መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መክብብ 7

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከውድ ሽቶ መልካም ስም ይሻላል፥ ከልደት ቀንም የሞት ቀን ይሻላል።
2ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ወደ ሀዘን ቤት መሄድ ይሻላል፥ በሕይወቱ መጨረሻ ሰው ሁሉ ሀዘን ይገጥመዋልና፥ ስለዚህ ሕያዋን የሆኑ ሰዎች ይህንን ልብ ማለት አለባቸው።
3ከሣቅ ጥልቅ ሐዘን ይሻላል፥ ከፊት ሐዘን በኋላ የልብ ደስታ ይመጣልና።
4የጠቢብ ልቡ ሐዘን ቤት ውስጥ ነው፥ የሞኞች ልብ ግን በግብዣ ቤት ውስጥ ነው።
5የሞኞችን መዝሙር ከመስማት የጠቢብን ተግሳጽ መስማት ይሻላል።
6ከድስጥ ሥር የሚነድ እሾህ እንደሚንጣጣ የሞኞች ሣቅ ደግሞ እንደዚሁ ነው። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው።
7ቀማኛነት ጠቢቡን ሰው ያለጥርጥር ሞኝ ያደርገዋል፥ ጉቦም ልቡን ያበላሸዋል።
8የአንድ ነገር መጨረሻ ከጅማሬው ይሻላል፤ በመንፈሳቸው ትዕግስተኞች የሆኑ ሰዎች በመንፈሳቸው ከሚታበዩት ይሻላሉ።
9በመንፈስህ ለመቆጣት አትቸኩል፥ ቁጣ በሞኞች ልብ ያድራልና።
10"ከእነዚህ ይልቅ ያለፉት ዘመናት ለምን ተሻሉ?" አትበል፥ ይህንን የምትጠይቀው ጥበበኛ ስለሆንክ አይደለምና።
11ጥበብ ከአባቶቻችን የምንወርሳቸውን ጠቃሚ ነገሮች ያህል መልካም ነው። እርሱ ፀሐይን ለሚያዩ ለእነዚያ ትርፍ ያስገኝላቸዋል።
12ገንዘብ ጥበቃ ሊሰጥ እንደሚችል ጥበብም ጥበቃን ይሰጣል፥ የዕውቀት ብልጫው ግን ጥበብ ላገኟት ሕይወት መስጠቷ ነው።
13የእግዚአብሔርን ሥራ ተመልከት፡ እርሱ ያጣመመውን የትኛውንም ነገር ማን ሊያቃናው ይችላል?
14ጊዜው መልካም ሲሆን በደስታ ኑርበት፥ ቀኑ ሲከፋ ግን ይህን አስብ፡ ሁለቱም አጠገብ ለአጠገብ እንዲኖሩ እግዚአብሔር ፈቅዶላቸዋል። በዚህ ምክንያት ማንም ሰው ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን የትኛውንም ነገር አያውቅም።
15ከንቱ በሆነው የሕይወት ዘመኔ ብዙ ነገሮችን ተመልክቻለሁ። ጻድቃን ቢሆኑም የሚጠፉ ጻድቅ ሰዎች አሉ፥ ክፋትን ቢያደርጉም ረጅም ዘመን የሚኖሩ አመጸኞችም አሉ።
16ራስህን አታጽድቅ፥ በራስህም ግምት ጠቢብ አትሁን። ለምን ራስህን ታጠፋለህ?
17እጅግ አመጸኛ ወይም ሞኝ አትሁን። ለምን ከቀንህ በፊት ትሞታለህ?
18ይህንን ጥበብ ብትይዝ መልካም ነው፥ ጽድቅንም ከማድረግ እጅህን ባትመልስ። እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ኃላፊነቱን ሁሉ ይወጣልና።
19በአንድ ከተማ ውስጥ ካሉ አሥር አስተዳዳሪዎች ይልቅ በጥበበኛ ሰው ውስጥ ያለች ጥበብ ተጽዕኖዋ ትልቅ ነው።
20መልካምን የሚያደርግና ፈጽሞ ኃጢአትን የማይሠራ አንድም ጻድቅ በምድር ላይ የለም።
21የሚነገረውን ቃል ሁሉ አታድምጥ፥ ምናልባት አገልጋይህ ሲረግምህ ትሰማው ይሆናልና።
22በተመሳሳይ፥ ሌሎችን በልብህ ብዙ ጊዜ እንደረገምካቸው አንተ ራስህ ታውቃለህ።
23ይህንን ሁሉ በጥበብ አረጋገጥሁ። እኔም፥ "ጠቢብ እሆናለሁ" አልሁ፥ እርሱ ግን መሆን ከምችለው በላይ ነው።
24ጥበብ ሩቅና ጥልቅ ናት። ማን ሊያገኛት ይችላል?
25ለመማርና ለመፈተን፥ ጥበብንና የእውነታን ማብራሪያ ለመፈለግና ክፋት የማይረባ፥ ሞኝነትም ዕብደት መሆኑን ለመረዳት ልቤን መለስሁ።
26ልቧ በወጥመድና በመረብ የተሞላ፥ እጆቿም የእግር ብረት የሆኑ የትኛዋም ሴት ከሞት ይልቅ መራራ ናት። እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ማንም ቢሆን ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛው ግን በእርሷ ይወሰዳል።
27"መርምሬ ያገኘሁትን ተመልከቱ" ይላል አስተማሪው። የእውነታን ፍቺ ለማግኘት በአንደኛው ምርምር ላይ ሌላውን እጨምር ነበር።
28እስካሁን የምፈልገው ይህንን ነው፥ ነገር ግን አላገኘሁትም። በሺህ ሰዎች መካከል አንድ ጻድቅ አገኘሁ፥ በእነዚያ ሁሉ መካከል ግን አንዲት ሴት አላገኘሁም።
29እግዚአብሔር ሰዎችን ቅን አድርጎ እንደ ፈጠራቸው፥ እነርሱ ግን ብዙ ችግሮችን እየፈለጉ ርቀው እንደ ሄዱ ይህንን ብቻ አገኘሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።