሉንም ነገር ይነግራችኋል።
22ያለንበትን ሁኔታ እንድታውቁና እናንተንም እንዲያበረታታ በማለት ወደ እናንተ ልኬዋለሁ።
23ከአብ፥ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ፍቅር ከእምነት ጋር ለወንድሞች ይሁን።
24ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ከሚወዱ ጋር ሁሉ ጸጋ ይሁን።