መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 6

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዮርዳኖስ ማዶ በምትውርሱአት ምድር የምትጠብቃችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳስተምራችሁ ያዘዘኝ እነዚህ ትእዛዘት፥ ሥርዓትና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤
2እኔ የማዛችሁን ሥርዓትንና ትእዛዘትን በመጠበቅ እናንተ፥ ልጆቻችሁ፥ የልጅ ልጆቻችሁም በዘመናችሁ ዕድሜአችሁ እንዲረዝም እግዚአብሔር አምላካችሁን አክብሩ።
3እንግዲህ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ መልካምም እንዲሆንላችሁ የአባቶቻችሁም አምላክ እግዚአብሔር ተስፋ እንደሰጣችሁ ወተትና ማር በምታፈስሰው ምድር እጅግ እንድትበዙ ነው።
4እስራኤል ሆይ፥ ስማ፥ እግዚአብሔር አምላካችን አንድ እግዚአብሔር ነው።
5እናንተም እግዚአብሔር አምላካችሁን በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁ፥ በፍጹም ኃይላችሁ ውደዱ።
6እኔም ዛሬ እናንተን የማዝዘው ቃል በልባችሁ ይሁን፤
7በቤታችሁም ስትቀመጡ፥ በመንገድም ስትሄዱ፥ ስትተኙም፥ ስትነሡም፥ ልጆቻችሁን አስተምሩአቸው።
8በእጃችሁም ምልክት አድርጋችሁ እሰሩት፥ በዓይኖቻችሁም መካከል እንደክታብ ይሁንላችሁ።
9በቤታችሁም መቃኖች በደጃፋችሁም በሮች ላይ ጻፉት።
10እግዚአብሔር አምላካችሁ ለእናንተ ሊሰጣችሁ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደ ማለላቸው ምድር ባገባችሁ ጊዜ፥ ያልሠራሃችኋቸውን ታላላቅና መልካም ከተሞች፥
11በመልካም ነገሮች ሁሉ የተሞሉ ቤቶች ያልማስሃችኋቸውን የተማሱ ጉድጓዶች፥ ያልተከልሃችኋቸውን ወይንና ወይራ በሰጣችሁ ጊዜ፥
12በበላችሁና በጠገባችሁ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣችሁን እግዚአብሔርን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ።
13አምላካችሁን እግዚአብሔርን አክብሩ፤ እርሱንም አምልኩት በስሙም ማሉ።
14በዙሪያችሁ ያሉትን አሕዛብ የሚያመልኩአቸውን ሌሎችን አማልክት ፍለጋ እንዳትሄዱ፥ እንዳከተከተሉ፤
15ምክንያቱም በመካከላችሁ ያለው እግዚአብሔር አምላካችሁ ቀናተኛ አምላክ ስለሆነ፥ ቁጣው እንዳይነድባችሁና ከምድር ገጽ እንዳያጠፋችሁ ተጠንቀቁ።
16በማሳህ እንደተፈታተናችሁት እግዚአብሔር አምላካችሁን አትፈታተኑት።
17ያዘዝኋችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዘትንና ሥርዓቱን አጥብቃችሁ ጠይቁ።
18መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ቅኑንና መልካሙን ነገር አድርጉ፤ እግዚአብሔርም ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥
19እግዚአብሔርም እንደተናገረ ጠላቶቻችሁን ሁሉ ከፊታችሁ ያወጣላችሁ ዘንድ።
20በኋለኛው ዘመንም ልጆቻችሁ እንዲህ ብለው በጠየቃችሁ ጊዜ፦ እግዚአብሔር አምላካችን ያዘዛችሁ የቃል ኪዳን ድንጋጌዎች፥ ሥርዓትና ሌሎችስ ድንጋጌዎች እነዚህ ምንድን ናቸው?
21እናንተም ለልጆቻችሁ እንዲህ በሉአችው፦ በግብፅ አገር የንጉሥ ፈርዖን አገልጋዮች ነበርን፥ እግዚአብሔርም በጽኑ እጅ ከግብፅ አወጣን፥
22እግዚብብሔርም በግብፅና በፈርዖን፥ በቤቱም ሁሉ ላይ በዓይናችን ፊት ታላቅና ክፉ፥ ምልክትና ተአምራትን አደረገ።
23ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር አምጥቶን እርስዋን ይሰጠን ዘንድ ከዚያ አወጣን።
24እንደ ዛሬም በሕይወት እንዲያኖረን ሁልጊዜም መልካም እንዲሆንልን እግዚአብሔር አምላካችንን እንፈራ ዘንድ ይህችንም ሥርዓት ሁሉ እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር አዘዘን።
25እርሱም እንዳዘዘን በእግዚአብሔር በአምላካችን ፊት እንፈጽመው ዘንድ ይህን ትእዛዝ ሁሉ ብንጠብቅ ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።