መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 33

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ ከመሞቱ በፊት ለእስራኤላውያን የሰው ቃለ ቡራኬ ይህ ነው።
2እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ከሲና መጣ፤ በእነርሱም ላይ ከሴይር እንደ ማለዳ ፀሐይ ወጣ፤ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፤ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጣ፤ በስተቀኙ የሚነድ እሳት ነበር።
3በእርግጥ ሕዝቡን የምትወድ አንተ ነህ፤ ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ውስጥ ናቸው። ከእግርህ ሥር ሁሉ ይስገዳሉ፤ ከአንተ ትእዛዝ ይቀበላሉ፤
4ይህ ሙሴ የሰጠን ሕግ የያዕቆብ ጉባኤ ርስት ነው።
5የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ጋር ሆነው፤ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፤ እግዚአብሔር በይሹሩን ላይ ንጉሥ ነበር። ሮቤል በሕይወት ይኑር፤ አይሙት።
6የወገኖቹ ቁጥርም ጥቂት ይሁን።
7ስለይሁዳ የተነገረው ባትኮት ይህ ነው። ሙሴም እንዲህ አለ፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ የይዳን ጩኸት ስማ፤ ወደ ወገኖቹም እንደገና አምጣው። ስለእርሱ ተዋጋለት፤ አቤቱ ከጠላቶቹ ጋር ሲዋጋ ረዳቱ ሁን!
8ስለ ሌዊም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ቱሚምህና ኡሪምህ ለምትወደው ሰው ይሁን፤ ማሳህ በተባለው ቦታ ፈተንኸው፤ በመሪባም ውሃ ከእርሱ ጋር ተከራከርህ።
9ስለ አባቱና ስለ እናቱ ሲናገርም፤ ስለ እነርሱ ግድ የለኝም አለ። ወንድሞቹን አልለያቸውም፤ ልጆቹንም አላወቃቸውም። ስለቃልህ ከለላ አደረገ፤ ኪዳንህንም ጠበቀ።
10ሥርዓትህን ለያዕቆብ፤ ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራል። ዕጣን በፊትህ፤ ያሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ በምሠዊያህ ላይ ያቀርባል።
11እግዚአብሔር ሆይ፥ ኃይሉን ሁሉ ባርክለት፤ በእጁ ሥራ ደስ ይበልህ፤ በእርሱ ላይ የሚነሡበትን ሽንጣቸውን ቁረጠው፤ ጠላቶቹንም እንደገና እንዳይነሡ አድርገህ ምታቸው።
12ሙሴ ስለ ብንያም እንዲህ አለ፦ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ በእርሱ ተጠብቆ በሰላም ይረፍ፤ ቀኑን ሙሉ ይጋርደዋልና፤ እግዚአብሔር የሚወደውን ሰው በትክሻዎቹ መካከል ያርፋል።
13መሴ ስለ ዮሴፍ ደግሞ እንዲህ አለው፦ እግአብሔር ምድሩን ይባርክ፤ ውድ በሆኑ ሰማያዊ ነገሮች፥ ጠል ከላይ በማውረድ፤ ከታች በጥልቅ በተንጣለለው ነገሮች ይባርክ።
14ከፀሐይ በተሠሩ ምርጥ ፍሬ፤ ጨረቃም በምትሰጠው እጅግ መልካም ነገር፤
15ከጥንት ተራሮች በተገኘ ምርጥ ስጦታ፤ በዘላለማዊ ኮረብቶች ፍሬያማነት ይባርክ።
16ምድር በምታስገኘው ውድ ስጦታና በብዛት በቁጥቋጦም ውስጥ በነበረው በእርሱ መልካም ሞገስ። እነዚህ ሁሉ በረከቶች በወንድሞቹ መካከል ገዥ በሆነው፤ በዮሴፍ ራስ ላይ ይውረድ።
17በግርማው እንደ በኩር ኮርማ ነው፤ ዘንዶቹም የጎሽ ቀንዶች ናቸው። በእነርሱም ሕዝቦችን በምድር ዳርቻ ላይ ያሉትን እንኳ ሳይቀር ይወጋል፤ እነርሱም የኤፍሬም አሥር ሺዎቹ ናቸው።
18ስለ ዛብሎንም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ዛብሎን ሆይ፥ ወደ ውጭ በመውጣትህ፤ አንተም ይሳኮር በድንኳኖችህ ውስጥ ደስ ይበልህ።
19እነርሱም አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፤ በዚያም የጽድቅን መሥዋዕት ያቀርባሉ። እነርሱም ከባሕሮች በአሸዋ ውስጥ የተደበቀውን ሀብት ያወጡበታል።
20ስለ ጋድም ሙሴ እንዲህ አለ፦ የጋድን ግዛት የሚያሰፋ የተባረከ ይሁን! ክንድንና ራስን በመገነጣጠል፤ ጋድ እንደ አንበሳ በዚያ ይኖራል።
21ለአለቃን ድርሻ ሆኖ የተጠበቀለትን ለም የሆነውን መሬት ለራሱ መረጠ። ከሕዝብ አለቆች ጋር መጣ። በእስራኤል ላይ የወሰነውን የእግዚአብሔርን ሥርዓትንና ፍርዱን ፈጸመ።
22ስለ ዳንም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ዳን ከባሳን ዘሎ የሚወጣ፤ የአንበሳ ደቦል ነው።
23ስለ ንፍታሌምም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ንፍታሌም በእግዚአብሔር ሞገስ ረክቶአል፤ በበረከቱም ተሞልቶአል፤ ባሕሩንና የደቡብን ምድር ይወርሳል።
24ስለ አሴርም ሙሴ እንዲህ አለ፦ አሴር ከሌሎች ልጆች ይልቅ የተባረከ ይሁን፤ በወንሞቹ ዘንድ ተወዳጅ ይሁን፤ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ።
25በዘመንህና ደህንነትህ ሁሉ የደጃፍህ መቀርቀሪያ ብረትና ናስ ይሁን፤ ኃይልህም በዘመንህ ሁሉ ይኖራል።
26አንተን ለመርዳት በሰማያት ላይ በግርማው በደመናትም የሚገሠግሥ፤ እንደ ይሽሩን አምላክ ያለ ማንም የለም።
27ዘላለማዊ አምላክ መኖርያህ ነው፤ የዘላለም ክንዶቹም ከበታችህ ናቸው፤ እርሱን አጥፋው! በማለት፤ ጠላትህን ከፊትህ ያስወግደዋል።
28ስለዚህ እስራኤል በሰላም ይሆራል።። የሰማያት ጠል በሚወርድበት፤ እህልና የወይን ጠጅ ባለበት ምድር የያዕቆብን ምንጭ የሚነካው የለም።
29እስራኤል ሆይ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ እግዚአብሔር ያዳነው ሕዝብ፤ እንዳንተ ያለ ማን ነው? እርሱ ጋሻህና ረዳትህ፤ የክብርህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህ ተሸብራው በፍርሃት፤ ወደ አንተ ይመጣሉ። አንተም ከፍታቸውን መረማመጃ ታደርጋለህ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።