መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 9

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እስራኤል ሆይ፥ ስሙ፥ ከእናንተ የበለጡትንና የበረቱትን አሕዛብ፥ እስከ ሰማይም ድረስ የተመሸጉትን ታላላቅ ከተሞች ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ዛሬ ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ነው፤
2የኤናቅ ልጆች ፥ ታላቅና ረጅም ሕዝብ፥ እናንተም የምታውቃቸው ስለ እነርሱም እንዲህ ያላችኋቸው፦ በዔናቅ ልጆች ፊት ማን መቆም ይችላል?
3ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁም እንደሚበላ እሳት ሆኖ በፊታችሁ ስለሚያልፍ፥ ዛሬ እርሱ ያጠፋቸዋል፥ በፊታችሁም ያዋርዳቸዋል፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገራችሁ እናንተ ታሳድዳቸዋላችሁ ፈጥናችሁም ታጠፋቸዋላችሁ።
4እግዚአብሔር አምላካችሁ ከፊታችሁ ካወጣቸው በኋላ ፦ እንወርሳት ዘንድ ወደዚህች ምድር እግዚአሔር ያመጠን፥ ስለ ጽድቄ ነው፥ እነዚህንም አሕዛብ እግዚአብሔር ከፊታችን ያወጣቸው ኃጢአተኞች ስለ ሆኑ ነው፥ ብላችሁ በልባችሁ እንዳትናገሩ።
5ምድራቸውን ትወርሱአት ዘንድ የምትገቡት ስለ ጽድቃችሁ ወይም ስለ ልባችሁ ቅንነት አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ከፊታችሁ በሚያጠፋቸው በእነዚያ አሕዛብ ኃጢአት ምክንያትና ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የማለላቸውን ቃል ይፈጽም ዘንድ ነው።
6እንግዲህ እናንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ስለ ሆናችሁና እግዚአብሔር አምላካችሁ ይህን መልካም ምድር ርስት አድርጎ የሰጣችሁ ስለጽድቃችሁ እንዳይደለ እወቁ።
7እግዚአብሔር አምላካችሁን በምድረ በዳ እንዳስቁጣችሁት ከግብፅ አገር ከወጣችሁበት ቀን ጀምሮ ወደዚህ ስፍራ እስከ መጣችሁ ድረስ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፃችሁ አስቡ።
8በኮሬብ ደግሞ እግዚአብሔርን አስቆጣችሁ፤ እግዚእብሔርም ሊያጠፋችሁ ተቆጣባችሁ።
9እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባውን የቃል ኪዳን፥ የድንጋዩን ጽላቶችን ከእግዚአብሔር ለመቀበል ወደ ተራራ ወጥቼ በተራራው ላይ ለአርባ ቀናትና አርባ ሌሊት በቆየሁበት ጊዜ እንጀራም አልበለሁም፥ ውኃም አልጠጠሁም።
10እግዚአብሔርም በእርሱ ጣት የተጻፉትን ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶችን ሰጠኝ፤ በጽላቶቹም ላይ በተራራው ሥር በነበረው ጉበዔ እግዚአብሔር በእሳት መካከል ሆኖ የተናገራችሁ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር።
11ከአርባ ቀንና ከእርባ ሌሊትም በኋላ እግዚአብሔር ሁለቱን የድግንጋይ ጽላቶች፥ ያቃል ኪዳኑን ጽላቶች ሰጠኝ።
12እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ተነሥተህ ከዚህ ፈጥነህ ውረድ ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ረክሰዋል። ፈጥነው ካዘዝኋቸውም መንገድ ፈቀቅ ብለዋል። ቀልጦ የተሠራ ምስልም ለራሰቸው አድርገዋል።
13ከዚህም በተጨማሪ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ ይህ ሕዝብ አንገተ ደንዳና መሆኑን አይቼአለሁ።
14ስለዚህ አጠፋቸው፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች እደመስሳለሁ፥ አንተንም ከእነርሱ ለሚበረታና ለሚበዛ ሕዝብ አደርግሃለሁ።
15እኔም ተመልሼ ከተራራው ወረድሁ፥ ተራራውም በእሳት ይነድድ ነበር። ሁለቱም የቃል ኪንን ጽላቶች በእጆቼ ነበሩ።
16እናንተም እግዚአብሔር አምላካችሁን እንደበደላችሁ አየሁ። ለእናንተም ለራሳችሁ የጥጃ ምስል ሠርታችሁ ነበር። እግዚአብሔርም ካዘዛችሁ መንገድ ፈቀቅ ብላችሁ ነበር።
17ሁሉቱንም ጽላቶች ወስጄ፥ ከእጆቼ ጣልኋቸው። በዓይናችሁም ፊት ሰበርኋቸው።
18ስለ ሠራችሁት ኃጢአት ሁሉ፥ እርሱንም ለማስቆጣት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ከማድረጋችሁ የተነሣ እንደገና በእግዚአብሔር ፊት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ወደቅሁ፥ እንጀራም አልበላሁም፥ ውኃም አጠጣሁም ነበር።
19ምክንያቱም እግዚአብሔር ሊያጠፋችሁ ከተቆጣባችሁ ከቁጣውና ከመዓቱ የተነሣ ስለ ፈራሁ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር በዚያን ጊዜም ሰማኝ።
20እግዚአብሔርም አሮንን ሊያጠፋው እጅግ ተቆጣው፤ ስለ አሮንም ደግሞ በተመሳሳይ ሁኔታ ጸለይሁ።
21ያደረጋችሁትንም ኃጢአት ጥጃውን ወስድሁ በእሳትም አቃጠልሁት፥ አደቅዝቅሁትም፤ ዱቄትም እስኪሆን ድረስ ፈጨሁት። ዱቄቱንም ከተራራ በሚወርድ ወንዝ ጣልሁት።
22እግዚአብሔርንም በቀቤራ፥ በማሳህ፥ በምኞት መቃብርም አስቆጥታችሁት ነበር።
23እግዚአብሔርም ውጡ የሰጠኋችሁንም ምድር ውረሱ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁ ጊዜ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ትእዛዝ ላይ አመፃችሁ፥ በእርሱም አላመናችሁም፤ወይም ድምፁንም አልሰማችሁም።
24እናንተን ካወቅሁበት ቀን ጀምሮ በእግዚአብሔር ላይ ዓመፀኞች ነበራችሁ።
25እግዚአብሔር ያጠፋችሁ ዘንድ ስለ ተናገረ በእነዚያ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእግዚአብሔር ፊት ወደቅሁ።
26ጌታ በእግዚአብሔርም ፊት እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ በታላቅነትህና በኃያልነትህ ከግብፅ ያወጣቸውን፥ የተበዠሃቸውን ሕዝብህንና ርስትህን አታጥፋ ።
27አገልጋዮችህን አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም አስብ፤ የዚህን ሕዝብ ደንዳናነት፥ ክፋቱንና ኃጢአቱን አትመልከት፤
28እኛንም ያወጣህባት ምድር ሰዎች እግዚአብሔር ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ያገባቸው ዘንድ ስላልቻለ፤ ስለጠላቸውም በምድረ በዳ ሊገድላቸው አወጣቸው ይላሉ።
29እነርሱም በታላቅ ኃይልህ በጸነችውም ክንድህ ያወጣሃቸው ሕዛብህና ርስትህ ናቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።