1እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትወሱአት ወደምትገቡባት ምድር ባመጣችሁ ጊዜ፤ ከፊታችሁም ብዙ አሕዛብ ከእናንተ የበለጡትንና የበረቱትን ሰባቱን አሕዛብ ኬጢያዊውን፥ ጌርጌሳውያንን፥ አሞራውያንብ፥ ከነዓናውያንን፥ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውንና ኢያቡሳዊውን አወጣቸው።
2እንዲሁም ጦርነት በገጠማችሁ ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁ ድል በሰጣችሁ ጊዜ፥ እነርሱን ማጥቃት አለባችሁ፥ ከዚያም ፈጽሞ ማጥፋት ይኖርባችኋል።
3ከእርሱም ጋር ቃል ኪዳን ማድረግ ወይም ምሕረት አለማድረግ፥ ከእነርሱም ጋር አትጋቡም፤ ሴት ልጆቻችሁን ለወንድ ልጆቻቸው አትስጡ፥ ሴት ልጃቸውንም ለወንድ ልጃችሁ አትውሰዱ።
4ሌሎች አማልክትን እንዳያመልኩ፥ ልጆቻችሁን እኔን እንዳይከተሉ ይመልሳሉ፥ የእግዚአብሔርም ቁጣ ይነድድባችኋል ፈጥኖም ያጠፋችኋል።
5በእነርሱ ላይ የምታደርጉባቸው እንደዚህ ነው፥ መሠዊያቸውን አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቁረጡ፥ የተቀረጸውን ምስላቸውንም በእሳት አቃጥሉ።
6እናንተ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የተለያችሁ ሕዝብ ናችሁ። እግዚአብሔር አምላካችሁ በምድርም ገጽ ከሚኖሩ ሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ መረጣችሁ።
7እግዚአብሔርም የወደዳችሁና የመረጣችሁ ከአሕዛብ ሁሉ በቁጥር ስለ ባዛችሁ አይደለም፤ እናንተ ከአሕዛብ ሁሉ በቁጥር ጥቂቶች ነበራችሁና፤
8ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ወደዳችሁ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን ቃል ኪዳን ስለ ጠበቀ ነው። እግዚአብሕር በጽኑ እጅ ያወጣችሁ፥ ከባሪነትም ቤት ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ ያዳናችሁ ለዚህ ነው።
9ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ እርሱ አምላክ እንደ ሆነ ለሚወድዱትና ትእዛዘትንም ለሚጠብቁት፥ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆን እወቁ፥
10ነገር ግን የሚጠሉትን በፊታቸው ሊያጠፋቸው ብድራትን ይመልሳል፤እንዲሁም ብድራትን ለመመለስ አይዘገይም።
11እንግዲህ ታደርጉት ዘንድ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዘት፥ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎችን ጠብቁ።
12እነዚህን ድንጋጌዎችን ሰምታችሁ ብትጠብቁና ብታደርጉ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ለአባቶቻችሁ የማለላችውን ቃል ኪዳን በታማኝነት ለእናንተ ይጠብቅላችኋል።
13እርሱም ይወድዳችኋል፥ ይባርካችኋል፥ ያበዛላችኋል፤ እንዲሁም የሆዳችሁንና የምድራችሁን ፍሬ፥ እህላችሁን፥ ወይናችሁን፥ ዘይታችሁን፥ የከብቶቻችሁንና የበጎቻችሁን መንጋ ይባርካል።
14ከአሕዛብም ሁሉ ይልቅ የተባረካችሁ ትሆናላችሁ፥ በሰዎቻችሁና በከብቶቻችሁ ዘንድ ወንድ ወይም ሴት ቢሆኑ መካን አይሆንባችሁም።
15እግዚአብሔርም ሕመምን ሁሉ ከእናንተ ያርቃል፥ የምታውቁአችሁን ክፉውን የግብፅ በሽታ ሁሉ በእናንተ ላይ አያደርስባችሁም በሚጠሉባችሁም ሁሉ ላይ ያመጣባቸዋል።
16እግዚአብሔር አምላካችሁም በእጃችሁ አሳልፎ የሚሰጣችሁን አሕዛብ ሁሉ ታጠፋቸዋላችሁ፥ ዓይናችሁም አያዝኑላቸውም። ወጥመድ እንዳይሆኑባችሁአማልክታቸውንም አታምልኩአችሁም።
17በልብህም እንዲህ ብትሉ፦ እነዚህ አሕዛብ ከእኔ ይልቅ ይበዛሉና አወጣቸው ዘንድ እንዴት እችላለሁ?
18እግዚአብሔር አምላካችሁ በፈዖንና በግብፅ ሁሉ ያደረገውን ትዝ ስለሚላችሁ እነሱን አትፍራቸው፤
19አምላካችሁ እግዚአብሔር ዓይናችሁ ፊት ታላቅን መቅሠፍት፥ ምልክትንና ተአምራትን በማድረግ በጸናችው እጅ፥ በተዘረጋውም ክንድ አወጣችሁ። እንዲሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተ በምትፈሩአችሁ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ያደርጋል።
20በተጨማሪም እግዚአብሔር አምላካችሁ ራሳቸውን የተሸሸጉትን ከፊታችሁ እስኪጠፉ ድረስ በመካከላችው ተርብ ይሰድድባቸዋል።
21እግዚአብሔር አምላካችሁ ታላቅና የተፈራ አምላክ በመካከላችሁ ስላለ፤ ከእነርሱ የተነሣ አትደንግጡ።
22እግዚአብሔር አምላካችሁ እነዚህን አሕዛብ ጥቂት በጥቂት ከፊታችሁ ያወጣቸዋል። ሁሉንም አንድ ጊዜ አታጠፋቸውም፤ ወይም የዱር አራዊት በዙሪያችሁ በጣም ብዙ ይሆናሉ።
23እግዚአብሔር አምላካችሁ እነርሱን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ እስኪጠፉም ድረስ በታላቅ ድንጋጤ ያስደነግጣቸዋል።
24ነገሥታታቸውንም በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች ታጠፋቸዋላችሁ። እስክታጠፏቸውም ድረስ ማንም በፊታችሁ ይቆም ዘንድ አይችልም።
25የተቀረጸውንም የአማልክታቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላላችሁ፤ ከብር ወይም ከወርቅ የተሠሩትንም ለራሳችሁ ለመውሰድ አትመኙ፥ በእግዚአብሔር በአምላካችሁም ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመዱበት ከእርሱ ምንም አትውሰዱ።
26እንደ እርሱም ርጉም እንዳትሆኑ ርኩስን ነገር ወደ ቤታችሁ አታግቡ ለማምለክም አትቃጡ፥ ለጥፋት የተለየ ስለ ሆነ ፈጽሞ ተጸየፉት፥ ጥሉትም።