መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መክብብ 8

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ጥበበኛ የሆነ ሰው ማን ነው? በሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ሁነቶችን ትርጉም የሚያውቅ ማን ነው? በሰው ውስጥ ያለች ጥበብ ፊቱን ታበራለች፥ የፊቱም ክባዴ ይለወጣል።
2እግዚአብሔር ሊጠብቀው ምሎለታልና የንጉሡን ትዕዛዝ እንድትፈጽም እመክርሃለሁ።
3ንጉሡ ደስ ያለውን ያደርጋልና ከፊቱ በችኮላ አትውጣ፥ ትክክል ላልሆነውም ነገር ድጋፍህን አትስጥ።
4የንጉሥ ቃል ይገዛል፥ ስለዚህ፥ "ምን እያደረግህ ነው?" ማን ይለዋል?
5የንጉሡን ትዕዛዝ የሚጠብቅ ጉዳትን ያርቃል። የጠቢብ ልብ የመተግበሪያ ጊዜንና ተገቢ አካሄድን ያስተውላል።
6የሰው መከራው ብዙ ነውና ለእያንዳንዱ ጉዳይ ትክክለኛ ምላሽና ምላሹን የሚሰጥበት ጊዜ አለ።
7ቀጥሎ የሚሆነውን ማንም አያውቅም። ሊመጣ ያለውን ማን ሊነግረው ይችላል?
8መተንፈስን ለማቆም በሕይወት እስትንፋስ ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም፥
9ደግሞም በሞቱ ቀን ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም። በጦርነት ጊዜ ከሠራዊቱ የሚሰናበት ማንም የለም፥ አመጻም ባሪያ የሆኑለትን አይታደጋቸውም። ይህንን ሁሉ አስተዋልሁ፤ ከፀሐይ በታች ለሚሠራው ለሁሉም ዓይነት ሥራ ልቤን ሰጠሁ። አንድ ሰው በሌሎች ላይ ክፉ ለማድረግ አቅም የሚያገኝበት ጊዜ አለ።
10ስለዚህ አመጸኞች በይፋ ሲቀበሩ አየሁ። ከተቀደሰው አካባቢ ተወስደው ተቀበሩ፥ የአመጽ ሥራቸውን ይሠሩበት የነበረ ከተማ ሰዎችም አመሰገኗቸው። ይህ ደግሞ ከንቱነት ነው።
11በክፉ ወንጀል ላይ ፍርድ ፈጥኖ በማይሰጥበት ጊዜ፥ ክፋትን እንዲያደርጉ የሰው ልጆችን ልብ ያነሣሣል።
12አንድ ኃጢአተኛ መቶ ጊዜ ክፋትን ቢያደርግና ረጅም ዘመን ቢኖር እንኳን እግዚአብሔርን ለሚያከብሩት፥ አብሯቸው መሆኑን ለሚያከብሩ በጎነት እንደሚሆንላቸው አውቃለሁ።
13ለክፉ ሰው ግን በጎነት አይሆንለትም፤ ሕይወቱም አይረዝምም። እግዚአብሔርን አያከብርምና ዘመኑ ፈጥኖ እንደሚያልፍ ጥላ ነው።
14በምድር ላይ የተደረገ ሌላ ከንቱ እንፋሎት አለ። በክፉ ሰዎች ላይ የሚደርሰው በጻድቃኑም ላይ ይደርሳል፥ ለጻድቃኑ የሚደርሰውም ለክፉዎች ሰዎችም ይደርሳል። እኔም፥ ይህ ደግሞ ክፉ እንፋሎት ነው አልሁ።
15ለሰው ከፀሐይ በታች ከመብላት፥ መጠጣትና መደሰት የሚሻል ነገር ስለሌለው ደስታ ይሻላል እላለሁ። ከፀሐይ በታች እግዚአብሔር በሰጠው የሕይወት ዘመኑ ሁሉ በሚደክምበት ነገር ደስታ አብሮት ይሆናል።
16ጥበብን ለማወቅና በምድር ላይ የሚሠራውን ሥራ ለማስተዋል ልቤን በሰጠሁ ጊዜ ብዙ ጊዜ በቀንም ሆነ በሌሊት ያለ እንቅልፍ በሚሠራው ሥራ
17ከዚያም የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ ተመለከትሁ ከፀሐይ በታች የሚሠራውን ሥራ ሰው ሊያስተውለው አይችልም። አንድ ሰው መልሶቹን ለማግኘት ምንም ያህል ቢጥር አያገኛቸውም። ጠቢብ ሰው እንድሚያውቅ ቢያምንም እንኳን በርግጥ አያውቅም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።