1ሙሴም ወጥቶ እነዚህን ቃሎች ለእስራኤል በሙሉ ነገራቸው።
2እንዲህም አላቸው፦ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖኛል ከእንግዲህ መወጣትና መግባት አልችልም፤ እግዚአብሔርም ዮርዳኖስን አትሻገርም ብሎኛል፥
3እግዚአብሔር አምላካችሁ ራሱ በፊታችሁ ቀድሞ ይሄዳል፤ እነዚህንም አሕዛብ ከፊታችሁ ያጠፋቸዋል፤ እናንተም ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው፤ ኢያሱም እናንተን ቀድሞ ይሻገራል።
4እግዚአብሔር የአሞራውያንን ነገሥታት ሴዎንንና ዐግን ከነምድራቸው እንዳጠፋቸው እነዚህንም ያጠፋቸዋል።
5እግዚአብሔር እነርሱን በፊታችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋል፤ እናንተም ያዘዝኋችሁን ሁሉ በእነርሱ ላይ ታደርጋላችሁ።
6ብርቱና ደፋር ሁኑ፥ አትፍሯቸው ወይም አትደንግጡል አላቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ ከእናንት ጋር ይሄዳልና አይተዋችሁም አይጥላችሁምም።
7ከዚያም ሙሴ ኢያሱን ጠርቶ በእስራኤል ሁሉ ፊት እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ሊሰጥ ወደ ማለላቸው ምድር ከዚህ ሕዝብ ጋር አብረህ ስለምትገባ፤ ምድሪቱን ርስታችው አድርገህ ስለምታከፋፍል በርታ፤ ደፋርም ሁን።
8እግዚአብሔር ራሱ በፊትህ ይሄዳል፤ ከአንተም ጋር ይሆናል፤ ፈጽሞ አይለይህም፤ አተውህምም አትፍራ ተስፋም አትቁረጥ።
9ሙሴም ይህን ሕግ ጽፎ የእግዚአብሔርን የኪዳን ታቦት ለሚሸከሙ፥ ለሌዊ ልጆች፤ ለካህቱና ለእስራኤል አለቆች ሁሉ ሰጠ።
10ከዚያም በኋላ ሙሴ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ዕዳ በሚተውበት የዳስ በዓልም በሚከበርበት በየሰባቱ ዓመት መጨረሻ
11እስራኤል ሁሉ እርሱ በሚመርጠው ስፍራ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ሲታይ ይህ ሕግ በእነርሱ ፊት በጆሮአቸው ታነባቸዋላችሁ።
12እነርሱም ይስሙና አምላካችሁን እግዚአብሔርን መፍራት ይማሩ ዘንድ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ በጥንቃቄ እንዲከተሉ ሕዝቡን ይኸውም ወንዶችን፥ ሴቶችንና ልጆቻቸሁንና በከተሞቻችሁን የሚኖረውንም መጻተኛ ሰብስቡ።
13ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይህን ሕግ የማያውቁት ልጆቻቸሁም መስማትና አምላካችሁን እግዚአብሔርን መፍራት ሊማሩ ይገባቸዋል።
14እግዚአብሔር ሙሴን እነሆ የምትሞትበት ቀን ቀርቦአል፥ ትእዛዝ እንድሰጠው ኢያሱን ጥራውና ወደ መገናኛው ድንኳንም ቅረቡ።
15እግዚአብሔር በድንኳኑ ላይ በደመና ዐምድ ተገለጠ፤ የደመናውም ዐምድ ከድንኳኑ ደጃፍ ላይ ቆመ።
16እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ እነሆ ከአባቶቻችሁ ጋር ልታርፍ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚገባበት ምድር በሚገኙ አማልክት ወዲያውኑ ያመነዝራል፤ እኔን ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋር የገባሁትን ኪዳን ያፈርሳሉ።
17በዚያም ቀን ቁጣዬ በእነርሱ ላይ ይነዳል፤ እተዋቸዋለሁም። ፊቴንም ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይጠፋሉ። ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር ይደርስባቸዋል፤ በዚያም ቀን ይህ ጥፋት የደረሰሰብን አምላካችን ከእኛ ጋር ባለመሆኑ አይደለምን? ይላሉ።
18ወደ ባዕዳን አማልክት በመዞር በፈጸሙት ክፋታቸው የተነሣ በዚያን ቀን ፊቴን ከእነርሱ ፈጽሞ እሰውራለሁ።
19እንግዲህ ይህን መዝሙር ለራሳችሁ ጻፉና ለእስራኤል ልጆች አስተምሩ። ስለ እኔ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ እንዲዘምሩ አድርጉ።
20ወተትና ማር ወደምታፈሰውና ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባህላቸው ምድር ባመጣሃቸው ጊዜ ከበሉና ከጠገቡ፥ ከበለጸጉም በኋላ እኔን ንቀው ኪዳኔንም አፍርሰው ወደ ባዕዳን አማልክት ይዞራሉ፤ እነርሱንም ያመልካሉ።
21ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር በደረሰባቸው ጊዜ ይህ መዛሙር ምስክር ይሆንባቸዋል። በዘራቸውም አፍ የሚረሳ አይሆንም፤ ወደ ማልሁላቸው ምድር ሳላስገባቸው በፊት ምን ለማድረግ እንደሚያስቡ እንኳን አስቀድሜ አውቃለሁ።
22ስለዚህም ሙሴ ይህን መዝሙር በዚያን ቀን ጻፈና እስራኤላውያንን አስተማራቸው።
23እግዚአብሔርም ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በር ደፋር ሁን፤ የእስራኤልን ልጆች በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ታስገባቸዋለህና እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ በማለት ትእዛዝ ሰጠው።
24ሙሴ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የዚህን ሕግ ቃል በመጽሐፍ ጽፎ እንዳበቃ፤
25የእስራኤልን የኪዳን ታቦት የሚሸከሙ ሌዋውያንን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤
26ይህን የሕግ መጽሐፍ ውሰዱ፤ በዚያም በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ አኑሩት።
27ዐመፀኞችና አንገተ ደንዳኖች እንደ ሆናችሁ አውቃለሁ፥ተመልከቱ እኔ ዛሬ በሕይወት ከእናንተ ጋር እያለሁ እንኳን በእግዚአሔር ላይ እንደህ ካመፃችሁ ከሞትሁ በኋላማ እንዴት አታደርጉም?
28ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ ጠርቼባቸው ይህን ቃል ይሰሙ ዘንድ ብጆሮኣቸው እንድናገር ፤ የነገድ አለቆቻችሁን በሙሉና ሹሞቻችሁን ሁሉ በፊቴ ሰብስቡ።
29እኔ ከሞትሁ በኋላ ፈጽማችሁ እንደምትረክሱ ካዘዝኋችሁም መንገድ ዘወር እንደምትሉ አውቃለሁና። በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ስለምትፈጽሙ፤ ይህ የሚሆነው እጆቻችሁ በሠሯቸውም ነገሮች እርሱን ለቁጣ ስለምታነሣሡት በሚመጡት ዘመናት ጥፋት ይደርስባችኋል።
30ሙሴ የዚህን መዝሙር ቃል ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ ለተሰበሰበው ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በጆሮአቸው አሰማ።