መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መክብብ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ለሁሉም ነገር የተቀጠረለት ጊዜ አለው፥ ከምድር በታች ለሚሆነውም ወቅት አለው።
2ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞት ጊዜ አለው፥ ለመትከል ጊዜ አለው፥ ለመንቀል ጊዜ አለው፥
3ለመግደል ጊዜ አለው፥ ለመፈወስ ጊዜ አለው፥ ለማፍረስ ጊዜ አለው፥ ለመገንባት ጊዜ አለው፥
4ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሣቅ ጊዜ አለው፥ ለማዘን ጊዜ አለው፥ ለመጨፈር ጊዜ አለው፥
5ድንጋይ ለመወርወር ጊዜ አለው፥ ድንጋይ ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፥ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመተቃቀፍ ለመራቅ ጊዜ አለው፥
6ለመፈለግ ጊዜ አለው፥ ፍለጋን ለማቆም ጊዜ አለው፥ ነገሮችን ለመጠበቅ ጊዜ አለው፥ ነገሮችን ወርውሮ ለመጣል ጊዜ አለው፥
7ልብስ ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋት ጊዜ አለው፥ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገር ጊዜ አለው፥
8ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላት ጊዜ አለው፥ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላም ጊዜ አለው።
9ሠራተኛው ከጥረቱ የሚያተርፈው ምንድነው?
10እግዚአብሔር እንዲፈጽሙት ለሰው ልጆች የሰጣቸውን ሥራ አይቻለሁ።
11እግዚአብሔር ሁሉን ነገር በጊዜው ተስማሚ አድርጎ ሠራው። ደግሞም በልባቸው ውስጥ ዘላለማዊነትን አስቀመጠ። ነገር ግን የሰው ልጆች ከጅማሬአቸው እስከ ፍጻሜአቸው ድረስ እግዚአብሔር የሠራውን ሥራ ሊያስተውሉት አይችሉም።
12ለሰው በሕይወት ዘመኑ ከመደሰትና መልካም ከማድረግ በቀር የሚሻል ምንም ነገር እንደሌለ አውቃለሁ።
13ደግሞም ሰው ሁሉ ሊበላና ሊጠጣ፥ ከሥራውም ሁሉ በሚመጣ መልካም እንዴት መደሰት እንዳለበት ሊያውቅ። ይህ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው።
14እግዚአብሔር የሠራው ሁሉ ለዘላለም እንደሚኖር አውቃለሁ። በዚህ ላይ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይቻልም። ምክንያቱም ሰዎች በአክብሮት እንዲቀርቡት ይህንን ያደረገው እግዚአብሔር ነው።
15አሁን ያለው ሁሉ ቀደም ሲል የነበረ ነው፤ ወደ ፊት የሚኖረውም ሁሉ ቀደም ሲል የነበረ ነው። እግዚአብሔር ሰዎችን የተደበቁ ነገሮችን እንዲፈልጉ ያደርጋቸዋል።
16ከፀሐይ በታች ፍትሕ ሊኖር በሚገባበት ግፍ መኖሩን አየሁ፥ ጽድቅ ሊኖር በሚገባበትም ሥፍራ ብዙ ጊዜ የሚገኘው ግፍ ነው።
17እኔም በልቤ፥ "ስለ እያንዳንዱ ጉዳይና ስለ እያንዳንዱ ሥራ በጻድቁና በአመጸኛው ላይ በትክክለኛው ጊዜ እግዚአብሔር ይፈርዳል" አልሁ።
18እኔም በልቤ፥ "የሰው ልጆች እንደ እንስሳ መሆናቸውን ለማሳየት እግዚአብሔር ይፈትናቸዋል" አልሁ።
19በእንስሳት ላይ የሚደርሰው ያው ዕድል ፈንታ በሰው ልጆች ላይ ይደርሳልና። እንደ እንስሳቱ፥ ሰዎች ሁሉ ይሞታሉ። ያንኑ አየር ሁሉም ይተነፍሱታል፥ ስለዚህ በዚህ መንገድ ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም። ሁሉም ነገር ፈጥኖ የሚጠፋ እስትንፋስ አይደለም?
20ሁሉም ወደ አንድ ሥፍራ ይሄዳሉ። ሁሉም ነገር ከአፈር ይመጣል፥ ሁሉም ነገር ደግሞ ወደ አፈር ይመለሳል።
21የሰው መንፈስ ወደ ላይ፥ የእንስሳ መንፈስም ወደ ታች ወደ ምድር ውስጥ ይሄድ እንደሆነ የሚያውቅ ማን ነው?
22ስለዚህ ማንም ሰው በሥራው ከመደሰት የሚበልጥ የተሻለ ነገር እንደሌለ እንደገና አስተዋልሁ፥ ያ ዕድል ፈንታው ነውና። ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን እንዲያይ ማን መልሶ ሊያመጣው ይችላል?
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።