መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 34

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሙሴ ከሞዓብ ሜዳ ተነሥቶ ለኢያሪኮ ትይዩ ወደ ሆነው ፈስጋ ጫፍ ወደ ናባው ተራራ ሄደ። በዚያም እግዚአብሔር ከገለዓድ እስከ ዳን ያለውን ምድሪቱን ሁሉ፤
2ንፍታሌምን ሁሉ፥የኤፍሬምንና የምናሴን ግዛት እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ያለውን የይሁዳን ምድር ሁሉ አሳየው፤
3ኔጌብንና የዘንባባ ከተማ ከሆነችው ከኢያሪኮ ሸለቆ እስከ ዞዓር ያለውን ምድር ሁሉ አሳየው።
4ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለአብርሃም፥ ለይስሐንና ለያዕቆብ ለአባቶቻችሁ እሰጣለሁ ብዬ በመሐላ ቃል የገባሁላቸው ምድር፥ በዐይንህ እንድታያት አድርጌአለሁ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትሻገርም አለው።
5እግዚአብሔር እንደተናገረው የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሞዓብ ምድር ሞተ።
6በሞዓብ ምድር በቤተ ፌጎር ፊት ለፊት ባለው ሸለቆ እግዚአብሔር ቀበረው፤ ይሁን እንጂ መቃብሩ የት እንደ ሆን እስከ ዛሬ ማንም አያውቅም።
7ሙሴ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሃያ ዓመት ነበር፤ ሆኖም ዐይኑ አልፈዘዘም፤ ጉልበቱም አልደከመም።
8የልቅሶውና የሐዘኑ ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ እስራኤላውያን በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን አለቀሱለት።
9ሙሴ እጆቹን ጭኖበት ስለ ነበር የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ መንፈስ ተሞላ። ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ አደመጡት፤ እግዚአብሔር ሙሴን አዞት የነበረውንም ሁሉ አደረገ።
10እግዚብብሔር ፊት ለፊት ያወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል አልተነሣም።
11እግዚአብሔር ልኮት እነዚያን ታምራዊ ምልክቶችና ድንቆች ሁሉ በግብፅ በፈርዖን በሹማምንቱና በምድሪቱ ሁሉ ላይ እንዲያደርግ የላከውን ያደረገ ማንም ሰው አልነበረም።
12ሙሴ በእስራኤል ሁሉ ፊት ያሳየውን ታላቅ ኃይል ያሳየ ወይም ያደረገውን አስደናቂ ተግባር የፈጸመ ማንም ነቢይ የለም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።