1በሕይወት እንድትኖሩና እንድትበዙ፥ እግዚአብሔርም ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱአት ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዘትን ሁሉ ጠብቁ።
2እግዚአብሔር አምላካችሁ በልባችሁ ያለውን፥ ትእዛዘቱን መጠበቃችሁን ወይም አለመጠበቃችሁን ያውቅ ዘንድ ሊፈትናችሁና ትሁት እንድትሆኑ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራችሁን መንገድ ሁሉ አስቡ።
3አስጨነቃችሁ፥ እንድትራቡም አደረጋችሁ፥ እንዲሁም እናንተና ልጆቻችሁ፥ አባቶቻችምሁ የማያውቁአቸውን መና መገባችሁ። ይህም ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል እንጂ በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር ያስታውቃችሁ ዘንድ ነው።
4በእነዚህ አርባ ዓመታት ውስጥ የለበሳችሁት ልብስ አላረጀም፥ እግራችሁም አላበጠም።
5ሰውም ልጁን እንደሚገሥጽ እንዲሁም እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን እንደሚገሥጽ በልባችሁ አስቡ።
6በመንገዱም እንድትሄዱ እርሱንም እንድትፈሩ የእግዚአብሔ የአምላካችሁን ትእዛዝ ጠብቁ።
7እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደ መልካምና፥ ከሸለቆና ከኮረብታ የውኃ ጅረቶችና ፈሳሾች የሚመነጩ ምንጮች ወዳሉባት ምድር፤ ስንዴና ገብስ፤
8በለስና ሮማን፥ ወይራና ማር ወደ ሞሉባት፥
9ሳይጎድላችሁ እንጀራ ወደምትበሉባት ምድር፥ አንዳችም ወደማታጡባት፥ ድንጋይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተራራዋም መዳብ ወደሚማስባት ምድር አመጣችሁ።
10እናንተም ትበላላችሁ፥ ትጠግባላችሁ፥ ስለ ሰጣችሁም ስለ መልካሚቱ ምድር እግዚአብሔር አምላካችሁን ትባርካላችሁ።
11ዛሬ እኔ እናንተን የማዝዛውን ትእዛዘትን፥ ድንጋጌዎችንና ሥርዓቶችን ባለመጠበቅ እግዚአብሔር አምላካችሁን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ።
12ከበላችሁና ከጠገባችሁ ሙሉም ከሆናችሁ በኋላ መልካምም ቤት ሠርታችሁ በዚያ መኖር ከጀመራችሁ በኋላ እንዳትረሱ ተጠንቀቁ።
13የላምና የበግ መንጋ ከበዛላችሁ በኋላ፥ ብራችሁና ወርቃችሁም፥ ያላችሁም ሁሉ ከበዛላችሁ በኋላ፥
14ልባችሁ እንዳይኮራ ከግብፅም ምድር ከባርነት ቤት ያወጣችሁን እግዚአብሔርን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ።
15መርዛማ እባብና ጊንጥ፥ውኃ በሌለባትና ጥማትም ባለባት በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራችሁን፥ ከዐለት ድንጋይም ውኃን ያወጣላችሁን፥
16በመጨረሻም ዘመን መልካም ያደርግላችሁ ዘንድ ሊፈትናችሁ ሊያዋርዳችሁም አባቶቻችሁ ያላውቁትን መና በምድረ በዳ ያበላችሁን እግዚአብሔር አምላካችሁን እንዳትረሱ፥
17በልባችሁም፦ ጉልባታችን የእጃችን ብርታት ይህን ሀብት አመጣልን እንዳትሉ።
18ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአባቶቻችሁ የማለላችሁን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ሀብት ለማከማቸት ጉልበት ሰጥቶአችኋል፥ እግዚአብሔር አምላካችሁን አስቡ።
19አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ብትረሳ ሌሎችንም አማልክት ብትከተል፥ ብታመልካቸውም፥ ብትሰግድላቸውም ፈጽሞ እንደምትጥፉ እኔ ዛሬውኑ እመሰክርባችኋልለሁ።
20የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ቃል ስላልሰማችሁ እግዚአብሔር ከፍታችሁ እንደሚያጠፋቸው እንደ አሕዛብ እንዲሁ እናንተ ትጠፋላችሁ።