1ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ በፍጹም ብትታዘዙና እኔ ዛሬ የምሰጣችሁን ትእዛዘትን ሁሉ በጥንቃቄ ብትከተሉ አምላካችሁ እግዝአብሔር በምድር ላይ ከሚኖሩ አሕዝብ ሁሉ በላይ ከፍ ያደርጋችኋል።
2እግዚአብሔር አምላካችሁን ብትታዘዙ እነዚህ በረከቶች ሁሉ የእናንተ ይሆናሉ፤ አይለዩአችሁምም።
3በከተማና በእርሻ ትባረካላችሁ።
4የማሕፀናችሁ ፍሬ፥ የምድራችሁ አዝመራ፥ የእንስሳታችሁ ግልገሎች፥ የክብታችሁ ጥጃ፥ የበግና የፍየል ግልገሎቻችሁም ይባረካሉ።
5እንቅባችሁና ቡሓቃያችሁም ይባረካሉ።
6ስትጓዙ ትበረካላችሁ፤ ስትወጡም ትባረካላችሁ።
7እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የሚነሡ ጠላቶቻችሁን በፊታችሁ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል፤በአንድ አቅጣጫ ቢመጡባችሁ በሰባት አቅጣጫም ከእናንተ ይሸሻሉ።
8እግዚአብሔር በጎተራችሁና እጃችሁ በነካው ሁሉ በረከቱን ይልካል። አምላካችሁ እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ምድር ላይ ይባርካችኋል።
9የእግዚአብሔር የአምላካችሁ ትእዛዞች የምትጠብቁና በመንገዱ የምትሄዱ ከሆነ በማለላቸው ተስፋ መሠረት የተቀደሰ ሕዝቡ አድርጎ ያቆማችኋል።
10ከዚያ የምድር አሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ስም መጠራታችሁን ያያሉ፤ ይፈርሁማል።
11እግዚአብሔርም ሊሰጣችሁ ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር የማሕፀናችሁ ፍሬ፥ በእንስሳታችሁ፥ ግልገል፥ በምድራችሁም ሰብል፥ የተትረፈረፈ ብልጽግና ይሰጣችኋል።
12እግአብሔር ለምድራችሁ በወቅቱ ዝናብን ለመስጠትና የእጃችሁን ሥራ ሁሉ ለመባረክ መልካሙን መዝገብ ሰማዩን ይከፍትላችኋል፤ እናንተም ለብዙ አሕዛብ ታበድራላችሁ እንጂ ከአንዳቸውም አትበደሩም።
13እግዚአብሔም ራስ እንጂ ድራት አያደርጋችሁም፤ ዛሬ የምሰጣችሁን የአምላካችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በጥንቃቄ ብትጠብቁ መቼውንም ቢሆን በላይ እንጂ ፈጽሞ በታች አትሆኑም።
14ሌሎች አማልክት በመከተል እነርሱን በማገልገል ዛሬ ከምሰጣችሁ ትእዛዞች ቀኝም ግራም አትበሉ።
15ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ባትታዘዙ በዛሬዋ ዕለት የምሰጣችሁን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ሁል በጥንቃቄ ባትከተሉአቸው እነዚህ ርግማኖች ሁሉ ይደርሱባችኋል፤ ያጥለቀልቁአችኋልም።
16በከተማ ትረገማላችሁ፤ በእርሻም ትረገማላችሁ።
17እንቅባችሁና ቡሓቃያችሁ የተረገሙ ይሆናሉ።
18የማሕፀናችሁ ፍሬ፥ የእርሻህ ሰብል፥ የመንጋችሁ ጥጆች፥ የበግና የፍየል ግልገሎቻችሁ ይረገማሉ።
19ስትገቡ ትረገማላችሁ፤ ስትወጡም ትረገማላችሁ።
20እርሱን በመተው ክፉ ድርጊት ከመፈለጋችሁ የተነሣ እስክትደመስሱ ፈጥናችሁም እስክትጠፉ ድረስ እጃችሁ በነካው ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ርግማንን መደናገርንና ተግሣጽን ይሰድባችኋል።
21እግዚአብሔር ልትወርሱአት ከምትገቡባት ምድር ላይ እስኪያጠፋችሁ ድረስም በደዌ ይቀሥፋችኋል።
22እግዚአብሔር እስክትጠፉ ድረስ በሚቀሥፍ ደዌ ትኩሳትና ዕባጭ ኃይለኛ ሙቀትና ድርቅ ዋግና አረማሞ ይመታችኋል።
23ከራሳችሁ በላይ ያለው ሰማይ ናስ ከእግራችሁ በታች ያለው ምድርም ብረት ይሆናል።
24እግዚአብሔር የምድራችሁን ዝናብ ወደ አቧራነትና ወደ ትቢያነት ይለወጠዋል፤ ይህም እስክትጠፉ ድረስ ከሰማይ ይወርድባችኋል።
25እግዚአብሔር በጠላቶቻችሁ ፊት እንድትሸነፉ ያደርጋችኋል፤ በአንድ አቅጣጫ ትመጣበቸዋላችሁ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሽሻላችሁ ለምድር መንግሥታትም ሁሉ መሸማቀያ ትሆናላችሁ።
26ሬሳችሁ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት ሲሳይ ይሆናል፤ በማስፈራራትም የሚያባርሩአቸው አይኖርም።
27እግዚአብሔር በማትድኑበት በግብፅ ብጉጅ፥ በእባጭ በሚመግል ቁስልና በእከክ ያሠቃያችኋል።
28እግዚአብሔር በእብደት፥ በዕውርነትና ግራ በማጋባት ያስጨንኣቃችል።
29በእኩለ ቀን በጨለማ እንዳለ ዕውር በዳበሳ ትሄዳላችሁ። የምታደርጉት ሁሉ አይሳካላችሁም። በየዕለቱ ትጨቆናላችሁ፤ ትመዘበራላችሁም፤ የሚታደጋችሁም አይኖርም።
30ሚስት ለማግባት ልጃገረድ ታጫላችሁ ሌላው ግን ወስዶ በኃይል ይደፍራታል። ቤት ትሠራላችሁ፤ ግን እናንተ አትኖሩበትም። ወይን ትተክላላችሁ ፍሬውን ግን አትበሉም።
31በሬህ ዐይናችሁ እያየ ይታረዳል፤ ከሥጋውም አንዳች አትቀምሱም። አህያችሁም በግድ ይወሰድባችኋል፤ አትበሉም። በጎቻችሁ ለጠላቶቻችሁ ይሰጣሉ፤ የሚያሰጥላቸውም አይኖርም።
32ወዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ለባዕድ ሕብብ ይሰጣሉ፤ እጃችሁንም ለማንሣት እቅም ታጣላችሁ፤ ይመጣሉ፤ በማለትም ዐይኖቻችሁ ሁልጊዜ እነርሱን በመጠባበቅ ይደክማሉ።
33የምድራችሁንና የድካማሁን ፍሬ ሁሉ የማታውቁት ሕዝብ ይበላዋል፤
34ሁልጊዜ በጭቆናና በጫን ትኖራላችሁ፤ በምታዩት ሁሉ ትጃጀላላችሁ።
35እግዚአብሔር ከእግራችሁ ጥፍር እስከ ራስህ ጠጉር በሚወርር ሊድን በማይችልና በሚያሠቃይ ቁስል ጉልበታችሁንና እግራችሁን ይመታችኋል።
36እግዚአብሔር እናንተንና በላያችሁ ያነገሣችሁትን ንጉሥ፥ እናንተና አባቶቻችሁ ወደ ማታውቁት ሕዝብ ይወሰዳችኋል፤ ከዚያም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማክልትን ታመልካላችሁ።
37እግእብብሔር እንድትገቡ በሚመራችሁ ምድር ለአሕዛብ ሁሉ መሸማቀቂያ ማላገጫና መዘባበቻ ትሆናላችሁ።
38በእርሻ ላይ ብዙ ዘር ትዘራላችሁ አንበጣ ስለሚበላው የምትሰበስቡ ጥቂት ይሆናል። ወይን ትተክላላችሁ ትንከባከበዋላችሁ፤
39ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጡም ዘለላውንም አትሰበስቡም።
40በአገራችሁ ምድር ሁሉ የወይራ ዛፍ ይኖራችኋል፤ ፍሬው ስለሚረግፍባችሁ ግን ዘይቱን አትቀቡም።
41ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻችሁን ትወልዳላችሁ ነገር ግን በምርኮ ስለሚወሰዱ፤ አብረዋችሁ አይኖሩም።
42ዛፋችሁንና የምድራችሁን ሰብል ሁሉ አንበጣ መንጋ ይወረዋል።
43በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ ከእናንተ በላይ ከፍ ከፍ ሲል እናንተ ግን ዝቅ ዝቅ ትላላችሁ።
44እርሱ ያበድራችኋል እንጂ እናንተ አታበድሩም። እርሱ ራስ ይሆናል፤ እናንተ ግን ጅራት ትሆናላችሁ።
45እነዚህ ርግማኖች እስክትጠፉ ድረስ ይከተሉአችኋል፤ ሁሉ በእናንተ ላይ ይመጣሉ፤ ይህም የሚሆነው አምላካችሁን እግዚአብሔርን ስላልታዘዛችሁና የሰጣኋችሁን ትእዛዝና ሥርዓት ስላልጠበቃችሁ ይወርዱባችኋልም።
46እነዚህ ርግማኖች እንደ ምልክትና ድንቅ ነገሮች ሆነው በእንንተና በዘራችሁ ለዘላለም ይሆናል።
47በብልጽግና ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁን በደስታና በሐሤት ስላላገለገችሁ በራብና በጥም በእርዛትና በከፋ ድኽነት
48እግዚአብሔር የሚያስነሣባችሁን ጠላቶቻችሁን ታገለግላላችሁ፤ እስኪያጠፉአችም ድረስ በአንገታችሁ ላይ የብረት ቀንበር ይጭንባችኃል።
49እግዚአብሔር እንደ ንስር በፈጣን የሚበሩና ቋንቋውን የማታውቁአችሁን ሕዝብ እጅግ ሩቅ ከሆነ፥ ከምድርም ዳርቻ ያስነሣነሰባችኋል፤
50ሽማግሌ የማያከብር፥ ለወጣትም መልካም ያልሆኑና የሚያስፈራና ጨካኝ ሕዝብ ነው።
51እስክትጠፉም ድረስ የእንስሳታችሁን ግልገልና የምድራችሁን ሰብል ይበላል፤ እስኪያጠፋችሁም ድረስ እህል፤አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት የመንጋችሁን ጥጃና የበግና ፍየል መንጋችሁን ግልገል አያስቀሩላችሁም።
52የምትታመኑባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪወድቁ ድረስ በመላው አገራችሁ ያሉትን ከተሞቻችሁን ሁሉ ይከባል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሚሰጥጣችሁምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወራቸዋል።
53ጠላቶቻችሁ ከበው በሚያስጨንቁአችሁ ጊዜ ከሥቃይ የተነሣ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሰጣችህን የአብራካችሁ ፍሬ የሆኑትን የወንዶችና የሴቶች ልጆቻችሁን ሥጋ ትበላላችሁ።
54ሌላው ይቅርና በመካከላችሁ በጣም ደግና ርኅሩኅ የሆነው ሰው እንኳ ለገዛ ወንድሙ ወይም ለሚወዳት ሚስቱ ወይም ለተረፉት ልጆቹ አይራራላቸውም።
55ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ላይም ቅንጣት ያህል እንኳ ከእነርሱ ለአንዱ አያቀምስም፤ ከተሞቻችሁ ሁሉ በመከበባቸው ጠላቶቻችሁ ከሚያደርሱባችሁ ሥቃይ የተነሣ ለእርሱ የቀረለት ይህ ብቻ ነውና።
56በመካከላችሁ ተመቻችታና ተቀማጥላ የምትኖር ከልስላሴና ከቅምጥልነት የተነሣ እግሯን አፈር ነክቶት የማያውቅ ሴት የምትወደውን ባሏን፥ የገዛ ወንድና ሴት ልጆቿን ትንቃለች።
57ከማሕፀኗ የወጣውን የምትወልዳቸውን ሕፃናት ትጠየፋለች፤ በመከራው ወቅት ጠላቶቻችሁ ከተሞቻችሁን ከበው በሚያስጨንቁአችሁ ጊዜ ሌላ የሚበላ ስለማይኖር እነርሱን ደብቃ ትበላለች።
58በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን የዚህን ሕግ ቃሎች ባትከተሉና የተከበረውና አስፈሪ የሆነውን የአምላካችሁን
59የእግዚአብሔርን ስም ባታከብሩ እግዚአብሔር አስፈሪ መቅሠፍት፥ አስጨናቂና ለብዙ ጊዜ የሚቋይ መዓት አሠቃቂና በቀላሉ የማይወገድ ደዌ በእናንተና በዘሮቻችሁ ላይ ይልክባችኋል።
60የምትፈሩአችሁንም የግብፅ በሽታዎች ሁሉ ያመጣባችኋል፤ በእናንተም ላይ ይጣበቃሉ።
61ደግሞም እግዚአብሔር በዚህ የሕግ መጽሐፍ ያልተጸፈውን ማንኛውንም ዓይነት ደዌና መከራ እስክትጠፉ ድረስ ያመጣባችኋል።
62ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ስላልታዛዝችሁ እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝታችሁ ቢሆን እንኳ እናንተ ጥቂት ብቻ ትቀራላችሁ።
63እግዚአብሔር ለእናንተ መልካም በማድረግና ቁጥራችሁን በማብዛት ደስ እንዳተሰኘ ሁሉ ፤ እናንተን በመደምሰስና በማጥፋት ደስ ይለዋል። ከምትወርሱዋት ምድር ትነቀላላችሁ።
64ከዚያም እግዚአብሔር ከአንዱ የምድር ዳርቻ እስከ ሌላው ዳርቻ በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይበትናችኋል። በዚያም አባቶአኣችሁ የማታውቋቸውን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማልክትን ታመልካላችሁ።
65በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍት አታገኙም፤ ለእግራችሁም ጫማ ማረገጫ አይኖርም፤ እዚያም እግዚአብሔር የሚጨነቅ አእምሮ፥ የሚደክም ዐይንና ተስፋ የሚቋርጥ ልብ ይሰጣችኋል።
66ዘመናችሁን በሙሉ ቀንና ሌሊት በፍርሃት እንደ ተዋጣችሁ ሕይወትታችሁ ዘወትር በሥጋት ትኖራላችሁ።
67ልባችሁ በፍርሃት ከመሞላቱና ዐይናችሁ ከሚያየው ነገር የተነሣ ሲነጋ ምነው አሁን ሲመሽ ፥ደግሞ ምነው አሁን በነጋ ትላላችሁ።
68ዳግመኛ አትመለሱባትም ባልሁ መንገድም እግዚአብሔር በመርከብ ወደ ግብፅ ይመልሳችኋል። እዚያም እንደ ወንድና ሴት ባሪያ ለጠላቶቻችሁ ለመሸጥ ራሳችሁን ታቀርባላችሁ የሚገዛችሁ ግን አይኖርም።