መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መክብብ 11

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እንጀራህን በውሃ ላይ ጣል፥ ከብዙ ቀናት በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህ።
2ከሰባት እንዲያውም ከስምንት ሰዎች ጋር ተካፈለው፥ በምድር ላይ የሚመጣውን ጥፋት አታውቅምና።
3ደመና ዝናብን ከተሞላ በምድር ላይ ይለቀዋል፥ አንድ ዛፍ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ወይም ወደ ሰሜን ቢወድቅ፥ ዛፉ በወደቀበት በዚያው ይኖራል።
4ማንም ንፋስን የሚጠባበቅ አይተክልም፥ ደመናንም የሚጠብቅ መከሩን አይሰበስብም።
5ንፋስ ከየት አቅጣጫ እንደሚመጣ፥ እንዲሁም የሕጻኑ አጥንቶች በእናቱ ማኅፀን ውስጥ እንዴት እንደሚያድግ እንደማታውቅ ሁሉን የፈጠረውን የእግዚአብሔር አሠራር ደግሞ ለማወቅ አትችልም።
6በጠዋት ዘርህን ዝራ፤ እስከ ምሽትም ድረስ፥ የሚያስፈልገውን ያህል በእጆችህ ሥራ፤ የትኛው እንደሚበቅል፥ የጠዋቱ ወይም የምሽቱ፥ ይህ ወይም ያኛው፥ ወይም ሁለቱም መልካም ይሆኑ እንደኾነ አታውቅምና።
7በእውነት ብርሃን ጣፋጭ ነው፥ ፀሐይን ማየትም ለዓይን የሚያስደስት ነገር ነው።
8ሰው ረጅም ዘመን ቢኖር በእነዚያ ሁሉ ደስ ይበለው፥ ነገር ግን ብዙዎች ናቸውና ሊመጡ ያሉትን ጨለማ ቀናት ያስብ። የሚመጣውም ሁሉ እንደ እንፋሎት ጠፊ ነው።
9አንተ ወጣት፥ በወጣትነትህ ደስ ይበልህ፥ በወጣትነትህም ዘመን ልብህን ደስታ ይሙላው። የልብህን መልካም ምኞትና ዓይንህ የሚያየውን ሁሉ ተከተል። ይሁን እንጂ ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ እወቅ።
10ከልብህ ቁጣን አስወግድ፥ የትኛውንም በሰውነትህ ያለውን ሕመም ቸል በለው፥ ወጣትነትና ብርታቱ እንፋሎት ነውና።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።