መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 30

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በፊታችሁ ያስቀመጥሁት ይህ በረከትና መርገም ሁሉ በእናንተ ላይ ሲመጣና አምላካችሁ እግዚአብሔር በትኖአችሁ ከምትኖሩበት አሕዛብ መካከል ሆናችሁ፤
2ወደ ልባችሁ ተመልሳችሁ ነገሮቹን በምታስተውሉበት ጊዜ፥ እንዲሁም ዛሬ እኔ በማዝዛችሁ ሁሉ መሠረት እናንተና ልጆቻችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመልሳችሁ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ እርሱን ስትታዘዙ፤
3እግዚአብሔር አምላካችሁ ምርኮአችሁን ይመልስላችኋል፤ ይራራላችሁማል፤ እናንተን ከበተነበት አሕዛብ መካከል እንደ ገና ይሰበስባችኋል።
4ከሰማይ በታች እጅግ ሩቅ ወደ ሆነ ምድር ብትጋዙ እንኳ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከዚያ ይሰበስባችኋል፤ መልሶም ያመጣችኋል።
5የአባቶቻችሁ ወደ ሆነችው ምድር ያመጣችኋል፤ እናንተም ትወርሱታላችሁ፤ ከአባቶቻችሁ ይበልጥ ያበለጽጋችኋል፤ያበዛችሁማል።
6እግዚአብሔር አምላካችሁን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ እንድትወዱት፤በሕይወትም እንድትኖሩ እግዚአብሔር አምላካችሁ የእናንተንና የዘራችሁን ልብ ይገርዛል።
7አምላካችሁ እግዚአብሔር ይህን ርግማን ሁሉ በሚጠሉአችሁና በሚያሳድዱአችሁ ጠላቶቻችሁ ላይ ያደርገዋል።
8እናንተም ተመልሳችሁ ለእግዚአብሔር ትታዘዛላችሁ፥ ዛሬ እኔ የማዛችሁን ትእዛዛ ሁሉ ትጠብቃላችሁ።
9በዚያም እግዚአብሔር በእጃችሁ ሥራ ሁሉን በወገባችሁ ፍሬ በእንስሳታችሁ፥ ግልገሎችና በምድራችሁ ሰብል እጅግ ያበለጽጋችኋል። በአባቶቻችሁ ደስ እንደ ተሰኘ ሁሉ እግዚአብሔር እናንተንም በማበልጸግ ደስ ይለዋልና።
10ይህም የሚሆነው አምላካችሁን እግዚአብሔርን ከታዘዛችሁና በዚህ የሕግ መሕሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙንና ሥርዓቱን በመጠበቅ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ስትመለሱ ነው።
11ዛሬ የምሰጣችሁ ትእዛዝ ይህን ያህል አስቸጋሪ ወይም ከእናንተ የራቀ አይደለም።
12እንድንፈጽሙት አምጥቶ ይነግረን ዘንድ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? እንዳትሉ በሰማይ አይደለም።
13ደግሞም እንድናደርገው አምጥቶ ይነግረን ዘንድ ማን ባሕሩን ይሻገራል? እንዳትሉም ከባሕር ማዶ አይደለም።
14ነገር ግን ቃሉ ለእናንተ በጣም ቅርብ ነው፤ ታደርጉትም ዘንድ በአፋችሁና በልባችሁ ውስጥ ነው።
15እነሆ ዛሬ ሕይወትንና በረከትን፥ ሞትንና ጥፋትን በፊታችሁ አኑሬአለሁ።
16እግዚአብሔር አምላካችሁን እንድትወዱ በመንገዱም እንድትሄና ትእዛዙን፥ ሥርዓቱንና ሕጉን እንድትጠብቁ አዝዛችኋል፤ ከዚያም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ ትበዛላችሁም፤ አምላካችሁም ትወርሱአት ዘንድ በምትገቡበት ምድር ይባርካችህኋል።
17ዳሩ ግን ልባችሁን ወደ ኋላ በመለሰና ባትታዘዙ ለሌሎች አማልክት ለመስገድ ብትታለሉና ብታመልኩአችሁ፤
18በርግጥ እንደምትጠፉ እኔ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ትወርሱአት ዘንድ በምትገቡባት ምድር ብዙ አትኖሩባትም።
19ሕይወትንና ሞትን፥ በረከትንና ርግማንን በፊታችሁ እንዳስቀመጣችሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራችኋለሁ። እንግዲህ እናንተና ልጆቻችሁ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጡ፤
20ይኸውም እግዚአብሔር አምላካችሁን እንድትወዱ ቃሉን እንድታደምጥና ከእርሱ ጋር እንድትጣበቁ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕይወታችሁ ነው፤ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለሕስሐቅና ለያዕቆብ ሊሰጣቸው በማለላቸው ምድር ረጅም ዕድሜ ይሰጣችኋል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።