መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 5

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሙሴም የእስራኤል ልጆችን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦እስራኤል ሆይ፥ እንድትማሩአቸውና እንድትጠብቁአቸው ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራውን ሥርዓቶችንና ድንጋጌዎችን ስሙ።
2እግዚአብሔር አምላካችን ከእኛ ጋር በኮሬብ ቃል ኪዳን አድርጎአል።
3እግዚአብሔር ከአባቶቻችን ቃል ኪዳን አላደረገም ዛሬ በሕይወት ካለነው ከእኛ ጋር ነው።
4እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ፊት ለፊት በተራራው ላይ በእሳት መካከል ተናገረ፥
5(በዚያን ጊዜ ከእሳቱም የተነሣ ፈርታችሁ ወደ ተራራው ባልቀረባችሁ ጊዜ ቃሉን ልገልጥላችሁ በእግዚአብሔርና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር) ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦
6ከባርነት ቤት፥ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
7ከእኔ በቀር በፊቴ ሌሎች አማልክት አይኑራችሁ።
8በላይ በሰማይ፥ወይም በታች በምድር፣ወይም ከምድርም በታች በውኃ፥ ማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውን ምስል ለራሳችሁ አታድርጉ።
9እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቀናተኛ ስለሆንኩ ለአማልክት አትስገዱላቸው፥ ወይም እነርሱን አታገልግሉአችሁ። በሚጠሉኝ ላይ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የእባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ ቅጣትን ያመጣል፥
10ለቃል ኪዳኔም ታማኝነት ለሚያሳዩኝና ለሚወዱኝ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቀናተኛ አምላክ ነኝ።
11የአምላካችሁን ስም በከንቱ አትጠቀሙ፥ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠቀመውን ከበደል አያነጻውምና።
12እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ የሰንበትን ቀን ትቀድሱት ዘንድ ጠብቁ።
13ስድስት ቀን ሥሩ ተግባራችሁንም ሁሉ አድርጉ፤
14ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ሰንበት ነው። እናንተ እንደምታርፉ ሁሉ አገልጋያችሁና የቤት ሠራተኛችሁ ያርፉ ዘንድ እናንተ ወንድ ልጆቻችሁ፥ ሴት ልጆቻችሁም ፥ አገልጋዮቻችሁ፥ የቤት ሠራተኞቻችሁም በፊታችሁ፥ አህዮቻችሁም፥ ከብቶቻችሁም፥ ሁሉ በደጆቻችሁ ውስጥ ያለው እንግዳም ጭምር በሰንበት ምንም ሥራ አትሥሩ።
15እናንተም በግብፅ በሪያ እንደ ነበራችሁ አስቡ፥ እብዚአብሔር አምላካችሁ በጸናች እጅና በተዘረጋች ክንድ ከዚያ አውጣችሁ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ የሰንበትን ቀን ትጠብቁ ዘንድ አዘዛችሁ።
16እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሰጣችሁ ምድር ላይ ዕድሜአችሁ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንላችሁ አባታቸውንና እናታቸውን አክብሩ።
17አትግደሉ።
18አታመንዝሩ።
19አትስረቁ።
20በባልንጀራችሁ ላይ በሐሰት አትመስክሩ።
21የባልንጀራችሁን ሚስት አትመኙ፤ የባልጀራችሁን ቤት፥ እርሻውንም፥ አገልጋዩንም፥ የባልጀራችሁንም በሬውንም፥ አህያውንም፥ ከባልጀራችሁ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኙ።
22እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳትና በደመና በጨለማም ውስጥ ሆኖ በታላቅ ድምፅ፥ እነዚህን ቃሎች ለጉባኤአችሁ ሁሉ ከተናገረው ምንም አልጨመረም። በሁለቱም የድንጋይ ጽላችቶች ላይ ጻፋቸው ለእኔም ሰጠኝ።
23ተራራው በእሳት ሲነድድ ከጨለማው ውስጥ ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ እናንተ የነገዶቻችሁ አለቆች ሽማግሌዎቻችሁም ወደ እኔ ቀረባችሁ።
24አላችሁም፦ እነሆ አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፥ ከእሳትም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔርም ከሰዎች ጋር ሲነጋገር ሰዎችም በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል።
25አሁን እንግዲህ ይህች ታላቂቱ እሳት ታቃጥለናለችና ለምን እንሞታለን? እኛ የእግዚአብሔርን የአምላካችንን ድምፅ ደግሞ ብንሰማ እንሞታለን።
26ከሥጋ ለባሽ ሁሉ እኛ እንደ ሰማን በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሕያው አምላክን ድምፅ ሰምቶ በሕይወቱ የኖረ ማን ንው?
27አንተ ቅረብ፤ እግዚአብሔር አምላካችን የሚለውን ሁሉ ስማ፤ እግዚአብሔር አምላካችንም ለአንተ የሚናገረውን ሁሉ ለእኛ ንገረን፤ እኛም ሰምተን እናደርገዋለን አላችሁ።
28በተናገራችሁኝም ጊዜ እግዚአብሔር የእናንተን ቃል ሰማ። እግዚአብሔርም አለኝ፦ይህ ሕዝብ የተናገሩህን ቃል ሰምቼአለሁ፤ የተናገሩትም ሁሉ መልካም ነው።
29ለእነርሱ ለዘላለምም ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ፥ እንዲፈሩኝ፥ ሁልጊዜም ትእዘዜን ሁሉ እንዲጠብቁ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው በነበራቸው!
30ሄደህ እንዲህ በላቸው፦ ወደ ድንኳናችሁ ተመለሱ።
31አንተ ግን በዚህ በእኔ ዘንድ ቁሙ፥ ርስት አድርጌ በምሰጣቸውም ምድር ላይ ያደርጉአት ዘንድ የምታስተምራቸውን ትእዛዜንና ሥርዓቴን፥ ድንጋጌንም ሁሉ እነግርሃለሁ።
32ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ፥ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ።
33በሕይወት እንድትኖሩ መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሄዱ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።