መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1አሁንም እስራኤል ሆይ እንድታደርጉአቸው፥ በሕይወት እንድትኖሩና የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ሄዳችሁ እንድትወርሱ የማስተምራችሁን ሥርዓትንና ድንጋጌን ስሙ።
2እኔ የማዛችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዛትን ሁሉ ሳትጨምሩና ሳታጎሉ ትጠብቃላችሁ።
3ከብዔልፌጎርም የተነሣ፥ ብዔልፌጎርን የተከተሉትን ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከመካከላችሁ እንዳጠፋ ዓይኖቻችሁ አይተወል።
4እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁን የተከተላችሁ እስከ ዛሬ ድረስ በሕይወት አላችሁ።
5እነሆ እናንተ ለመውረስ በምትሄዱባቸው ምድር ሰዎች መካከል ታደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር አምላኬ እንዳዘዘኝ ሥርዓትንና ድጋጌን አስተማርኋችሁ።
6ስለዚህ ጠብቁአቸው፥ አድርጉአቸውም፤ ምክንያቱም ስለእነዚህ ሥርዓት ሰምተው፦ 'በእውነት ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢብና አስተዋይ ሕዝብ ነው' በሚሉ ሰዎች ሁሉ ፊት ይህ ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ነው።
7በምንጠራው ጊዜ ሁሉ እንደምቀርበን እንደ እግዚአሔር አምላካችን፥ ወደ እነርሱ የቀረበ አምላክ ያለው ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?
8ዛሬ በፊታችሁ እንደማኖራው ሥርዓት ሁሉ ጽድቅ የሆነው ሥርዓትና ድንጋጌ ያለው ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?
9ዓይኖቻችሁ ያዩትን ነገር እንዳትረሱ በሕይወታችሁም ዘመን ሁሉ ከልባችሁ እንዳይጠፋ ብቻ አስታውሉ፤በጥንቃቄም ራሳችሁን ጠብቁ። እግዚአብሔር፦ ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ በምድርም በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩ ዘንድ ልጆቻቸውንም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን አሰማቸዋለሁ ብሎ እንደተናገረኝ፥
10በእግዚአብሔር አምላካችሁ ፊት በኮሬብ በቆማችሁ ቀን እንደሰማችሁ፥ይህን በልጆቻችሁና በልጅ ልጆቻችሁ ዘንድ እንዲታውቅ አድርጉ።
11እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር። እስከ ሰማይም መካከል ድረስ እሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፤ ጨለማና ደመና ድቅድቅ ጨለማ ነበረ።
12እግዚአብሔርም በእሳት ውስጥ ሆኖ ተናገራችሁ፤ ድምፅን በቃል ሰማችሁ መልክን ግን አላያችሁም፤ ድምፅን ብቻ ሰማችሁ።
13ታደርጉትም ዘንድ ያዘዛችሁን ቃል ኪዳን አሥሪቱን ቃላት አስታወቃችሁ። በሁለቱም በድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው።
14በዚያን ጊዜ ትወርሱአት ዘንድ በምትሄዱባት ምድር የምታዳርጉትን ሥርዓትና ድንጋጌ አስተምራችሁ ዘንድ እግዚአብሔር አዘዝኝ።
15እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት መካከል ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክን ከቶ እንዳላያችሁ፤ለራሳችሁ እጅግ ተጠንቀቁ።
16የማናቸውንም ፍጥረት ምሳሌ የተቀረጸውን ምስል በወንድ ወይም በሴት፥
17ወይም በማናቸውም በምድር ባለው በዱር እንስሳ መልክ፥ ወይም ከሰማይም በታች የሚበርረውን የወፍን ምሳሌ፥
18ወይም በምድር ላይ የሚሳበውን ሁሉ ምሳሌ፥ ወይም ከምድርም በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረውን የዓሣን ሁሉ ምሳሌ በማድረግ እንዳትረክሱ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
19ዓይኖቻችሁን ወደ ሰማይ አንሥታችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት ሕዝብ ሁሉ የመደባቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊት ሁሉ ባያችሁ ጊዜ አምልኮና ስግደት በማቅረብ እንዳትስቱ ተጠንቀቁ።
20እናንተን ግን እግዚአብሔር እንደ ዛሬው ሁሉ የርስቱ ሕዝብ ትሆኑለት ዘንድ ወስዶ ከብረት እሳት ከግብፅ አወጣችሁ።
21ከዚህም በተጨማሪ እግአብሔር በእናንተ ምክንያት ተቆጣኝ፣ ዮርዳኖስንም እንዳልሻገር ፥እግዚአብሔር አምላካችሁም ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ወደመልካሚቱ ምድር እንዳልገባ ማለ።
22እኔ ግን በዚህች ምድር እሞታለሁ፥ ዮርዳኖስንም አልሻገርም፥ እናንተ ግን ትሻገራላችሁ፥ ያችንም መልካሚቱን ምድር ትወርሳላችሁ።
23እግዚአብሔር አምላካችሁም ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ እግዚአብሔር አምላካችሁም የከለከለውን በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ።
24እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚበላ እሳት ቀናተኛም አምላክ ነውና።
25ልጆችን የልጅ ልጆችንም በወለዳችሁ ጊዜ፥ በምድሪቱም ብዙ ዘመን በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ በማናቸውም ምስል የተቀረጸውን ምስል አድርጋችሁ በረከሳችሁም ጊዜ፥ ታስቆጡትም ዘንድ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር በሠራችሁ ጊዜ ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ፤
26ከምትገቡባት ምድር እንደምትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆኑ እጠራለሁ፤ ዘመናችሁም አይረዝምም፥ ፈጽሞም ትጠፋላችሁም።
27እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፥ በአሕዛብም መካከል ጥቂት ትሆናላችሁ፥እግዚአብሔርም ያስወጣችሁኋል።
28በዚያም የማያዩትን፥ የማይሰሙትን፥ የማይበሉትን፥ የማያሸቱትንም በሰው እጅ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን አማልክት ታመልካላችሁ።
29ነገር ግን ከዚያ እግዚአብሔር አምላካችሁን ትሻላችሁ፤ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁም የፈለጋችሁት እንደ ሆነ ታገኛላችሁ።
30በተጨነቃችሁና ይህም ሁሉ በደርሰባችሁ ጊዜ በዘመኑ ፍጻሜ ወደ እግዚአብሔር አምላካችሁ ትመለሳላችሁ፥ ድምፁንም ትሰማላችሁ።
31እግዚአብሔር አምላካችሁ መሓሪ አምላክ ነውና፥ አይተዋችሁም፥ አያጠፋችሁምም፤ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን ቃል ኪዳኑን አይረሳም።
32እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ከሰማይ እስከ ዳርቻዋ ድረስ ከቶ እንዲህ ያለ ታላቅ ነገር ወይም እንደ እርሱ ያለ ተሰምቶ እንደ ሆነ ከእናንተ በፊት የነበረውምን የቀደመውን ዘመን ጠይቁ።
33እናንተ ከእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የእግዚአብሔርን ድምፅ እንደሰማችሁት ሌላ ሕዝብ ሰምቶአልን?
34ወይም እግዚአብሔር አምላካችሁ በዓይናችሁ ፊት በግብፅ ለእናንተ እንዳደረገው ሁሉ በፈተናና በተአምራት በድንቅና በጦርነት በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ በታላቅም ማስፈራት እግዚአብሔር ከሌላ ሕዝብ መካከል ለራሱ ሕዝብን ይወስድ ዘንድ በዐይናችሁ ፊት አድርጎ ያውቃልን?
35እግዚአብሔርም አምላክ እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ የተገለጡ ናቸው፤ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም።
36ያስተምራችሁ ዘንድ ከሰማይ ድምፁን አሰማችሁ፥ በምድርም ላይ ታላቁን እሳት አሳያችሁ፤ ድምፁንም ከእሳት መካከል ሰማችሁ።
37አባቶቻችሁን ስለወደደ ከእነሱም በኋላ ዘራቸውን መረጠ፥ ከግብፅም በታላቁ ኃይል በመገኘቱ አወጣችሁ፤
38ዛሬ እንደ ሆነ ከእናንተ የጸኑትን ታላላቆችን አሕዛብ ከፊታችሁ ሊስያወጣቸውና ለእናንተም ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ሊሰጣችሁ ነው።
39እንግዲህ እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር አምላክ እንደ ሆነ፥ ሌላም እንደሌለ ዛሬ እወቁ፤ በልባችሁም ያዙት።
40ለእናንተ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችሁም ለዘላለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።
41በዚያን ጊዜ ሙሴ አስቀድሞ ጠላት ያልነበረውን ሰው ሳያውቅ የገደለው ሰው
42ወደ አንዲቱ ሸሽቶ በሕይወት ይኖር ዘንድ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሦስት ከተሞች መረጠ።
43ከተሞቹም ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ቦሶር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።
44ሙሴ በእስራኤል ልጆች ፊት ያኖራት ሕግ ይህች ናት።
45ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ከወጡ በኋላ እግዚአብሔር የተናገራቸው የቃል ኪዳን ድንጋጌዎች፥ ሥርዓቶች፥ ሌሎችም ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤
46በቤተ ፌጎር አንጻር ባለው ሸለቆ፥ በሴዎን ምድር፣ ከዮርዳኖስ በስትምሥራቅ፥ በነበሩበት ጊዜ፥ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብፅ በወጡበት ጊዜ ድል ያደረጉአቸው በሐሴቦን ተቀምጦ በነበረው በአራውያን ንጉሥ ነበር።
47የእርሱንና የባሳንን ንጉሥ የዐግን ምድር ወሰዱ፤
48በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ የነበሩትን የሁለቱ የአሞራያን ነገሥታት እነዚህ ናቸው። ይህም ምድር ከአርኖን በአሮዔር ዳርቻ እስከ ሴዎን ተራራ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ፥
49በምሥራቅ በኩል የዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ሜዳ በሙሉ ጨምሮ በዮርዳኖስ ማዶ ከፈስጋ ተራራ በታች ያለውን ዓረባ ሁሉ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ ያለው ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።